“ለመንፈስ ቅዱስ ልባችሁን ክፈቱ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሚያዚያ 2023 (እ.አ.አ)።
ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ)
ለመንፈስ ቅዱስ ልባችሁን ክፈቱ
በዚህ የፋሲካ ሰሞን ቤዛችን ለመሆን በፈቃዱ ወደ ምድር ለመጣው ለውድ ልጁ ስጦታ የሰማይ አባታችንን አመሰግናለሁ። ለኃጢያቶቻችን ክፍያ ማድረጉን እና በትንሳኤ መነሳቱን በማወቄም አመስጋኝ ነኝ። በየቀኑ፣ በኃጢያት ክፍያው ምክንያት፣ ከምወዳቸው ቤተሰቦቼ ጋር ለመኖር አንድ ቀን ከሞት እንደምነሳ በማወቄ የተባረኩኝ ነኝ።
እነዛን ነገሮች የማውቀው ማንኛችንም እነሱን ማወቅ በምንችለው ብቸኛ መንገድ ነው። መንፈስ ቅዱስ ወደ አዕምሮዬ እና ልቤ እውነት እንደሆኑ—አንዴ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ጊዜ—ተናግሯል።
መንፈስ ቅዱስ እንደ ጓደኛችን የሚሆንበት ዋጋ የማይተመንበት ቃል ኪዳን አለን። የእኛ ግዴታ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ቀጣይነት ያለውን መንፈሳዊ ምሪ እና ምቾት ለመቀበል ልባችንን ለመክፈት መምረጥ ነው።
የመጀመሪያው ምርጫ ከእግዚአብሔር ፊት ትሁት መሆን ነው።
ሁለተኛው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን መጸለይ ነው።
ሶስተኛው በትክክል ታዛዥ መሆን ነው።
አራተኛውም የሌሎችን ፍላጎቶች እና ልቦች ለማወቅ እና ለጌታ እንዴት እንደምንረዳቸው ለማወቅ መጸለይ ነው።
በደግነት ወደ እናንተ የተላከውን የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ እንድትሰሙ በሙሉ ልቤ እጸልያለው። እናም መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል እና እርሱን ቋሚ ጓደኛ በማድረግ ደስታ ይኖራችሁ ዘንድ ልባችሁን ሁሌም እንድትከፍቱ እጸልያለው።
© 2023 Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly For the Strength of Youth Message, April 2023 ትርጉም። Language. 19006 506