2023 (እ.አ.አ)
ለወጣቶች እና ለልጆች የሚሆኑ የመረጃ ምንጮች
የካቲት 2023 (እ.አ.አ)


“ለወጣቶች እና ለልጆች የሚሆኑ የመረጃ ምንጮች፣” ሊያሆና፣ የካቲት 2023 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ የ ሊያሆና መልዕክት፣ የካቲት 2023 (እ.አ.አ)

ለወጣቶች እና ለልጆች የሚሆኑ የመረጃ ምንጮች

ወላጆች ከወንድ ልጃቸው ጋር ቅዱሳን ጽሁፎችን ሲያነቡ

ወላጆች ለልጆቻቸው ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለወንጌሉ የማስተማር ዋነኛ ሃላፊነት አለባቸው። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ ወላጆች የሚያደርጓቸውን ጥረቶች የሚደግፉ ድርጅቶች፣ ፕሮግራሞች እና ሌሎች ግብዓቶች አሏት፡፡ ወላጆች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ጓደኞች በአንድነት፣ ሁሉም ልጆች እና ታዳጊዎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መርዳት ይችላሉ።

የመጀመሪያ ክፍል ልጆች

ፎቶግራፍ በቤን ጆንሰን

የመጀመሪያ ክፍል

የመጀመሪያ ክፍል ከ18 ወር እስከ 11 ዓመት ለሚሆናቸው ልጆች የተዘጋጀ የቤተክርስቲያኗ ድርጅት ነው። በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ፣ ልጆች በክፍል ትምህርት፣ በሙዚቃ እና በአክቲቪቲዎች ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለወንጌሉ ይማራሉ። የመጀመሪያ ክፍል፣ ልጆች እግዚአብሄር ለእነርሱ ያለው ፍቅር እንዲሰማቸው ሊረዳ ይችላል።

የአሮናዊ ክህነት ቡድን እና የወጣት ሴቶች ክፍሎች

በዓመቱ በጥር ወር ውስጥ ዕድሜያቸው 12 ዓመት የሚሞላቸው ልጆች ወንዶች ከሆኑ ወደ አሮናዊ ክህነት ቡድን ልጃገረዶች ከሆኑ ወደ ወጣት ሴቶች ክፍሎች ይዛወራሉ። በቡድኖቻቸው እና በክፍሎቻቸው ውስጥ ወጣቶች ምስክርነቶቻቸውን ያጠናክራሉ እንዲሁም ሌሎችን ያገለግላሉ።

እጆች ስዕል እየሳሉ።

የልጆች እና ወጣቶች ፕሮግራም

በልጅነቱ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ “በጥበብና በቁመት፣ እና በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት” አደገ (ሉቃስ 2፥52)። የልጆች እና የወጣቶች ፕሮግራም፣ ወጣት የቤተክርስቲያን አባላት የክርስቶስን ምሳሌ እንዲከተሉ ይረዳቸዋል። በሁሉም የሕይወታቸው ዘርፎች—መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ አካላዊ እና እዕምሯዊ ትምህርት ያገኛሉ እንዲሁም ያድጋሉ።

የቤተክርስቲያን መጽሔቶች

የቤተክርስቲያኗ የልጆች መጽሄት የ ጓደኛ መጽሄት ነው። ለወጣቶች ጥንካሬ ለወጣቶች የሚዘጋጅ መጽሄት ነው። እነዚህ መጽሄቶች በተለይ ለልጆች እና ለታዳጊዎች የሚሆኑ ታሪኮችን፣ ትምህርቶችን እና አክቲቪቲዎችን ያካትታሉ።

የመምሪያ መጽሃፍ የሽፋን ገጽ በእስፓንሽ ቋንቋ

ለወጣቶች ጥንካሬ የመምሪያ መጽሃፍ

ለወጣቶች ጥንካሬ፦ምርጫዎችን ለማድረግ የሚረዳ መመሪያ ወጣቶችን ስለወንጌል እውነቶች ያስተምራል። ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል የሚረዱ ውሳኔዎችን እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ ያስተምራቸዋል። በተጨማሪም ወጣቶች ወንጌልን ስለመኖር ሊኖሯቸው ለሚችሏቸው ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶችንም ያካትታል።

የወንጌል ላይብረሪ

የወንጌል ላይብረሪ ቪዲዮዎችን፣ ሙዚቃዎቸን፣ የቅዱሳት መጻህፍት ታሪኮችን እና አክቲቪቲዎችን ጨምሮ ብዙ ዲጂታል የመረጃ ምንጮች አሉት። በተጨማሪም ወላጆች እና መሪዎች የወንጌልን መርሆዎች ለማስተማር የሚጠቀሙባቸውን የመረጃ ምንጮችንም ያካትታል። እነዚህ የመረጃ ምንጮች በ ChurchofJesusChrist.org የወንጌል ላይብረሪ ውስጥ እና በወንጌል ላይብረሪ መተግበሪያ ውስጥ ይገኛሉ።

የኤፍኤስዋይ ጉባኤዎች

ዓመቱ ሲጀምር 14 ዓመት የሚሆናቸው ወጣቶች በለወጣቶች ጥንካሬ (ኤፍኤስዋይ) ጉባኤዎች ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። እነዚህ ዝግጅቶች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነትን ለማጠናከር እና ወጣቶች መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ አካላዊ እና አዕምሯዊ እድገት እንዲያደርጉ የሚረዷቸውን እንቅስቃሴዎች እና የትምህርት ክፍሎች ያካትታሉ።