የቃልኪዳን መንገዴ
ተስፋ መቁረጥን እና መሰናክሎችን መቋቋም
የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ በጨለማ የህይወታችን ጊዜያት ብርሃን እንዲፈነጥቅ ማድረግ ይችላሉ።
እያንዳንዱ ቀን እውቅና የሚቸረው፣ የሚያስደስት እና የሚደነቅ ብዙ የደስታ ጊዜያት አሉት። ሆኖም አንዳንድ ጊዜ –ፈተናዎች፣ ተስፋ መቁረጥ፣ የስሜት ጉዳት፣ የተዛባ አመለካከት ደመናዎች በመንገዳችን ይጋረጡና ዘላለማዊ ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ነገሮች ይጋርዱብናል። ይህ ህይወት እንድናድግ እና ለዘለአለም ደስታ እንድንዘጋጅ በሚረዱ ልምዶች የተሞላ ነው።
በ“ኑ፤ ተከተሉኝ” የጥናት ማንዋላችን ውስጥ ካለው የፍጥረት ታሪክ እግዚአብሔር ካልተደራጀ ነገር አስደናቂ ነገርን መሥራት እንደሚችል እንማራለን። ምናልባት እኛም የወንጌል መርሆዎችን ለመኖር በምናደርገው ጥረት አልፎ አልፎ በመጠኑ “ያልተደራጀን” እንሆናለን።
“የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጣሪዎች ናቸው፤ እኛን የመፍጠር ስራቸውም ገና አላለቀም በጨለማ የህይወታችን ጊዜያት ብርሃን እንዲፈነጥቅ ማድረግ ይችላሉ። በህይወት ማዕበል አዘል ባህር ውስጥ ጠንካራ መሬት መፍጠር ይችላሉ…ልንሆን ወደታሰብነው ቆንጆ ፍጥረታት ሊለውጡን ይችላሉ።”1
ፈተናዎቻችን በጣም ከባድ ሲመስሉን እና ተስፋ መቁረጥ ሲጎበኘን አዳኛችን በጸጋው የሰጠንን የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ እና የድፍረት ስጦታ እንደገና ለመላበስ ልናደርጋቸው የምንችላቸው አንዳንድ ተጨባጭ ነገሮች እነሆ፦
-
በጸሎት ትጉ—በተለይ ስለሚያስጨንቁን ነገሮች እንናገር ከዚያም ዝም ብለን እናዳምጥ። ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፦ “ልባችሁን፣ አእምሯችሁን እና ነፍሳችሁን ይበልጥ ወደሰማይ አባታችን እና ወደልጁ ወደኢየሱስ ክርስቶስ እንድትመልሱ እጋብዛችኋለሁ።”2
-
ቅዱሳን ጽሁፎችን ማንበባችሁን ቀጥሉ—ከራሳችን ጋር በማመሳሰል መነሳሳትን እና ማስተዋልን ማግኘት እንችላለን።
-
በጌታ እርዳታ የሚያስጨንቁንን ነገሮች መገምገም። እነዚህን ጥያቄዎች እራሳችንን ልንጠይቅ እንችላለን፦ እኛ ምንን በተለየ መንገድ መስራት ያስፈልገናል? አኛ ምን ማድረግ እንችላለን? ጌታ እኛን ለመርዳት ምን ሊያደርግ ይችላል?
መንገዶቻችንን ለመቀየር እና ዘላለማዊ እይታችንን ለመያዝ ከልብ ፈቃደኞች ነን? የእኛን ፈቃድ ለጌታ ፈቃድ ለማስገዛት ፈቃደኞች ነን? ለአዳዲስ ማስተዋሎች እና ምክር የድጋፍ ቡድናችን ወደሆኑት ወደእግዚያብሄር፣ ወደቤተሰብ፣ ወደጓደኞች ለመዞር ፍቃደኞች ነን? ለጌታ መነሳሳት ምላሽ ለመስጠት እና ለመከተል ፍቃደኞች ነን?
-
የጌታን ሰዓት ለማድነቅ ጣሩ—መከራችንን እና ራሳችንን እንታገስ።
-
አዳኛችን እና ሰማይ አባት ስለሰጡን እርዳታዎች እና በረከቶች አመስጋኝነታችንን ለመግለጽ ጊዜ ይኑረን። በእነሱ እርዳታ የምናደርጋቸውን እያንዳንዷን እድገት እውቅና መስጠት እና ማክበር እንችላለን።
ሽማግሌ ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዲህ ብለዋል “አሁን ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ተስፋ አለን። ምንም ብንጨነቅ፣ ምንም ብናዝን፣ ምንም ብንሳሳት፣ ማለቂያ የሌለው ርህራሄ ባለቤት የሆነው የሰማይ አባታችን ወደ እኛ ይቀርብ ዘንድ ወደ እርሱ እንድንቀርብ ይፈልጋል። ልባችንን በአስደናቂ ደስታ ይሞላል፣ አስከፊ መጥፎ ሁኔታዎቻችንን በተባረከ ሰላም ያበራልናል፣ ውድ የሆኑ እውነቶችን በአእምሯችን ውስጥ ያኖራል፣ በመከራ ጊዜ ይጠብቀናል፣ ስንደሰት ይደሰታል እንዲሁም የጽድቅ ልመናዎቻችንን ይመልሳል።3
በጥቅምት 2020 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ መጨረሻ ላይ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ይህንን በረከት ሰጥተውናል፦ “በኢየሱስ ክርስቶስ ደስታ እንድትሞሉ እባርካችኋለሁ። የእርሱ ሰላም ሁሉም ሟቾች ሊገነዘቡት ከሚችሉት በላይ ነው። የእግዚአብሔርን ህግጋት ለመታዘዝ የላቀ ፍላጎት እና ችሎታ እንዲኖራችሁ እባርካችኋለሁ። ይህንን ስታደርጉ ታላቅ ድፍረትን፣ የላቀ የግል መገለጥን፣ በቤት ውስጥ ጣፋጭ ስምምነትን እንዲሁም እርግጠኝነት በሌለበትም ጊዜ እንኳን ደስታ ማግኘትን ጨምሮ በበረከቶች እንደምትጥለቀለቁ ቃል እገባላችኋለሁ።”4