2022 (እ.አ.አ)
ቡራኬያችሁን መቀበል
መስከረም 2022 (እ.አ.አ)


የቃልኪዳን መንገዴ

ቡራኬያችሁን መቀበል

ቡራኬ ቢያንስ 18 አመት ለሆናቸው እና ለተዘጋጁ እንዲሁም ብቁና ዝግጁ ለሆኑ የቤተክርስቲያኗ አባላት ሁሉ የሚሰጥ የተቀደሰ እድል ነው።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስያን አባል መሆን ልዩ በረከት ነው። በተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አማካኝነት የዘላለማዊው ወንጌል ሙላት አለን። ለመዳናችን የሚያስፈልጉ “ግልጽና ውድ እውነት”1 የሆኑ ነገሮችን መማር እንችላለን። በቅዱሳን መጻህፍት “ሰው በድንቁርና ሊድን ዘንድ አይችልም” የሚለውን እንማራለን (ት እና ቃ 131፡6)። አዳኛችን ዘላለማዊ ህይወት ማለት ብቸኛውን እውነተኛውን እግዚአብሄርን—የሰማይ አባታችንን እና እራሱን—ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥቷል። አዳኛችንንና የሰማይ አባታችንን የማወቂያው እርግጠኛ መንገድ በቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ በምንቀበለው ቡራኬያችን አማካኝነት ነው።

በቃልኪዳኔ መንገድ ፕሮግራም ውስጥ የሚከተለውን እናነባለን፦ “የቤተመቅደስ ቡራኬ ከእግዚአብሄር ለእያንዳንዳችን የሚሰጥ የተቀደሱ በረከቶች ስጦታ ነው። ቡራኬው ሊሰጥ የሚችለው በሱ መንገድና በተቀደሰ ቤተመቅደሱ ውስጥ ብቻ ነው። በቤተመቅደስ ቡራኬ አማካኝነት ከምትቀበሏቸው አንዳንድ ስጦታዎች መካከል እነዚህ ይካተታሉ፡

  • “በጌታ አላማዎች እና ትምህርቶች ላይ የበለጠ እውቀት።

  • “እግዚአብሄር እንድናደርግ የሚፈልገውን ሁሉ የማድረግ ሀይል።

  • “ጌታን፣ ቤተሰቦቻችንን እና ሌሎችን ስናገለግል መለኮታዊ ምሪት እና ጥበቃ።

  • “የበለጠ ተስፋ፣ ማጽናኛ እና ሰላም።”

  • “ለአሁን እና ለዘላለም ቃል የተገቡ በረከቶች።”

ቡራኬ ቢያንስ 18 አመት ለሆናቸው እንዲሁም ለሱ ለተዘጋጁ ብቁና ዝግጁ ለሆኑ የቤተክርስቲያኗ አባላት ሁሉ የሚሰጥ የተቀደሰ እድል ነው። ብቁ መሆን አስፈላጊ ነው፣ ዝግጁ መሆን አስፈላጊ ነው፣ መዘጋጀት አስፈላጊ ነው። ለዚህ የተቀደሰ ስርዓት ብቁ ፣ዝግጁ ለመሆን፣ እና ለመዘጋጀት ያደረኩትን አስታውሳለሁ፦ ትእዛዛቱን ለመጠበቅ መጣር፣ በየቀኑ ንስሀ መግባት፣ በየቀኑ ቅዱሳን መጻህፍትን ማጥናት፣ በቤዛው ላይ ሙሉ ለሙሉ መተማመን፣ የቤተመቅደስ መዘጋጃ ክፍልን መሳተፍ፣ ስለቤተመቅደስ የተሰጡ ንግግሮችን ማጥናት።

ሚስዮን ለማገልገል ከመሄዴ ከጥቂት ወራት በፊት ቤተሰቤ እና እኔ በተመሳሳይ ቀን ቤተመቅደስ ውስጥ የመታተም እና ቡራኬያችንን የመቀበል ድርብ በረከትን አግኝተን ነበር። ያ ትውስታ ለዘላለም ለልቤ ውድ ሆኖ ይቆያል። በስተመጨረሻ በጌታ እንደተመረጥኩ አውቄ የቤተመቅደስ መግቢያ ካርዴን ይዤ ቤተመቅደስ ስገባ በነፍሴ ውስጥ የጸሀይ ብርሀን ነበር። ፕሬዚዳንት ረስል ኤም. ኔልሰን “እያንዳንዱ ድርጊት፣ እያንዳንዱ ትምህርት፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የምናደርገው ነገር ሁሉ፣ ወደ ጌታ እና ወደ ቅዱስ ቤቱ ይጠቁማሉ። ወንጌሉን የማወጅ ጥረታችን ቅዱሳኑን ፍጹም ያደርጋል፣ ሙታንን ያድናል፣ ሁሉም ወደ ቤተመቅደስ ያመራሉ። እያንዳንዱ ቅዱስ ቤተመቅደስ በቤተክርስቲያኗ የአባልነታችን ምልክት፣ ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ የምናሳይበት የእምነታችን ምልክት፣ ለእኛና ለቤተሰባችን ወደዘላለማዊ ክብር የሚደረግ አንድ የተቀደሰ የወደፊት እርምጃ ነው።”2

ቡራኬያችሁን ለመቀበል ስትዘጋጁ ሀሴትን ትቀበላላችሁ።

ማስታወሻዎች

  1. “What Plain and Precious Truths were Restored by the Book of Mormon?”, ሊያሆና, Jan. 2020, 41 ይመልከቱ።

  2. ራስል ኤም.ኔልሰን, “Personal Preparation for Temple Blessings”, Ensign, May 2001, 32.