የአባል ድምጾች
እምነት በሰማይ አባት እንዲሁም በአዳኛችን እና በቤዛችን በኢየሱስ ክርስቶስ
በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለን እምነት አማካኝነት በህይወታችን ውስጥ ያሉትን ተራራዎች ማንሳት እንችላለን።
በ2021 አጠቃላይ ጉባኤ ወቅት ውዱ ነቢያችን ረስል ኤም. ኔልሰን ሁልጊዜ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት እንዲኖረን እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለን እምነት አማካኝነት በህይወታችን ውስጥ ያሉትን ተራራዎች ማንሳት እንደምንችል አስተምሮናል።1
ይህ መልዕክት ነክቶኛል፤ እንዲሁም በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ በያውንዴ በተደረገው የአውራጃ ጉባኤ ላይ ከአንዳንድ የቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር ያደረግናቸውን ውይይቶች አስታወስኩኝ። በዚህ ውይይት ወቅት እያንዳንዱ መሪ ምስክርነቱን/ቷን ሰጠ/ች፤ እኔ እና ባለቤቴ ምስክርነታችንን በመስጠታችን ብዙ ተግዳሮቶችን የተቋቋምነው በእምነት እንደሆነ ተገነዘብን።
ልንወጣቸው ይገቡን ከነበሩት ተራሮች አንዱ ከባለቤቴ ቤተሰብ ጋር ለጋብቻችን ሁሉንም ዝግጅቶች ልናደርግ በነበረበት ጊዜ ነበር። ካቶሊክ የሆነው የባለቤቴ ቤተሰብ ሴት ልጃቸውን ለማግባት ከፈለግኩኝ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ ስርአዓት መጋባት እንዳለብን የሚገልጽ ቅድመ ሁኔታ አስቀመጡ። ምን ማድረግ እንዳለብን ምንም አናውቅም ነበር።
እኔና ባለቤቴ የቤተመቅደስ ጋብቻ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው በእርሱ እና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት አለን፤ መጾም እና መጸለይ አለብን ከዚያም በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደንብ መጋባትም ቢሆን የሰማይ አባታችን የሚገልጽልንን ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይኖርብናል ተባባልን። ሁላችንም አንድ ላይ መጸለይ እንችል እንደሆነ ለመጠየቅ ከባለቤቴ ቤተሰብ ጋር ለመገናኘት ወሰንን። የሰማይ አባታችን በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ደንብ መጋባት እንዳለብን ከገለጸልን ያንኑ ማድረግ ነበረብን፤ ሆኖም እግዚአብሔር በቤተመቅደስ መጋባት እንዳለብን ከገለጸልን የባለቤቴ ቤተሰብ ምላሹ እንዲቀበሉ እንጋብዛለን። አላማው፦ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መቀበል ነው።
ከጾምን እና ከጸለይን በኋላ የሰማይ አባታችን በቤተመቅደስ መጋባት እንዳለብን ገለጸልን። በጣም የተገረምነው የሚስቴ ቤተሰቦች ከዚያ በኋላ አላስቸገሩንም።
ከተጋባን ሶስት ዓመት ሆነን እንዲሁም በሚቀጥለው ወር ወደ ቤተመቅደስ ለመሄድ አስበናል።
ከጥቂት ወራት በፊት የባለቤቴ እናት በጸሎቱ ወቅት “አስማት አድርገንባቸው እንደነበር” ለባለቤቴ ነገረቻት። ምን እንደሆነ አልገባቸውም ነበር። ባለቤቴም በትህትና ልቧን የነካው የእግዚአብሔር መንፈስ እንደነበረ ገለጸች።
በእግዚአብሔር ስንታመን አናዝንም። ነብዩ ረስል ኤም. ኔልሰን እንዳሉት “ጌታ የእርሱን ፍጹም ሃይል ለመቀበል ፍጹም እምነት አይጠብቅብንም፤ ሆኖም እንድናምን ይፈልጋል”።2