2022 (እ.አ.አ)
የአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ ለሽማግሌ ጆሴፍ ሲታቲ እና እህት ግላደስ ሲታቲ ስንብት አቀረበ
መስከረም 2022 (እ.አ.አ)


የአዘጋጁ ማስታወሻ

የአፍሪካ ማዕከላዊ አካባቢ ለሽማግሌ ጆሴፍ ሲታቲ እና እህት ግላደስ ሲታቲ ስንብት አቀረበ

የአፍሪካ ማዕከላዊአካባቢ ለሽማግሌ ጆሴፍ ደብሊዉ. ሲታቲ እና እህት ግላደስ ሲታቲ በአካባቢው ለሰጡት አገልግሎት ልባዊ ምስጋና ያቀርባል። ሽማግሌ ሲታቲ ከነሀሴ 2020 እስከ ነሀሴ 2022(እ.አ.አ) በባለቤቱ ግላዴስ በመደገፍ የአፍሪካማእከላዊ አካባቢ ፕሬዝዳንትበመሆን አገልግሏል።

ሽማግሌ ሲታቲ በ2009 (እ.አ.አ)የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሰባዎችአጠቃላይባለስልጣን በመሆንተሹሞ ነበር እናም ያለፉትን 13 አመታት ፤ የአፍሪካምእራብ አካባቢ አመራሮች አማካሪ፣ በክህነት እና ቤተሰብ ክፍል ውስጥ እንደ ረዳት ዋና አስተዳዳሪ፣ በሚስዮናዊ ክፍል ውስጥ ረዳት ዋና አስተዳዳሪ፣ የደቡብ ምስራቅ አካባቢ የመጀመሪያ አማካሪን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በታማኝነት በማገልገል አሳልፏል።

አሁን ከአጠቃላይ ባለስልጣንነት በክብር ወርዷል እናም እንደ ኤሜሪተስ ሰባ ይታወቃል። በዚህ በአዲሱ የህይወታቸው ክፍል ሲሄዱ የሲታቲ ቤተሰብ ለአመራራቸው እና በነጻ ለሰጡት አገልግሎታቸው በጣም እንዲባረኩ እንጸልያለን።

አትም