2022 (እ.አ.አ)
ንቁ ተሳታፊ ያልሆኑትን አድኑ
መስከረም 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ መሪ መልዕክት

ንቁ ተሳታፊ ያልሆኑትን አድኑ

በችግር ውስጥ ያሉትን የመርዳት ሃላፊነቶቻችንን ስንወጣ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች እና መከራዎች መቋቋም እንችላለን።

ላለፉት 13 ዓመታት የቤተክርስቲያኗ አባል እንደመሆኔ ስለደህንነታቸው ለመጠየቅ እና ኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ፍቅር ለእነርሱ ለማካፈል ንቁ ተሳታፊ ያልሆኑ አባላትን መጎብኘት እወዳለሁ።አንድ ቅዳሜ የእኔ ማጽናኛ ለሚያስፈልጋቸው እንድደርስ እንዲረዳኝ እና ክርስቶስ ለእነርሱ ያለውን ፍቅር አውቅ ዘንድ እንዲረዳኝ ተንበርክኬ ወደሰማይ አባት መጸለዬን አስታውሳለሁ። ጸሎቴን በጨረስኩኝ ጊዜም ንቁ ተሳታፊ ካልሆኑት እህቶች መካከል አንዷን እንድጎበኝ የመንፈስ መነሳሳት ተሰማኝ። ለረዥም ጊዜያት ቤተክርስቲያን መጥታ አታውቅም ነበር። በደወልኩላት ጊዜም ጽኑ ህመም ተገኝቶባት ሆስፒታል እንዳለች ነገረችኝ። ምንም እንኳን አብሮኝ የሚሄድ ረዳት ባላገኝም(አይነስውር ነኝ) በራሴ ለመሄድ እና ይህችን እህት ለመጎብኘት ወሰንኩኝ።

ባየችኝም ጊዜ በደስታ ተሞላችና “አንቺ የመጀመሪያ ጠያቂዬ ነሽ” አለችኝ። የአልዓዛርን ታሪክ እንዲሁም በእምነቱ ምክንያት ክርስቶስ እንዴት ከሞት እንዳስነሳው አካፈልኳት (ዮሃንስ 11፥1–44 ይመልከቱ)።

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ይህች እህት ወደቤተክርስቲያን መጣችና መጀመሪያ ስለጠየቀቻት የቤተክርስቲያን አባል ምስክርነቷን ሰጠች።

ምስክርነቷን እንዴት እንዳጠናከረላት እና የሰማይ አባት ለልጆቹ ያለውን የደስታ እቅድ እንድትገነዘብ ፤ በህይወት ውስጥ አዲስ ተስፋ እንደሰጣት አካፍላለች።

ንቁ ተሳታፊ ያልሆኑ አባላትን በምንጎበኝበት ጊዜ የኢየሱስ ክርስቶስን የጠፋውን በግ የመፈለግ ምሳሌ እየተከተልን ነው (ማቴዎስ 18፥12–14 ይመልከቱ)። ይህንን በምናደርግበት ጊዜ ሌሎችን ብቻ እየረዳን አይደለም የራሳችንም ምስክርነት ይጠናከራል።

በቤተክርስቲያን እንቅስቃሴዎች አነስተኛ ተሳትፎ ያላቸውን ልጆቹን ማገልገል ከሰማያዊ አባታችን ትዕዛዛት አንዱ ነው።ሃላፊነቶቻችንን ስንወጣ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች እና መከራዎች መወጣት እንችላለን።“ነገር ግን የእግዚያብሄርን ትዕዛዛት ከጠበቅህ፣ እናም በእነዚህ ቅዱስ ነገሮች እግዚያብሄር ባዘዘህ መሰረት ከሰራህ (በምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ወደጌታ አቤት እንድትል ይገባልና) እነሆ ከአንተ ሊወስድብህ የሚችል ምንም ኃይል፣ የምድርም ሆነ የሲኦል፣ አይኖርም፣ ምክንያቱም እግዚአብሄር ቃሉን ሁሉ ይፈጽም ዘንድ ኃያል ነውና“የሚሉትን በአልማ 37፥16–17 ውስጥ የተጠቀሱትን ቃል የተገቡ በረከቶች እናገኛለን።

አትም