2022 (እ.አ.አ)
‘ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ’
መስከረም 2022 (እ.አ.አ)


የአካባቢ አመራር መልእክት

‘ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ’

ዛሬ እራሳችሁን በእያሪኮ መንገድ ላይ አግብታችሁ ቢሆን ኖሮ ልምዳችሁ ምን ይሆን ነበር?

አዳኛችን እና ቤዛችን እየሱስ ክርስቶስ “የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአልና…

“እንደዚሁ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ ፈቃድ አይደለም (ማቲዎስ 18፥11፣ 14) ብሎ ሲያውጅ የእግዚአብሄርን ልጆች ለማዳን ያለውን ተልእኮ ተረድቶ ነበር።

ለአባቱና ለአባታችን ባደረገው የአማላጅነት ጸሎት የእያንዳንዱን ነፍስ ዋጋ እንድንረዳ ለመርዳት እየሱስ ክርስቶስ እንዲህ አለ “ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን በስምህ እኔ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም መጽሐፉም እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም” (ዮሀንስ 17፥12)። በዘመናዊው ራእይ “አባቴ ከሰጠኝ ማንኛቸውም አይጠፋም በማለት አዟል” (ትእናቃ 50፥42)።

እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙርነታችን፣ ለመዳን እና በየቀኑ እርዳታ ለማግኘት የሚጣሩትን የብዙ ወንድሞቻችንን፣ እህቶቻችንን፣ ወጣቶችን፣ እና ልጆችን ድምጽ ለመስማት የግል አቅማችንን በመጨመር የሱን ፍቅር እና ርህራሄ መከተላችን በጣም አስፈላጊ ነው።

በአዳኛችን ጊዜ “ቀይ መንገድ” ወይም “የደም መንገድ” ተብሎ ይጠራ በነበረው መንገድ ላይ ጉዞ ልውሰዳችሁ። ከፍታው 3400 ጫማ ይወርዳል(ከአንድ ኪሎሜትር በላይ) ሲሆን ዘራፊዎችና ሽፍታዎች ነበሩበት፡፡ይሄ መንገድ ከእየሩሳሌም ወደ እያሪኮ የሚወርደው ነበር። “ባልንጀራዬስ ማን ነው?” ለሚለው ለጠበቃው ጥያቄ ምላሽ (ሉቃስ 10፥29) አዳኙ የመልካሙን ሳምራዊ ምሳሌ ሰጠ (ሉቃስ 10፥30–37 ይመልከቱ)። ክርስቶስ በነበረበት ጊዜ በአይሁዶችና በሳምራዊያን መሀከል ከፍ ያለ ጥላቻ ነበር። በማንኛውም ሁኔታዎች ውስጥ እነዚህ ሁለት ቡድኖች የእርስ በርስ ግንኙነትን ይሸሹ ነበር።

በተጻፈው የሙሴ ህግ ውስጥ ካህናት እና ሌዋውያን እግዚአብሄርን እና ጎረቤቶቻቸውን በቤተመቅደስ እንዲሁም እንደአስተማሪ እና የእግዚአብሄር ህግ አርአያ ሆነው እንዲገለግሉ ተመድበው ነበር። እነዚህ የክህነት ተሸካሚዎች “ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ” (ዘሌዋውያን 19፥18)።

የሚለውን ትእዛዝ በደንብ ያውቁት ነበር። እንደውም ሌዋዊያን በተለይ ተጓዦችን በኢኮኖሚያዊ እና በሌሎች መንገዶች እንዲረዱ ታዘው ነበር (ዘሌዋውያን 25፡35–36)። በአዳኙ ምሳሌ ውስጥ ግን ካህኑ እና ሌዋዊው እነዚህን ትእዛዛት ተላልፈው ነበር ፤ ሁለቱም የቆሰለውን ሰው አዩት ግን “ገለል (ብለው አለፉ)” (ሉቃስ 10፡31–32)። ሳምራዊው ግን በፍቅርና በርህራሄ ተሞልቶ ነበር። ራሳችንን በዚህ የመልካም ሳምራዊ ምሳሌ ውስጥ አስቀምጠን ቀጣዮቹን ጥያቄዎች እራሳችንን እንጠይቅ እና እርዳታችንን ለሚፈልጉ እንዴት ምላሽ እንደምንሰጥ እናስብ።

ዛሬ እራሳችሁን በእያሪኮ መንገድ ላይ ብታገኙ ልምዳችሁ ምን ይሆናል? በዘራፊዎች መሀል የወደቀን እና እርዳታችሁን የሚያስፈልገውን ሰው ለማየት ያቅታችኋል? የተጎዳውን አይቶ እና ልመናውን ሰምቶ ገለል ብሎ የሚያልፍ ሰው ትሆናላችሁ? ወይሥ የሚያይ፣ የሚያዳምጥ፣ የሚቆም እና የሚረዳ ሰው ትሆናላችሁ?

ኔፊ በኋለኛው ቀናት የእግዚአብሄርን በግ ቤተክርስቲያን በራእይ ተመለከተ። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት በጽድቅ እና በሀይል ይታጠቃሉ ብሏል። ለመውደድ፣ ለመቀየር፣ ለመታዘዝ፣ የኛ እርዳታና ማዳን የሚያስፈልጋቸውን ለማገልገል፣ በሳምራዊው ምሳሌ ውስጥ እንደተገለጸው የክርስቶስን ንጹህ የክርስቲያን ፍቅር ምሳሌ የመከተል ሀይል።

ፕሬዚዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዲህ ብለዋል፣ “ኢየሱስ ’ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ’ የሚለውን የመፈክር ቃላችንን ሰጥቶናል። ይህን አዋጅ ስንከተል ለእይታችን አቻ የማይገኝለት እና መቼም የተሻለ የማይገኝለት ሰፊ የሀሴት እይታ ይከፈታል። …

“በዛ መልካም ሳምራዊ መንገድ ስንራመድ ወደፍጹምነት የሚያመራውን መንገድ እንራመዳለን።”1

ሳምራዊው ለመርዳት ፍላጎት ስለነበረው ርህራሄ ነበረው ለቆሰለው ሰው አዘኔታ ተሰምቶታልና፡፡በጌታ መንፈስ በተነካ በማንኛውም ሰው ልብ ውስጥ ይህ የደግነት ፍቅር አለ። ይህ የሰውን ችግር እንደራስ የማየት ስሜት አንዳችን ላንዳችን ሊሰማን ይገባል። በእርግጥአዳኙ የቃልኪዳኑ እስራኤላዊያን እርስበርስ በሚያሳዩት ፍቅር ሊታወቁ እና ሊለዩ ይገባል ብሏል (ዮሀንስ 13፥35)።

ሳምራዊው “ወደሱ ሄደ።” እርዳታ የሚያስፈልገው ሰው እስኪቀርበው አልጠበቀም ነገር ግን ያለውን ችግር ተመለከተ እናም ሳይጠየቅ ለመርዳት ወደፊት ሄደ።

ሳምራዊው “ዘይትና የወይን ጠጅ በቁስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው። “የህክምና እርዳታ አደረገለት እና የሚሰቃየውን ሰው ጥማት ቆረጠለት። ይህ ፈጣን እርዳታ የሰውየውን ህይወት አትርፏል።

ሳምራዊው በራሱ አህያ ላይ አስቀመጠው—ማለትም መጓጓዣ አዘጋጀለት እና የእረፍት እና የእንክብካቤ ቦታ ወደሆነው “ወደ እንግዶች ማደሪያ ወሰደው”። የሚያስፈልገውን ቤት በማቅረብ ለመዳን የሚያስፈልገውን ትክክለኛ ሁኔታ አመቻችቷል።

ሳምራዊው “ጠበቀው።” ለመዳን አስጊ ደረጃ ላይ በነበረበት ጊዜ ሳምራዊው የቆሰለውን ሰው የመንከባከቡን ስራ ወደሌሎች ሰዎች አላሳለፈም ነገር ግን ይህን የማዳን አገልግሎት በራሱ ለመስራት ጊዜውን እና ጉልበቱን መስዋዕት ማድረጉን ልብ በሉ።

ሳምራዊው “በማግስቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠ።” የሌላን ሰው ሳይሆን የራሱን ብር ወስዶ እሱ ለማቅረብ ላልቻላቸው አገልግሎቶች ከፈለ።

ሳምራዊው ለኑሮ የሚያስፈልገውን ገቢ ለማግኘት መሄድ ስለነበረበት ለእንግዶች ማደሪያ ጠባቂው “[እንዲጠብቀው]” ነገረው። በዚህ መንገድ ሌሎች—የሰው ሀብቶች—እንዲረዱ እና እንክብካቤውን እንዲቀጥሉ መለመለ።

ሳምራዊው በመቀጠልም “ከዚህ በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሀለው” ሲል ቃል ገባለት። እዚህ ላይ ትልቁ ርህራሄ ይታያል! የሚረዳበትን ገደብ አላስቀመጠም። እንዲሁም ምናልባትም በጣም አስፈላጊ የሆነው እዚያ አስቀምጦት አልረሳውም መደረግ ያለበት ሁሉ መደረጉን ለማረጋገጥ ቁርጠኝነቱን አሳይቷል።

በካስማ አመራር ውስጥ ሳገለግል ከሰባዎቹ ሽማግሌ የሆነው ሽማግሌ ሜርቪን ቢ. አርኖልድ በሚያዝያ 2004 እ.አ.አ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ንቁ ያልሆነ ተሳታፊ የሆነውን እና እሁድ እሁድ ቤተክርስቲያን የማይካፈለውን ፈርናንዶ የሚባል ወጣት ወንድን ስላዳነው ወንድም ማርከስ ታረክ ሲያጋራ፤ ባከፈለው ልምድ ተነክቼ ነበር።

ፈርናንዶ እሁድ ጠዋት ጠዋት ላይ በሚደረጉ በቦርድ ላይ ማእበል የመቅዘፍ ውድድር ላይ ስለሚሳተፍ የቤተክርስቲያን ስብሰባዎችን መሄድ አቆመ። አንድ እሁድ ጠዋት ወንድም ማርከስ ሄዶ በሩን አንኳኳ እና አባል ያልሆነችውን እናቱን ሊያናግረው ይችል እንደሆነ ጠየቃት። ፈርናንዶ እንደተኛ ነገረችው ስለዚህ እሱን ለመቀስቀስ ፍቃድ ጠየቃት። እንዲህ አለው “ፈርናንዶ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ረፍዶብሀል!” ማስተባባዮቹን ባለማዳመጥ ወደ ቤተክርስቲያን ወሰደው።

በቀጣይ እሁድ ተመሳሳይ ነገር ተፈጠረ፣ ስለዚህ በሶስተኛው ቀን እሱን ለመሸሽ በጠዋት ለመውጣት ወሰነ። ፈርናንዶ በሩን ሲከፍት ወንድም ማርከስ መኪናው ላይ ቁጭ ብሎ መጽሀፍ ቅዱስ እያነበበ አገኘው። ሲያየው ጥሩ! በጠዋት ተነስተሀል። ዛሬ ሄደን ሌላ ወጣት ወንድ እናገኛለን!’ አለው። ፈርናንዶ ምርጫ እንዲኖረው ጠየቀ ነገርግን ወንድም ማርከስ ‘ስለሱ በኋላ እናወራለን’ አለው።

ከስምንት እሁዶች በኋላ ፈርናንዶ ሊያስወግደው አልቻለም ስለዚህ አንድ ጓደኛው ቤት ለመተኛት ወሰነ። ፈርናንዶ በነጋታው ጠዋት ሱፍ እና ከረባት አድርጎ ወደሱ እየተራመደ ያለ ወንድ ሲያይ በባህር ዳርቻው ነበር። ወንድም ማርከስ መሆኑን ሲያቅ ወደ ውሀው ውስጥ ሮጠ። በድንገት በትከሻው ላይ የሆነ ሰው እጅ ተሰማው። እሰከደረቱ ውሀ ውስጥ ገብቶ የነበረው ወንድም ማርከስ ነበር! እጁን ያዘውና ‘አርፍደሀል! እንሂድ አለው።’ የምለብሰው ልብስ የለኝም ብሎ ፈርናንዶ ሲከራከር ወንድም ማርከስ ‘መኪናው ውስጥ ነው’” ብሎ መለሰለት።

በዚያን ቀን ከውቂያኖሱ እየተራመዱ ሲወጡ ፈርናንዶ በወንድም ማርከስ ልባዊ ፍቅር እና ለሱ ባለው ሀሳብ ተነክቶ ነበር። ‘የጠፋውንም እፈልጋለሁ የባዘነውንም እመልሳለሁ የተሰበረውንም እጠግናለሁ የደከመውንም አጸናለሁ’ (ህዝቅኤል 34፥16) የሚሉትን የአዳኙን ቃላት በእውነት ተረድቶ ነበር።2

ውድ ወንድሞች እና እህቶች ወደማዳን ስንሄድ ሌሎችን መርዳት እንችል ዘንድ እግዚአብሄር ሃይል፣ ማበረታቻ እና በረከቶች ይሰጠናል።

በችግር ውስጥ ሆነው እርዳታ የሚፈልጉ ሆኖም ወዴት መዞር እንዳለባቸው የማያውቁ ብዙ ስላሉ ለማዳን ለመሄድ እንዳትዘገዩ እጋብዛችኋለው። ለአንድ ሰው መልካም ለማድረግ መቼም አይረፍድም፤ ተስፋ አትቁረጡ። የመጨረሻውን በጭንቅላታችሁ በማድረግ ሌሎችን በማዳን ውስጥ ሀሴትን አግኙ (ት እና ቃ 18፥15–16)። እድሜያችን የቱንም ያህል ቢሆን ለመሄድ እና ለማዳን ሁላችንም ተጋብዘናል።

ፕሬዘዳንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ “እድሜያችን፣ አቅማችን፣ የቤተክርስቲያን ጥሪያችን፣ ወይ ቦታችን፣ ምንም ቢሆን እሱ ተመልሶ እስከሚመጣ በነፍስ የመኸር ስብሰባው ስራ ውስጥ [አዳኙን] ለማገዝ እንደ አንድ ተጠርተናል።” ብሎ አውጇል።3

ሄደን ተመሳሳዩን ለማድረግ የአዳኙን ግብዣ ከልባችን፣ በእውነት እንድንከተል እጸልያለሁ። እየሱስ ክርስቶስ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን እንደሚረዳ እመሰክራለው። ርህራሄ አለው እናም የሀጢአትን መንፈሳዊ ቁስል ይፈውሳል። ከሞት ያድነናል። በቤዛነቱ አማካኝነት እንድን ዘንድ የሚያሰፈልገንን ዋጋ ኢየሱስ ክርስቶስ በግል እንደከፈለልን እመሰክራለው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን, “Your Jericho Road”, ኢንዛይን, መስከረም 1989, 2, 4።

  2. መርቪል ቢ. አርኖልድ, “Strengthen Thy Brethren”, ኢንዛይን, ግንቦት 2004, 46–47።

  3. ኤንሪ ቢ. አይሪንግ, “We Are One”, ሊያሆና, ግንቦት 2013, 62።

አትም