2023 (እ.አ.አ)
ራስን መቻል ያጠነክረናል
ነሐሴ 2023 (እ.አ.አ)


“ራስን መቻል ያጠነክረናል፣” ሊያሆና፣ ነሐሴ 2023 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ነሐሴ 2023(እ.አ.አ)

ራስን መቻል ያጠነክረናል

ሁለት ሰዎች ዕቃ እያጠቡ

ራስን የቻሉ መሆን ማለት የራሳችንን እና የቤተሰባችንን ፍላጎቶች ማሟላት እንችላለን ማለት ነው። ራሳችንን የቻልን ስንሆን በተሻለ ሁኔታ ጌታን ለማገልገል እንዲሁም ሌሎችን ለመንከባከብም እንችላለን። ነገር ግን ራስን መቻል ማለት ችግሮቻችንን ብቻችንን መጋፈጥ ይኖርብናል ማለት አይደለም። በሚያስፈልገን ጊዜ ከጓደኞች፣ ከቤተሰብ፣ ከአጥቢያ ወይም ከቅርንጫፍ አባላት እና ከባለሙያዎች እርዳታ መጠየቅ እንችላለን።

ራስን የመቻል መርሆዎች

ራስን መቻል ትምሕርትን፣ ታዛዥነትን እና ተግቶ መሥራትን ይጠይቃል። ራሳችንን ለመንከባከብ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን እንዲሁም በሚያስፈልገን ጊዜ ከሌሎች እርዳታ እንጠይቃለን። ሆኖም፣ በትክክል ራስን የቻልን ለመሆን በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ሊኖረንም ይገባል። ራሳችንን በምንረዳበት ጊዜ እርሱ ያጠነክረናል።

ሁለት የተጣመሩ እጆች

በመንፈሳዊ ራስን መቻል

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን ምስክርነታችንን ለማጠናከር በመስራት የራሳችንን በመንፈሣዊ ራስን መቻል ልንገነባ እንችላለን። በመፀለይ፣ ቅዱሳት መፃህፍትን በማጥናት፣ በቤተክርስቲያን በመሳተፍ፣ ትዕዛዛቱን በመጠበቅ እና ወደ ክርስቶስ የሚያቀርቡንን ሌሎች ነገሮች በማድረግ ይህንን ማድረግ እንችላለን። ሊረዳን ፈቃደኛ ስለመሆኑ ያለን እውቀት ሕይወት ከባድ በሚሆንበትም ጊዜ እንኳን በታማኝነት እንድንዘልቅ እምነት ይሰጠናል።

በሥጋዊ ነገሮች ራስን መቻል

በሥጋዊ ነገሮች ራስን የቻሉ መሆን የራሳችንን እና የቤተሰባችንን ቁሳዊ ፍላጎቶች ማሟላትን ያካትታል። ይህም ምግብን፣ ቤትን እና ሌሎች ፍላጎቶችን ያካትታል። ይህንን የምናደርገው ጥሩ ትምሕርት በማግኘት፣ አስፈላጊ ክህሎቶችን በመማር እና በማሳደግ፣ ተግቶ በመስራት፣ ጊዜያችንን በጥበብ በመጠቀም እና ገንዘባችንን በጥሩ ሁኔታ በመያዝ ነው።

ሶስት ሴቶች አብረው እየተራመዱ

በሥሜት እራስን መቻል

በሥሜታዊ ራስን መቻል በድፍረት እና በእምነት ከሥሜታዊ ችግሮች ጋር የመስማማት ችሎታ ነው። ሁላችንም ፈተናዎች እና እንቅፋቶች አሉብን። ለወንጌሉ ምስጋና ይግባውና ምላሽ የምንሠጥባቸውን መንገዶች መምረጥ እንደምንችል እናውቃለን። በጌታ እምነት በማድረግ ምላሽ መስጠት ሌሎች አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በላቀ ተስፋ የመጋፈጥ ችሎታችንን ያሳድጋል።

ትምህርት

ሁልጊዜ መማር አለብን። እግዚአብሄር በመላ ሕይወታችን እንዲሁም በሚቀጥለው ዓለም አእምሯችንን እንድናስተምር እና ክህሎቶቻችንን እንድናሻሽል ይፈልጋል። የበለጠ ስንማር የበለጠ በጎ ተጽዕኖ ማሳደር እንዲሁም ለራሳችን፣ ለቤተሰባችን እና ለተቸገሩ ማቅረብ የምንችል እንሆናለን።

ወጣት ልጅ ቦርሳ ተሸክሞ

ራስን የቻሉ የመሆን በረከቶች

የራሳችንን ራስን መቻል ስናሻሽል በታላቅ ተስፋ እና ሰላም እንደምንባረክ ነቢያት አስተምረዋል። ቤተሰቦቻችንን እና ሌሎች የተቸገሩትን ለመርዳት እንችላለን። እንዲሁም በተጨማሪ እድሎችና እድገትን ለመቀጠል በሚያስችል ብቃት እንባርካለን።

የቤተክርስቲያን የጥናት ምንጮች

ካስማችሁ ራስን የመቻል ቡድኖች ሊኖሩት ይችላል። እነዚህ ስለገንዘብ አያያዝ ወይም የተሻለ ሥራ ለማግኘት ስለሚያስችሉ መርሆች ሊያስተምሯችሁ ይችላሉ። ተዛማጅ መረጃዎችን በወንጌል ቤተመጽሓፍት ውስጥ መፈለግ ትችላላችሁ። በመጀመሪያ “Books and Lessons” ከዚያም “Self-Reliance” ይምረጡ።