የአካባቢ ዜናዎች
ብራዛቪል፦ ‘እምነታችን ፍጹም አልነበረም፤ ሆኖም ግን ጌታ አስታወሰን’
በኮንጎ ሪፐብሊክ የሚገኙ ቅዱሳን በሃገራቸው ቤተመቅደስ የመገንባቱን አስደሳች ዜና ሲሰሙ ስሜታቸውን ገልጸዋል።
ሚያዝያ3 ቀን 2022(አ.አ.አ) በአለም ዙሪያ የሚገኙ ታማኝ ቅዱሳን አጠቃላይ ጉባኤን ለመመልከት በየቤታቸው ተሰብስበው ነበር።በኮንጎ ሪፐብሊክ የብራዛቪል ካስማ ፕሬዚዳንት ቤሌቪ ጋዩኤሌ እና ቤተሰባቸው ሂደቱን በቀጥታ ስርጭት በጥልቅ አክብሮት እየተከታተሉ እያሉ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን በብራዛቪል ቤተመቅደስ ይገነባል! ብለው ባስተዋወቁ ጊዜ ድንኳናቸውን ወደ አጠቃላይ ጉባኤው አዙረው ከተከታተሉት’ከሚሊዮኖች መካከል ነበሩ።
ፕሬዚዳንት ቤሌቪ ጋዩኤሌ ስለዚህ የተቀደሰ ተሞክሮ ሲናገሩ፣ “በዚህኛው በቅርቡ የአጠቃላይ ጉባኤ ላይ ቤተመቅደስ እንደሚገነባ ይገለጻል ብለን አልጠበቅንም ነበር።ሆኖም፣ በብራዛቪል እና በፖይን-ኑዋር (በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁለት ከተሞች ናቸው)፤ ዙሪያ የሚገኙ ቅዱሳን የነቢዩን የመደምደሚያ ንግግር ተስፋን ባዘለ መንገድ ተከታተሉ። ነቢዩ ሳይታሰብ በብራዛቪል ቤተመቅደስ እንደሚገነባ ሲያበስሩ ታላቅ ውጤት ነበረው።ለምሳሌ፣ ባለቤቴ በደስታ አልቅሳለች፣ በየቦታው ታላላቅ የደስታ አከባበሮች፣ የማያቋርጡ የቪዲዮ እና የስልክ ጥሪዎች ነበሩ፤ እንዲሁም በዚያን ምሽት መተኛት አልቻልንም ነበር! ቤተሰቤ እና እኔ በትህትና ተንበረከክንና የምስጋና ጸሎት አደረስን”፣ ብለዋል።
በብራዛቪል ካስማ የሞሳ አጥቢያ አባል የሆነችው እህት ኤስቴል ቪያን በምስጋና እንደተሞላች ተናግራለች። “ዛሬ የሰማዩ አባታችን በህይወት ባለው ነቢዩ አማካኝነት ቤቱ በእኔ አገር የመገንባቱን አስደናቂ ዜና በመናገሩ በጣም አመስጋኝ ነኝ” ብላለች። “በእርግጥ ጌታ እኛን የብራዛቪል ቅዱሳንን እንደሚያውቀን እና እንደሚያስታውሰን ተሰምቶኛል። ልቤ በደስታ ተሞልቷል።” የቅዱሳን ልቦች በአንድነት እና በፍቅር እንደተያያዙ በማረጋገጥ ከፖንትሬኑዋትር ካስማ፣ ከምፓካ አጥቢያ የመጣችው እህት ቢቢቻ ኪቶምቦ እና በኤሮፖር ካስማ ውስጥ ከሚገኘው የኤሮፖር አጥቢያ የመጣው ወንድም ቫን ሳምባላ ተመሳሳይ ስሜቶችን አጋርተዋል።
ፕሬዚዳንት ቤሌቪ ጋዩኤሌ እንዲህ ይላሉ “ዛሬ በብራዛቪል ውስጥ በሚገኙ አባላት ፊት ላይ አንድ ዓይነት የእርካታ ደስታ አለ።ለቤተመቅደስ ስርዓቶች ጥልቅ ሰላም እና የላቀ ቁርጠኝነት እንዳለ በእውነት ሊሰማችሁ ይችላል። አንዳንድ ሰዎችአሁንም ማመን አልቻሉም፤ ደስታው ታላቅ ነው፤ እንዲሁም ለጌታ መልካምነት ያለው ምስጋናም ጥልቅ ነው።”
በአሁኑ ጊዜ በብራዛቪል ለሚገኙ ቅዱሳን በጣም ቅርብ የሚባለው ቤተመቅደስ የሚገኘው በዲአርሲ፣ኪንሻሳ ውስጥ ነው። እዚያ መሄድ ሁልጊዜ ቀላል አልነበረም።
ፕሬዚዳንት ቤልቪ ጋዩኤሌ “ኪንሻሳ ወደሚገኘው ቤተመቅደስ ለመሄድ ትልቅ የጉዞ ዝግጅት አደረግን፤ ይህም ማለት አስቸጋሪ የሆነውን ወንዝ ለመሻገር ያለውን ፈተና ከቤተሰቦቻችን ጋር በመሆን በድፍረት መወጣት ነበረብን ማለት ነበር” ብለዋል። “እንዲሁም አገራችን በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ውስጥ ባለችበት ወቅት ነበር። ቤተሰቦች በድህነት ውስጥ የነበሩ ቢሆንም አባላት በእነዚህ ጉዞዎች ላይ ወንዙን ለመሻገር ትኬት በመቁረጥ፣ ለምግብ እና ለማረፊያ በመክፈል ትልቅ መስዋዕትነት ከፍለዋል። ወደ ቤተመቅደስ የምንሄደው በጣም ብዙ ስለነበርን አብዛኛውን ጊዜ በኪንሻሳው ቤተመቅደስ ውስጥ ቦታ አናገኝም ነበር። አንዳንድ ወንድሞች እና እህቶች ተራቸው እስኪደርስ ከቤተመቅደስ ውጪ መቆየት ነበረባቸው። እነዚህ ጉዞዎች በቤተመቅደስ ስርዓቶች ለመሳተፍ የነበሩ የእምነት እና የጽናት ፈተናዎች ጊዜያት ነበሩ። በመጨረሻም እነዚህ ጉዞዎች የቤተመቅደስን መንፈስ ወደ ቤተክርስቲያኗ አባላት ልብ ለማምጣት አስችሎናል” ብለዋል።
እህት ቢቢቻኪቶምቦ እንዲህ ስትል አክላለች፣ “በቤተመቅደስ ላይ ትኩረታቸውን እንዲያደርጉ በማበረታታት መሪዎች በተለይ ለወጣቶች እና ላላገቡ ወጣት አዋቂዎች ታላቅ የድጋፍ እና የመበረታቻ ምንጮች ነበሩ። ቫን ሳምባላ ይህ አብዛኛውን ጊዜ እንዲጸልዩ፣ እንዲጾሙ እና ትዕዛዛቱን በመጠበቅ እንዲጸኑ እንዳስቻላቸው ሃሳቡን ያጋራል።”
እህት ኤስቴል ቪያኒ የቤተመቅደስ በረከቶችን ለማግኘት እያንዳንዱ ቅዱሳን አሁን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ቅዱሳኑን ታስታውሳለች። “የግል ብቁነት የቤተመቅደስ በረከቶችን ለማግኘት አስፈላጊ ሁኔታ ነው”1 በማለት የፕሬዚዳንት ሪቻርድ ጂ. ስኮትን ጥቅስ አጋርታለች።ምስክርነቷ ቀላል ነው፦ ቤተመቅደስ የእግዚአብሔር ቤት ነው፤ እምነትን እና መንፈሳዊነትን ለማጠናከር ቁልፍ ነው።
ፕሬዚዳንት ቤሌቪ ጋዩኤሌ እንዲህ ሲሉ ይመክራሉ፦“ዛሬ እምነታችን ፍጹም እንዳልነበረ፣ጥረቶቻችን እና መስዋዕትነቶቻችን ትልቅ እንዳልነበሩ እናውቃለን ሆኖም ግን ጌታ ስላስታወሰን አመስጋኞች ነን።
“ቤተመቅደሱ ይህንን አገር እና ህዝቡን እንዲሁም አባላትን እና አባላት ያልሆኑትን ሁለቱንም ይባርካል። ይህ ቤተመቅደስ ለእኛ እና ለልጆቻችን በረከት ይሆናል።ቤተክርስቲያኗ ከጨለማ ትወጣለች እናም የእግዚአብሔርንም መንፈስ በስፋት ወደሀገራችን ያመጣል።”