2023 (እ.አ.አ)
መንፈሱን መሪያችሁ አድርጉት
ጥቅምት 2023 (እ.አ.አ)


“መንፈሱን መሪያችሁ አድርጉት፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ጥቅምት 2023 (እ.አ.አ)።

ወርሀዊ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ጥቅምት 2021(እ.አ.አ)

መንፈሱን መሪያችሁ አድርጉት

የሰማይ አባታችን በምድራዊ ህይወታችን ውስጥ ፈተናዎች፣ ችግሮች፣ እና ብጥብጦች እንደሚያጋጥሙን ያውቃል፤ በጥያቄዎች፣ ሃዘኖች፣ ፈተናዎች እና ድክቶች እንደምንቸገር ያውቃል። ምድራዊ ጥንካሬን እና መለኮታዊ ምሪትን ይሰጠን ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ሰጥቷል።

በመለኮታዊ ምደባ፣ መንፈሱ በጌታ ብርሃን እንድንሄድ ያነሳሳናል፣ ይመሰክርልናል እንዲሁም ይገፋፋናል። በህይወታችን ውስጥ ያለውን ተፅእኖ የማወቅ እና ምላሽ የመስጠት ቅዱስ የሆነ ሃላፊነት አለብን።

ያንን የምናደርገው እንዴት ነው?

በመጀመሪያ፣ ለመንፈሱ ብቁ የሚያደርገንን ህይወት ለመኖር እንጥራለን።

ሁለተኛ፣ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ፍቃደኛ መሆን አለብን።

ሶስተኛ፣ መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ መገንዘብ አለብን።

አራተኛ፣ በመጀመሪያው ማነሳሻ ላይ ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ አለብን።”

“ተደሰቱ፣ እንደሚገባችሁ እመራችኋለሁና” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 78፥18) የሚለውን የጌታን ጥሪ ከልብ አድርገን እንውሰደው። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ይመራናል። ከእግዚአብሔር እንደሚመጡ በማወቅ፣ በመጀመሪያ የመንፈስ ምሪት ላይ ፈጥነን በመተግበር፣ ወደ መንፈሱ ቀርበን እንኑር። መንፈስ ቅዱስ እኛን ለመምራት፣ ለመንከባከብ፣ እና ሁሌም አብሮን ለመሆን ኃይል እንዳለው እመሰክራለሁ።