2022 (እ.አ.አ)
በህያው ነቢያት የተመራ
መስከረም 2022 (እ.አ.አ)


“በህያው ነቢያት የተመራ፣” ሊያሆና፣ መስከረም 2022 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ መስከረም 2022 (እ.አ.አ)

በህያው ነቢያት የተመራ

ምስል
የቤተክርቲያኗ መሪዎች በክርስቶች ሀውልት ፊት

ነቢያት በሰማይ አባት ለእርሱ እንዲናገሩ የተጠሩ ሰዎች ናቸው። እነርሱም ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለወንጌሉ ይመሰክራሉ። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን አባላት በጥንት እና በዘመናዊ ነቢያት ያምናሉ።

እግዚአብሔር በነቢያት በኩል ይናገራል።

ነቢያት ከእግዚአብሔር ራዕይን ይቀበላሉ። ነቢያት እኛን ለማስተማር ሲነሳሱ፣ ይህም እግዚአብሔር እራሱ ለእኛ እደሚናገር አይነት ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥13ን ተመልከቱ)። እነርሱ የሚነግሩን እግዚአብሔር እንድናውቀው የሚፈልገንን እንደሆነ ለማመን እንችላለን።

ምስል
ሞርሞን የወርቅ ሰሌዳዎችን ይዞ

ሞርሞን ሰሌዳዎቹን አሳጥሮ ሲጽፍ በቶም ሎቬል

ነቢያት ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምራሉ

ለቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራሉ። እርሱ የእግዚአብሒእር ልጅ እንደሆነም ያስተምሩናል። ስለእርሱ ህይወት፣ ምሳሌ፣ እና የኃጢያት ክፍያ ያስተምሩናል። እንዲሁም እርሱን እንዴት እንደምንከተል እና ትእዝዛዛኡን እንደምናከብርም ያሳዩናል።

የነቢያት ሀላፊነቶች

ነቢያት የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን ያስተምራሉ። ትእዛዛትን ስናከብር የምንቀበላቸውን በረከቶች እና በማናከብርበት ጊዜ የምናገኛቸውን ውጤቶች ይገልጻሉ። አንዳንድ ጊዜም፣ ወደፊት ስለሚፈጸሙት ክንውኖች ሊነግሩን ይነሳሳሉ።

ምስል
ሙሴ ጽላቶችን ይዞ

ሙሴ እና ጽላቶች፣ በጄሪ ሀርስተን

የጥንት ነቢያት

እግዚአብሔር ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ በነቢያት በኩል ሰዎችን አስተምሯል። በብሉይ ኪዳን ዘመናት የነበሩ ነቢያትም አዳምን፣ ኖኅን፣ አብርሐምን፣ ሙሴን፣ ኢሳይያስን፣ እና ሌሎችን ያካታሉ። በመፅሐፈ ሞርሞን ህዝቦች መካከልም ነቢያት ነበሩ። እነዚህ ነቢያትም ሌሒን፣ ሞዛያን፣ አልማን፣ እና ሞሮኒን ያካትታሉ። እነርሱ ምን እንዳስተማሩ ቅዱሳት መጻህፍትን በማንበብ ለመማር እንችላለን።

የዚህ ዘመን ነቢያት

ጆሴፍ ስሚዝ የዚህ ዘመን የመጀመሪያ ነቢይ ነበር። እርሱም የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን በምድር ላይ በዳግም መመለስ። ራስል ኤም.ኔልሰን ዛሬ የቤተክርስቲያኗ ነቢይ እና ፕሬዘደንት ናቸው። የእርሳቸው የቀዳሚ አመራር አማካሪዎች እና አስራ ሁለት ሐዋርያትም ነቢያት፣ ገላጮች፣ እና ባለራዕያት ናቸው።

ምስል
ጥንዶች ጉባኤን በስልክ ሲያዩ

ነቢያትን ማዳመጥ

ነቢይ በአጠቃላይ ጉባኤ እና በሌሎች ጊዜያት ያነጋግረናል። እግዚአብሔር እንድናውቀው የሚፈልገውን እና ዛሬ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት እንደምንከተል ያስተምረናል። የሚያስተምረውን በሊያሆና እና በChurchofJesusChrist.org ውስጥ ለማግኘት እንችላለን።

ነብዩን የመከተል በረከት

የነቢዩን ትምህርቶች ከተከተልን እንባረካለን። ነቢዩን ንስንከተል፣ እግዚአብሔር እንድንሠራ የሚፈልገውን እየሠራን መሆናችንን ማወቅ እንችላለን። በህይወታችን ሰላም ይሰማናል እናም ወደ ኢየሱስ ክርስቶች ቅርብ ለመሆን እንችላለን።

አትም