2022 (እ.አ.አ)
ችግር ላይ ያለውን እና እርዳታ የሚያስፈልገውን መርዳት—ምንባቦች
ህዳር 2022 (እ.አ.አ)


ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)

ችግር ላይ ያለውን እና እርዳታ የሚያስፈልገውን መርዳት

ምንባቦች

የኦክስ ፖስተር ጥቅስ

ለወገኖቻችን ብዙ ደኅንነት እና ሰብአዊ አገልግሎት ስለመስጠት በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እና በእኛ አባሎቿ በኩል በትምህርት ይቀርባልም ተግባራዊ ይደረጋልም። ለምሳሌ፣ በየወሩ መጀመሪያ ላይ እንጾማለን እና ያልበላናቸውን የምግብ ዋጋ ያህል በራሳችን ስብሰባዎች መሃከል እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው በምፅዋት እንሰጣለን። ቤተክርስቲያኗም በአለም ዙሪያ ላሉት የሰብአዊ እና ሌሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ ትሰጣለች።

ቤተክርስቲያናችን በቀጥታ ብትሰራም፣ በዓለም ዙሪያ ለእግዚአብሔር ልጆች የሚሰጠው አብዛኛው ሰብዓዊ አገልግሎት የሚከናወነው ከቤተክርስቲያናችን ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት በሌላቸው ሰዎችና ድርጅቶች ነው። …

የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለማገልገል ቆራጥ ናት እናም በዚያ ጥረት ከሌሎች ጋር ለመስራት ቆራጥ ናት።

በአሁን ጊዜ ያሉ ራዕዮች፣ አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ “ወደ አለም ለሚመጣው ሰው ሁሉ የሚያበራ ብርሃነ ነው” [ትምህርት እና ቃልኪዳን 93:2 ]። በዚህ፣ ሁሉም የአምላክ ልጆች እሱን እና እርስ በራስ ባላቸው እውቀት እና አቅም እንዲያገለሉ አእምሮአቸው በርቷል።

… ብዙዎቻችን ሌሎች ያደረጉትን መልካም ነገርን መገንዘብ እና ጊዜና አቅም ሲኖረንም ይህን መደገፍ ይገባናል። …

የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ድሆችን እና የተጨነቁትን በአለም ዙሪያ ለመርዳት ብርሃኑ እና መንፈሱ ስለሚመራው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እመሰክራለሁ።