2022 (እ.አ.አ)
ሚስዮናውያን ሌሶቶ ደረሱ
መስከረም 2022 (እ.አ.አ)


ወሩ በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ

ሚስዮናውያን ሌሶቶ ደረሱ

በመስከረም 18፣ 1989 (እ.አ.አ) በዚች ትንሽ ተራራማ አገር ውስጥ ወንጌሉን ለማስተማር የተመደቡት የመጀመሪያዎቹ ወጣት ሚስዮናውያን ማርክ ሞደርስትዝኪ እና ብራድሊ ሶንደርሰን ወደ ሌሶቶ ገቡ። ሶስት አባል ቤተሰቦች መምጫቸውን በጉጉት እየተጠባበቁ ነበር፦ የማሴይ ቤተሰብ፣ የስኮት ቤተሰብ እና የዳፌንዶልስ ቤተሰብ። እነዚህ ሶስት ቤተሰቦች ወንድም ማሴይ እንደ ቡድኑ መሪ ሆኖ ቡድን መሠረቱ። ሁሉም ከአዲሶቹ ሽማግሌዎች ጋር የሚስዮናዊ ስራ ለመሥራት ጓግተው ነበር። በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት መጨረሻ ላይ ሚስዮናውያኑ የሚያስተምሯቸው 18 ቤተሰቦች ነበሯቸው።

ሽማግሌ ሳውንደርሰን በመዝገቡ ላይ “አካባቢው ባለው ታላቅ አቅም ተደምሜያለው፡ እርሻው በጣም ነጥቷል።” ብሎ ዘግቧል። በመጀመሪያው ወር ባደረጉት የሚማር ሰው ፍለጋ አራት ጊዜ ብቻ ነው እምቢ የተባሉት።

ሽማግሌዎቹ ሲመጡ ካገኟቸው ቤተሰቦች ውስጥ የአንዱ እናት የሆነችው እህት ስኮት እቤቷ እንዲካሄድ ለፈለገችው የመጀመርያ ጥምቀት በጣም ጓግታ ነበር። ነገር ግን የስኮት ቤተሰብ ገንዳ አልነበራቸውም ነበር፤ ስለዚህ ወንድም ስኮት ከርብራብ የተሰራ የግድግዳ ገንዳ ገዛ። ቀጣዩ ችግር ገንዳውን ለማስቀመጥ ግቢያቸው ውስጥ ትልቅ የሆነ ደልዳላ ቦታ አልነበረም። ያ ጉጉታቸውን አልቀነሰውም። ከሚጠመቁት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዎች አንዱ በሆነው ወንድም ላውረንስ ቫን ቶንደር እርዳታ ገንዳውን ለማስቀመጥ የስኮትስን ጓሮ ቆፈሩ።

አባላቶች እና ሚስዮናውያን ላደረጓቸው ብዙ ጥረቶች ምስጋና ይገባቸውና አሁን ላይ በሌሶቶ ውስጥ ከ1,300 በላይ አባላት አሉ።

አትም