“ኢሳይያስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሩአል፣” ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ መስከረም 2022 (እ.አ.አ)
“ኢሳይያስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሯል”
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ መስከረም 2022 (እ.አ.አ)
ኢሳይያስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሯል
ኢሳይያስ ነቢይ ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት ይኖር ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ እንደሚመጣ ያውቅ ነበር።
ኢሳይያስ ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር ልጅ እንደሚወለድ ተናገረ። ኢየሱስ ሌሎችን ይረዳል እናም ይፈውሳል።
ኢሳይያስ ደግሞም ኢየሱስ ወደምድር እንደሚመጣ ተናገረ። እርሱ የሰላም ልዑል ተብሎ ይጠራል። እኛን በጣም ስለሚወደን ህይወቱን ለእኛ አሳልፎ ይሰጣል።
ኢሳይያስ ያስተማራቸው ነገሮች ደረሱ። ከብዙ አመታት በኋላ፣ ኢየሱስ ወደምድር መጣ። መንገዱን አሳየን። ሞተ እና እንደገናም ኖረ። ዛሬም ህያው ነው!
ስለኢየሱስ ክርስቶስ ለመማር እችላለሁ። እርሱ ለእኔ ምን እንዳደረገ ሳስታውስ፣ ሰላም እና ተስፋ ሊሰማኝ ይችላል።
© 2022 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, January 2022 ትርጉም። Amharic። 18299 506