“ግንዛቤን እሹ” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ነሐሴ፣ 2023 (እ.አ.አ)
ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔት መልዕክት፣ ነሐሴ 2022(እ.አ.አ)
ግንዛቤን እሹ
ከ ሚያዝያ 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ንግግር የተወሰደ።
የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለመረዳት የምንሻበት አላማችን በእግዚአብሔር እና በእርሱ መለኮታዊ የደስታ እቅድ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ ላይ ያለንን እምነት ማሳደግ እና ዘላቂ መለወጥ ላይ መድረስ መሆን አለበት። እንዲህ ያለው የላቀ እምነት እና መለወጥ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳኖችን እንድንገባ እና እንድንጠብቃቸው ይረዳናል፣ ይህም ኢየሱስን ለመከተል ያለንን ፍላጎት ያጠናክራል እንዲሁም በውስጣችን እውነተኛ መንፈሳዊ ለውጥን ያመጣል። ይህ ለውጥ የበለጠ ደስተኛ፣ ውጤታማ እና ጤናማ ህይወትን ያጎናፅፈናል እንዲሁም ዘላለማዊ እይታ እንዲኖረን ይረዳናል።
እዚህ ላይ ለመድረስ፣ ራሳችንን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በማጥለቅ፣ በእነሱ በመደሰት፣ የእርሱን ትምህርት በመማር እና እርሱ በኖረበት መንገድ ለመኖር በመሞከር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መጣበቅ ይገባናል። ወደ እርሱ ስንመጣ እና በእርሱ ስናምን በፍፁም እንደማንራብና እንደማንጠማ እንገነዘባለን እርሱን የምናውቀው እና ድምፁን የምንለየውም ያኔ ነው። (ዮሐንስ 6:35 ይመልከቱ)።
ያ በአጋጣሚ ሊሆን አይችልም። ራሳችንን ከላቀ የፈሪሃ እግዚአብሄር ተጽዕኖ ጋር ማስማማት ቀላል ነገር አይደለም፤ እግዚአብሔርን መለመን እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዴት የህይወታችን ዕምብርት ማድረግ እንዳለብን መማርን ይጠይቃል።
የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በቁም ነገር፣ በቅንነት፣ በቁርጠኝነት እና ከልብ ለመረዳት ስንፈልግ እና በእውነተኛ ዓላማ እና በመንፈሱ አማካኝነት እርስ በርሳችን ስንማማር፣ እነዚህ ትምህርቶች ልቦችን ሊለውጡ እና በእግዚአብሔር እውነት የመኖር ፍላጎትን ሊያነሳሱ እንደሚችሉ እመሰክርላችኋለሁ።
© 2023 (እ.አ.አ) በ Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved። በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የ Monthly For the Strength of Youth Message, August 2023 (እ.አ.አ) ትርጉም። Language. 19046 506