2022 (እ.አ.አ)
አዳዲስ ተጠማቂዎች ማጠናከር
ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)


የክልል አመራር መልእክት

አዳዲስ ተጠማቂዎች ማጠናከር

ሌሎች ሰዎች የአካል ክፍል እንደሆኑ እንዲሰማቸው ስንረዳ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው ሲያምኑ፣ ወደ ጌታ ለመለወጥ እና በዳግም ከተመለሰችው ቤተክርስቲያን ጋር አንድ ይሆናሉ—እንዲሁም ለመሆን ይችላሉ።

ነቢዩ ሞሮኒ በጥምቀት ሥርዓት ወደ ክርስቶስ ስለሚመጡት እና የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በእነሱ ላይ ለመውሰድ ቃል ኪዳን ስለሚገቡት እንዲህ አስተምሯል፣ “እናም እርሱን ሁል ጊዜ አስታውሱ እና የሰጣቸውን ትእዛዛቱን ጠብቁ”1

““እናም ከተጠመቁ እናም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በላያቸው ላይ ከሰራ እናም ካነፃቸው በኋላ፣ ከክርስቶስ ቤተክርስቲያን ህዝቦች ጋር ተቆጥረዋል፤ እናም እነርሱን በትክክለኛው መንገድ ለማቆየት፣ የእምነታቸው ደራሲ እና ፈፃሚ በሆነው በክርስቶስ በጎ ሥራ ላይ ብቻ በመደገፍ ፀሎታቸውን ያለማቋረጥ እንዲሚቀጥሉ ለመጠበቅ፣ የእግዚአብሔርን መልካም ቃል በመመገብ ይታወሱ ዘንድ ስማቸው ተወስደዋል”2

ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳስተማሩት፣ “በመጋረጃው በሁለቱም በኩል ላሉት፣ በማንኛውም ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ እና እንዲጠብቁ ማንንም የሚረዳ ነገር ስናደርግ፣ እስራኤልን ለማሰባሰብ እየረዳን ነን”3። ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ (1910–2008) እንድናስታውስ እንዳደረጉን፣ “እያንዳንዱ ተቀያሪ ውድነው። እያንዳንዱ ተቀያሪ የእግዚአብሒእር ወድ ወይም ሴት ልጅ ነው። “እያንዳንዱ ተቀያሪ ታላቅ እና ከባድ ሀላፊነት ነው”4። በዚህ የኋለኛው ዘመን ታላቅ ስራ ስንሳተፍ የእኛ አካል የሆኑትን ሰዎች መንከባከብ በጣም አስፈላጊ ነው።

የእኛ ኃላፊነት የመድኃኒታችንና የቤዛችን የኢየሱስ ክርስቶስን በመንፈስ አነሳሽነት ምሳሌ መከተል ነው፤ እርሱም ወደ ሟች አገልግሎቱ መጨረሻ ሲቃረብ፣ ለአብ እንዲህ ብሏል፣ “የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና። እነርሱም ተቀበሉአቸው ከአንተም ዘንድ እንደ መጣሁ በእውነት አወቁ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።

እንዲህም በማለት ቀጠለ “የሰጠኸኝን በስምህ እኔ እጠብቃቸው ነበር፤ … ከእነርሱ ማንም አልጠፋም”5.

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ እግዚአብሔር በሕይወታቸው እንዲያሸንፍ የወሰኑትን ሰዎች ሁኔታ በደንብ የምንረዳው እኛ ነን። ይህ ከሰማይ አባታችን ጋር የምንገባው የቃል ኪዳን አካል ነው—በተለይ፣ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በንግግራችን፣ በሁሉም ጸሎታችን፣ በሁሉም ምክር እና በድርጊቶቻችን ሁሉ እናበረታታለን 6.

በ1999 (እ.አ.አ)፣ በቤተክርስቲያኗ አዲስ የተጠመቀች ሴት ለፕሬዘዳንት ጎርደን ቢ. ሂንክሊ የሚከተለውን ደብዳቤ ጻፈች፦ “‘የእኔ የቤተክርስቲያኗ አባልነት ጉዞ ልዩ እና በጣም ፈታኝ ነበር። ይህ ያለፈው አመት በህይወቴ ከኖርኩባቸው ጊዜያት ሁሉ በጣም አስቸጋሪው አመት ነው። እጅግ በጣም የሚክስም ነበር። እንደ አዲስ አባል፣ በየቀኑ መገዳደሬን እቀጥላለሁ፣’…

“‘የቤተክርስቲያኗ አባላት አዲስ የቤተክርስቲያን አባል መሆን ምን እንደሚመስል አያውቁም። ስለዚህ፣ እኛን እንዴት እንደሚደግፉ ማወቅ ለእነሱ ፈጽሞ የማይቻል ነገር ነው።’…

“እንዲህም በማለት ቀጠለች፣

“‘እኛ እንደ መርማሪዎች የቤተክርስቲያን አባላት ስንሆን፣ የራሱ ወጎች፣ ባህል እና ቋንቋ ያለው ዓለም ውስጥ መግባታችንን ስናውቅ እንገረማለን። ወደዚህ አዲስ ዓለም በምናደርገው ጉዞ መመሪያ ለማግኘት የምንፈልገው አንድ ሰው ወይም አንድም የማመሳከሪያ ቦታ እንደሌለ እናገኛለን። መጀመሪያ ላይ ጉዞው አስደሳች ነው፣ ስህተታችንም አስቂኝ ነው፣ ከዚያም ያበሳጫል እና በመጨረሻም ብስጭት ወደ ቁጣ ይለወጣል። እና በእነዚህ የብስጭት እና የቁጣ ደረጃዎች ላይ እንወጣለን። ወደ መጣንበት፣ ማንነታችንን ወደምናውቅበት፣ መሳተፍ ወደምንችልበት፣ እና ቋንቋውን ወደምንችልበት ዓለም እንመለሳለን።’”7

በቅርብ የተለወጡ ሰዎችን ለማጠናከር እንዲረዳን፣ ጌታ በህያው ነቢያችን፣ ፕሬዘደንት ኔልሰን፣ ሌሎችን ለመንከባከብ እና ለመደገፍ አዲስ፣ የተቀደሰ አቀራረብን ገልጿል። “አገልግሎት” እየተባለ የሚጠራው ይህም ህዝባችንን የምንጠብቅበት እና ከጽድቅ ጋር በተያያዙ ነገሮች የምንመግብበት ነው8። ጸሎቴ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ሁላችንም እርስ በርሳችን ለመተሳሰብ እንድንቆርጥ ነው—በተለይም በቅርብ ወደ ቤተክርስቲያን ወደተለወጡት።

በመነጋገር፣ በማዳመጥ፣ በመምራት፣ ጥያቄዎቻቸውን በመመለስ፣ ፈገግ በማለት እና በመመገብ ልናደርገው እንችላለን። እነዚህ ቀላል ድርጊቶች ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን በሌሎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። እነርሱ በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ለመቆየት እና ለመራመድ በሚያደርጉት ጥረት ብቸኝነት እንዳይሰማቸው፣ ነገር ግን በክርስቶስ ቤተሰብ ውስጥ የመሆን ስሜት እንዲሰማቸው ሌሎችን መርዳት አለብን9.

በቅርብ ጊዜ እንደ ተለወጡ ወደ ቤተክርስቲያኗ ለሚመጡት በጓደኝነት እና በፍቅር እንድትገናኙ እጋብዛችኋለሁ። ብቻቸውን እንዲቆሙ ልንተዋቸው አንችልም። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን መንገዶች እና ባህል ለመላመድ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

እንዴት መጸለይ እንዳለባቸው፣ ቅዱሳት መጻህፍትን እንዴት እንደሚያጠኑ፣ እንዴት እንደሚመሰክሩ፣ አሥራት እና የጾም ቁርባንን እንዴት እንደሚከፍሉ እንርዳቸው—ወደ ሴሚናሪ ክፍሎች ወይም የሃይማኖት ተቋም ትምህርቶች እንጋብዛቸው፣ እንዴት የቤተሰብ የቤት ምሽት መያዝ እንዳሚችሉ፣ በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ስራ እንዴት እንደሚሳተፉ፣ እንዴት ወደ ቤተመቅደስ ለውክል ስነስርዓቶች ስም መላክ ወይም መውሰድ እንደሚቻሉ እንዲያውቁ እንርዳቸው። ልክ እንደተጠመቁ ከእኛ ጋር ቤተ መቅደሱን ለመጎብኘት እንውሰዳቸው።

እነዚህን ነገሮች ብናደርግ፣ ጽዮን በዚህ በመካከላችን እንደምትቋቋም ቃል እገባላችኋለሁ። ሌሎች ሰዎች የአካል ክፍል እንደሆኑ እንዲሰማቸው ስንረዳ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው ሲያምኑ፣ ወደ ጌታ ለመለወጥ እና በዳግም ከተመለሰችው ቤተክርስቲያን ጋር አንድ ይሆናሉ—እንዲሁም ለመሆን ይችላሉ።

ቲየሪ ኬ. ሙቶምቦ በሚያዝያ 2020 (እ.አ.አ) እንደ አጠቃላይ ባለስልጣን ሰባ ተደግፈዋል። እርሳቸውም ትሼዪ ናተሊ ሲንዳን ጋረ የተጋቡ ናቸው፤ እነርሱም የስድስት ልጆች ወላጆች ናቸው።

ማስታወሻዎች

  1. ሞሮኒ 4፥3።

  2. ሞሮኒ 6፥4።

  3. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “እግዚአብሔር ያሸንፍ፣” ጥቅት 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።

  4. Teachings of Presidents of the Church: Gordon B. Hinckley, [2016], 298; ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ “ተቀያሪዎች እና ወጣት ወንዶች፣” ሚያዝያ 1997 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ።

  5. ዮሀንስ 17፥8፣ 12።

  6. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 108፥7 ይመልከቱ።

  7. Teachings of Presidents of the Church: Gordon B. Hinckley, 300–301; “በጎቹን ፈልጉ፣ በጉን መግቡ፣” ኤንዛይን፣ ግንቦት 1999 (እ.አ.አ)።

  8. ሞዛያ 23፥18 ይመልከቱ።

  9. ኤፌሶን 2:19 ይመልከቱ።

አትም