2022 (እ.አ.አ)
አዳዲስ አባላትን ማጠናከር
ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ መሪ መልዕክት

አዳዲስ አባላትን ማጠናከር

ጌታ አዲስ ከተጠመቁ አባላት ጋር ግንኙነት እንድንመሰርት እና እንድንረዳቸው ይፈልጋል።

የሰማይ አባታችን ፍቅር ነው፤ሁሉንም ልጆቹን በፍጹም ፍቅር ይወዳቸዋል። አንዳቸውም እንዳይጠፉ እያንዳንዱ ነፍስ ዋጋ እንዲሰጠው እንዲሁም በእኩልነት እንክብካቤ እንዲያኝ ይፈልጋል።1

አዲስ የተጠመቁ አባላት ፍቅር ያስፈልጋቸዋል፤ አንድ የሚንከባከባቸው ሰው ይፈልጋሉ። የወንጌልን ትምህርት እንዲረዱት ሊረዳቸው የሚችል ሰው ያስፈልጋቸዋል።

ከተዘራ ዘር ጋር ሊነጻጸሩ ይችላሉ። ዘሩ ከመዘራቱ በፊት አፈሩን በደንብ ማዘጋጀት እና መሬቱን ለም ለማድረግ ማዳበሪያ መጨመር አስፈላጊ ነው። አፈሩ ከተዘጋጀና ለምነቱን ለመጠበቅ ማዳበሪያ ከተጨመረበት በኋላ ዘሩ ይዘራል፤ ከዚያም ውሃ በማጠጣት እና በየቀኑ የጸሃይ ብርሃን የሚያገኝ መሆኑን በማረጋገጥ ዘሩ በትክክል እንዲያድግ ጥንቃቄ ይደረጋል። በተጨማሪም የዘሩን ትክክለኛ እድገት የሚያውክ መጥፎ አረም በአፈር ውስጥ እየበቀለ እንዳልሆነ እናረጋግጣለን።

አዳዲስ አባላት የእኛን ደግነት እና እንክብካቤም ይሻሉ። እምነታቸውን ሊነቀንቁ የሚችሉ ነገሮች ወይም ሰዎች ሲያጋጥሟቸው እንዳይወድቁ ለማበርታት ከተጠመቁ በኋላ ከወንጌል መመገብ ያስፈልጋቸዋል።

በተሰብሳቢዎች መሃል አዲስ ፊት ስንመለከት እንዲሁም ለዚያ ሰው አሳቢነት ማሳየታችን በጣም አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ በርግጥ መለወጣችንን እና ትሑት መሆናችንን ያሳያል። እነዚህ በእኛ እይታ እዚህ ግባ የማይባሉ የሚመስሉ ቀላል ድርጊቶች ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ እና በመካከላችን ባሉ አዳዲስ አባላት ሊታወሱ ይችላሉ።

ከሃያ አመት በፊት አባል በነበርኩበት ካሳቩቡ አጥቢያ የተጠመቀችን አንዲት እህት አስታውሳለሁ። አንድ ቀን እህቶች ካዘጋጇቸው አክቲቪቲዎች በአንዱ በተካፈልኩበት ወቅት በእኔ ሞቅ ያለ አቀባበል እና አሳቢነት በቤተክርስቲያን ለመጠንከር እንደቻለች ስለእኔ (እህት ታር) ምስጋና በማቅረብ ምስክርነቷን ስትሰጥ በመስማቴ ተገርሚያለሁ።

በትክክል ምን እንዳደረኩኝ ማስታወስ ስላልቻልኩኝ ስለዚህ በጣም የሚነካ ምስክርነት ማሰብ ጀመርኩኝ። መደምደሚያዬም ለምናገኛቸው አዳዲስ ሰዎች ትልቅ ነገሮችን እስክናደርግ መጠበቅ አይኖርብንም። ቀላል፣ ወዳጅነትን የሚያንጸባርቁ ነገሮችን ማድረግ እንችላለን።

በጣም ቀላል በሆኑ መንገዶች እንድንንቀሳቀስ ለሚገፋፋን ለስላሳ የመንፈስ ቅዱስ መነሳሳት ዝግጁ እንሁን።ያ አንዳንድ ጊዜ ፈገግታ፣ለሌሎች አቀባበል ማድረግ ወይም አሳቡነትን ማሳየት ሊሆን ይችላል።

የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ውስጥ እንዲያድር በልባችን ውስጥም ጥልቅ ለውጥ እንዲያመጣ ከእንግዲህም ስህተት መስራትን እንዳንሻ ይልቁንም የእግዚአብሔርን ነገሮች እንፈልግ ዘንድ በእውነት ዳግመኛ የተወለድን ለመሆን እንስራ።

ይህ የልብ ለውጥ ይበልጥ ትሁት፣ አፍቃሪ ተግባቢ ሰዎች እንድንሆን ይረዳናል። አዳዲስ አባላትን ወዲያውኑ ወደቤተክርስቲያን ለመቀበል ፈቃደኞች እንሆናለን።

አዳዲስ አባላት የሚያስፈልጓቸውን ድጋፍ የሚሰጧቸው ተገቢ የሆኑ ሰዎችን ይፈልጋሉ። እጅን በመጫን እና መንፈስ ቅዱስን በመቀበል የቤተክርስቲያን አባልነት ማረጋገጫ ተሰጥቷቸዋል። ከዚያም መንፈስ ቅዱስ ታማኝ ሆነው ይቀጥሉ ዘንድ የወንጌልን አስተምህሮቶች እና ትምህርቶች ወደ ልባቸው ማምጣት እና ማረጋገጥ መስጠት ይችላል።

አዲስ አባል እያለሁ ጠንክሬ ለመቆም፣ ንስሃ ለመግባት እንዲሁም በቃልኪዳኑ መንገድ ለመቆየት መርጬ ነበር። እነዚህ ሁለት ጥቅሶች ከብዙዎቹ መካከል የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድገነዘብ የረዱኝ ናቸው። ሞዛያ 4፥9–15, መዝሙር 104፥33–34።

እህት ካቦንጎ አንጀሊክ ታር በዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ምዌኔ ዲቱ ካሳይ ኦሬንታል ውስጥ ተወለደች። እርሷ እና ባለቤትዋ የአምስት ልጆች ወላጆች ሲሆኑ የአካባቢ ድርጅት አማካሪ ተደርጋ የተጠራችውም ሃምሌ 2021(እ.አ.አ) ነው።

ማስታወሻዎች

  1. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥15–16 ይመልከቱ።

አትም