“አሁን ፍጹም ልንሆን ይገባናልን?” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ የካቲት 2023 (እ.አ.አ)።
ወርሀዊ የ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ የካቲት 2023 (እ.አ.አ)
አሁን ፍጹም ልንሆን ይገባናል?
ከ የጥቅምት 2017 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ንግግር።
ቅዱሳት መጻህፍት የተጻፉት እኛን ለመባረክ እና ለማበረታታት ሲሆን በእርግጥም ያንን ያደርጋሉ። ነገር ግን አንድ አንድ ጊዜ እኛ ወደ ኋላ እንደቀረን የሚስታውሰን አንድ ገፅ እንደሚከሰት ተገንዝባችኋልን? ለምሳሌ፦ “እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ (ማቴዎስ 5፥48)። ያንን ትእዛዝ ስናስብ ወደ አልጋ ተመልሰን በብርድ ልብሱ እስከጭንቅላታችን መሸፈን እንፈልጋለን። እንዲህ ያለው ሰማያዊ ግብ ከአቅማችን በላይ ይመስላል። ሆኖም በእርግጥ ጌታ ልንጠብቀው እንደማንችል የሚያውቀውን ትዕዛዝ በፍጹም አይሰጠንም።
“አዎን፣ ወደ ክርስቶስ ኑ፣ እናም በእርሱም ፍፁማን ሁኑ፣” ሲል ሞሮኒ ይማጸናል። “በሙሉ ሃይላችሁ፣ አዕምሯቸሁ እና ጉልበታችሁ እግዚአብሄርን ከወደዳችሁ… በፀጋውም በክርስቶስ ፍጹም ትሆናላችሁ” (ሞሮኒ 10፥32፤ ትኩረት ተጨምሯል)። እውነተኛ ፍጽምና የምናገኝበት ብቸኛው ተስፋ ከሰማይ እንደ ሥጦታ መቀበል ነው—በስራችን “ማግኘት” አንችልም።
ከኢየሱስ ካደረጋቸው በስተቀር በዚህ በምንጓዘው ምድራዊ ጉዞ ውስጥ ምንም እንከን አልባ የሆኑ ድርጊቶች የሉም፣ ስለዚህ በሥጋዊ ህይወት ውስጥ እያለን የማያቋርጥ መሻሻል ለማድረግ እንጣር እንዲሁም ከራሳችንም ሆነ ከሌሎች ከልክ በላይ መጠበቅን እናስወግድ።
ብንጸና፣ በዘላለም ህይወት ውስጥ የሆነ ቦታ ላይ የእኛ መጣራት ያልቃል እንዲሁም ይጠናቀቃል—ይህ ነው የአዲስ ኪዳን የፍጽምና ትርጓሜ።
© 2023 (እ.አ.አ) በ Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የ Monthly For the Strength of Youth Message, February 2023ትርጉም። Language. 18910 506