2022 (እ.አ.አ)
አስራት ለምን እንደምንከፍል
ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)


“አስራት ለምን እንደምንከፍል” ሊያሆና፣ ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)

አስራት ለምን እንደምንከፍል

ምስል
የተደረደሩ ሳንቲሞቸ

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን አባላት የገቢያቸውን አንድ አስረኛ ለቤተክርስቲያኗ ይሰጣሉ። ይህ አስራት ይባላል፡፡ ገንዘቡ በመላው አለም የቤተክርስቲያንን ስራ ለማካሄድ ጥቅም ይውላል፡፡

አስራት ምንድን ነው?

ከእግዚያብሄር ትዕዛዛት አንዱ አስራት መክፈል ሲሆን ይህም የገቢያችንን አንድ አስረኛ ለእርሱ ቤተክርስቲያን መስጠት ማለት ነው። አሥራት በምንከፍልበት ጊዜ ስለተሰጡን በረከቶች ለእግዚአብሔር ምስጋናችንን እናሳያለን። በጌታ እንደምንታመንና በሁሉም ነገር እርሱን ለመታዘዝ ፈቃደኞች መሆናችንን እናሳያለን።

ምስል
ሰዎች ዕቃዎችን በአሥራት ክፍያ መልክ ለመልከ ጼዴቅ ሲያመጡ

መልከ ጼዴቅ—የመጋዘኑ ጠባቂ፣ በክላርክ ኬሊ ፕራይስ

የብሉይ ኪዳን ትምህርቶች

የእግዚያብሄር ህዝቦች ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ አሥራት ይከፍሉ ነበር። ለምሳሌ አብርሃም አሥራት ከፍሏል ( ዘፍጥረት 14፥18–20ይመልከቱ)። ሙሴንና ሚልክያን ጨምሮ የጥንት ነቢያትም ስለ አሥራት ህግ አስተምረዋል( ዘሌዋውያን 27፥30–34ነህምያ 10፥35–37ሚልክያ 3፥10ይመልከቱ)።

የአስራት ህግ ዳግም መመለስ

በ1838 (እ.አ.አ) ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የቤተክርስቲያኗ አባላት አስራት እንዴት መክፈል እንዳለባቸው ጌታን ጠየቀው። የጌታ መልስ በ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 119 ውስጥ ተመዝግቧል፤ እርሱም አባላት የትርፋቸውን አንድ አስረኛ ለቤተክርስቲያን ይስጡ ይላል ( ቁጥር 4ይመልከቱ)። የቤተክርስቲያን መሪዎች “ትርፍ” ማለት ገቢ ማለት እንደሆነ አስተምረዋል።

ምስል
ሰዎች በመጨባበጥ ላይ እያሉ አንድ ሰው ለሌላ ሰው ኤንቨሎፕ ሲያቀብል

ፎቶግራፍ በጄሚ ዴል ጆንሰን

አስራት እንዴት እንደሚከፈል

donations.ChurchofJesusChrist.orgላይ ያለውን የመዋጮ ቅጽ በመሙላት አስራት መክፈል እንችላለን። ወይንም የወረቀት ቅጽ መሙላትና ገንዘቡን ለኤጲስ ቆጶሱ ወይም የቅርንጫፍ አመራር አባል ከሆኑት ለአንዱ መስጠት እንችላለን። ገንዘቡ በሙሉ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች (ቀዳሚ አመራር፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን እና የኤጲስ ቆጶስ አመራር) እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል በጸሎት ወደሚወስኑበት ወደ ቤተክርስቲያኑ ዋና መሥሪያ ቤት ይላካል።

በረከቶች

አሥራት የሚከፍሉ በስጋዊ አና በመንፈሳዊ እንደሚባረኩ ጌታ ቃል ገብቷል። አስራት ሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ከእርሱ እንዲማሩ እንዲሁም በወንጌል እንዲያድጉ እድል በመስጠትም ይባርካቸዋል።

ምስል
የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ

የአስራት ገንዘብ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል

የአስራት ገንዘብ የጌታን ቤተክርስቲያን በመላው አለም በመገንባት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ይህም ቤተመቅደሶችን እና ሌሎች የቤተክርስቲያን ግንባታዎችን መገንባትን፣ ቅዱሳት መጻህፍትን እና ሌሎች ጽሁፎችን ማሳተምን፣ የቤተክርስቲያን ይዞታ ለሆኑ ትምህርት ቤቶች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግን እና የቤተሰብ ታሪክን እንዲሁም የሚስዮናዊ ስራን መደገፍን ይጨምራል።

የአስራት መግለጫ

በዓመት አንድ ጊዜ የቤተክርስቲያኗ አባላት ሙሉ አሥራት ከፋዮች ስለመሆናቸው ለመናገር ከኤጲስ ቆጶሳቸው (ወይም ከቅርንጫፍ ፕሬዚዳንታቸው) ጋር ይገናኛሉ።

የአሥራት ገንዘብ የሚከፈለው

ምስል
ኦክላንድ ካሊፎርኒያ ቤተመቅደስ

የኦክላንድ ካሊፎርኒያ ቤተመቅደስ ፎቶግራፍ በሎንጊን ሎንዛይና ጁኒየር

ምስል
በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉ የመፅሐፈ ሞርሞን ቅጂዎች
ምስል
የመሰብሰቢያ አዳራሽ

አትም