“ስለኢየሱስ ክርስቶስ መማር እና የእርሱን ሀይል መጠቀም፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ መስከረም 2022 (እ.አ.አ)
ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ መስከረም 2022 (እ.አ.አ)
ስለኢየሱስ ክርስቶስ መማር እና የእርሱን ሀይል መጠቀም
ከየሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ንግግር።
የጌታችንና የመምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ወደ ህይወታችን እንዴት መሳብ እንደምንችል ላካፍላችሁ እወዳለሁ።
ስለ እርሱ በመማር እንጀምራለን።1 “[እኛ] በድንቁርነት [ለመዳን አንችልም]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 131፥6)። የአዳኝን ትምህርት እና ለእኛ ያደረገውን በተረዳን መጠን፣ ለህይወታችን የምንፈልገውን ኃይል እንደሚሰጥ የበለጠ እናውቃለን።
እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ ለሁሉም ትንሳኤን እና ለኃጢአታቸው ንስሀ ለሚገቡት እና አስፈላጊ የሆኑ ስርዓቶችን እና ቃል ኪዳኖችን ለሚቀበሉት እና ለጠበቁት የዘላለም ህይወትን እውን ያደረገበትን ተልዕኮ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እንጠቅሳለን።
በአብ ታላቅ የዘለአለም እቅድ ስር፣ አዳኝ ነው መከራን የተቀበለው። የሞትን እስር የሰበረውም አዳኝ ነው። ለኃጢያቶቻችን እና ለበደላችን ዋጋ የከፈለው እና በንስሐ ቅድመ ሁኔታ እንዚህን የሰረየውም አዳኝ ነው። ከሥጋዊ እና ከመንፈሳዊ ሞት የሚያድነን አዳኝ ነው።
እንደ የኃጢያት ክፍያ እና ትንሳኤ ያሉ ቅዱሳት ቃላት በዚህ ህይወት በተስፋ እንድንኖር እና በሚመጣው አለም የዘለአለም ህይወት እንድናገኝ ዘንድ በአብ እቅድ መሰረት አዳኝ ያደረገውን ይገልፃሉ።
© 2022 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Translation of Monthly For the Strength of Youth Message, September 2022 ትርጉም። Amharic። 18316 506