“ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳ፣” ጓደኛ፣ ሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ)፣ 46–47።
ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ ሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ)
ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳ
ማርያም እና ማርታ አልዓዛር የሚባል ወንድም ነበራቸው። የኢየሱስ ክርስቶስ ጓደኖች ነበሩ።
አልዓዛር በጣም ታመመ። ከዚያም ሞተ። ማርያም እና ማርታ አዘኑ። ኢየሱስ ሲመጣ አብሯቸው አለቀሰ።
ከዚያም ኢየሱስ ወደ አልዓዛር መቃብር አብሯቸው ሄደ። እንዲህ አለ፣ “አልዓዛር ሆይ፣ ወደ ውጭ ና።”
አልዓዛርም ቆመ እና ከመቃብሩ ወጣ። እንደገና ህያው ሆነ። በኢየሱስ አማካኝነት እኛም በድጋሜ መኖር እንችላለን።
© 2023 (እ.አ.አ) Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Friend Message, April 2023 ትርጉም። Language. 19006 506