2022 (እ.አ.አ)
የማበረታታት ቅርስ —ምንባቦች
ህዳር 2022 (እ.አ.አ)


ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)

የማበረታታት ቅርስ

ምንባቦች

የወረቀት አውሮፕላን ከአውሮፕላን ጥላ ጋር

የሆነ ነገር እንዴት ከባድ እንደሆነ ሳጉረመርም እናቴ እንደነገረችኝ፣ “ኦ፣ ሃል፣ በእርግጥ ከባድነው።” መሆንም ነበርበት። ህይወት ፈተና ነች።”

ያንን በተረጋጋ መልኩ በፈገግታ ልትናገር ችላለች ምክንያቱም ሁለት ነገሮችን ታውቅ ስለነበር። ምንም ትግል ቢኖርም አስፈላጊው ነገር ከእሷ ሰማይ አባት ጋር ለመሆን ወደ ቤት መድረሷ ነው። በአዳኛ ላይ ባላት እምነት አማካኝነት ልታደርገው እንደምትችል አወቀች።

ለእኛ ትታው የሄደችው የማበረታታት ቅርስ፣ ሞርሞን ልጁን ሞሮኒን እና ህዝቦቹን ባበረታታቸው በበሞሮኒ 7 ውስጥ የበለጠ ይገለጻል።

ወደ ሰማይ ቤታቸው ወደሚመራው መንገድ ላይ የሚታገሉትን ሰዎች ማበረታቻ በመስጠት ኢየሱስ ክርስቶስን አስቀደመ፣ ልክ እሱን የተከተሉት ሁሉ እንዳደረጉት።

ለእምነታቸው ጥንካሬ ማረጋገጫ ሞርሞን ትህትናን ተመለከተ። …

ከዛ ሞርሞን የልባቸው ስጦታ በክርስቶስ ንፁህ ፍቅር በሚሞላበት መንገድ ላይ እንደሆኑ በመመስከር አበረታታቸው።…

ወደኋላ በመመልከት፣ ያ የልግስና—የክርስቶስ ንፁህ ፍቅር—ስጦታ እናቴን ወደ ቤቷ በመሄድ ትግሏ ውስጥ እንዴት እንዳጠነከራት፣ እንደመራት፣ እንደጠበቃት እና እንደቀየራት አሁን አያለው። …

… አዳኝ ትግላችሁን በጥልቅ ያውቃል። በእምነት፣ በተስፋ እና በልግስና የማደግ ታላቅ ችሎታችሁን ያውቃል።

እርሱ የሚሰጣችሁ ትዕዛዛት እና ቃልኪዳኖች እናንተን የመቆጣጠር ፈተናዎች አይደሉም። ወደ ሚወዷችሁ ወደ ሰማይ አባታችሁ እና ወደ ጌታችሁ ቤት እንድትመለሱ እና ሁሉንም የእግዚአብሔርን ስጦታዎች እንድትቀበሉ ከፍ ሊያደርጓችሁ ያሉ ስጦታ ናቸው።