2010–2019 (እ.አ.አ)
መንፈስ ቅዱስ ይምራ
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


15:43

መንፈስ ቅዱስ ይምራ

በመለኮታዊ ምደባ፣ በጌታ ብርሃን እንድንሄድ ያነሳሳናል፣ ይመሰክርልናል እንዲሁም ያስታውሰናል።

ወንድሞችና እህቶች፣ ሁላችሁም እንድምታስታውሱት፣ የጌታን ስራ መፋጠን በፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን እና በዛሬ ጠዋቱ መልዕክት እያየን ነው። ፕሬዘዳንት ሞንሰን፣ እንወድሃለን፣ እንደግፍሃለን፣ እንዲሁም ውድ ነብያችን እንፀልይልሃለን።1

በዚህ ሳምንት የመንፈስን መፍሰስ ተሰምቶናል። በዚህ ታላቅ አዳራሽ ውስጥም ሆናችሁ ከቤታችሁ እዩ ወይም በዓለም ሩቅ ቦታ በመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተሰብሰቡ፣ የጌታን መንፈስ የመሰማት እድሉን አግኝታችኋ። ያም መንፈስ በልባችን እና በአዕምሮአችን በዚህ ጉባኤ የተማርነውን እውነት አረጋግጧል።

የዚህን ታዋቂ መዝሙር ቃላት

መንፈስ ቅዱስ ይምራ፤

እውነትን ያስተምር።

ስለ ክርስቶስ ይመሰክራል፣

አዕምሮአችንን በሰማይ እይታ ያበራል።2

ከኋለኛው ቀን ራዕይ ሶስቱ ስላሴ ከሶስት የተለያዩ ግለሰቦች እንደተዋቀሩ እናውቃለን፥ እነሱም አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ናቸው። “አብ ሥጋ እና እንደ ሰው ተጨባጭ የሆነ አጥንት እና አካል አለው፤ ወልድም ደግሞ እንዲሁ ነው፣ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ሥጋና አጥንት ያለው አካል የለውም፣ ነገር ግን የመንፈስ ግለሰብ” እንደሆነ እናውቃለን። “ይህ ባይሆን ኖሮ፣ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ለመኖር ባልቻለ ነበር።” (3)

የዛሬ መልዕክቴ የመንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ውስጥ አስፈላጊነት ላይ ነው። የሰማይ አባታችን በምድራዊ ሕይወታችን ውስጥ ፈተናዎች፣ ችግሮች፣ እና ብጥብጦች እንደሚያጋጥመን ያውቃል፤ በጥያቄዎች፣ ሃዘኖች፣ ፈተናዎች እና ድክቶች እንደምንቸገር ያውቃል። ምድራዊ ጥንካሬን እና መለኮታዎ ምሪትን ሊሰጠን መንፈስ ቅዱስን አዘጋጀ።

መንፈስ ቅዱስ ከጌታ ጋር ያስረናል። በመለኮታዊ ምደባ፣ በጌታ ብርሃን እንድንሄድ ያነሳሳናል፣ ይመሰክርልናል እንዲሁም ያስታውሰናል። በሕይወታችን ውስጥ ግፊቱን ለማወቅ እና ምላሽ ለመስጠት ቅዱስ የሆነ ሃላፊነት አለብን።

የጌታን ቃል ኪዳን አስታውሱ፥ “አዕምሮአችሁን የሚያበራውን፣ ልባችሁን በደስታ የሚሞላውን መንፈሴን አካፍላችኋለሁ።”4 ያን ማረጋገጫ እወደዋለሁ። መንፈሳችንን የሚሞላው ደስታ በቀን ተቀን ሕይወታችን ውስጥ የዘላለም እይታን ያመጣል። ያ ደስታ በችግር እና የልብ ህመም መካከል እንደ ሰላም ይመጣል። መፅናናትን እና መበረታታትን ይሰጣል፣ የወንጌልን እውነታዎች ይፈታል እናም ለጌታ እና ለመላ የእግዚአብሔር ልጆች ያለንን ፍቅር ያሰፋል። ምንም እንኳን ለእንደዚህ አይነት ያለው ፍላጎት ከፍተኛ ቢሆንም፣ ዓለም በብዙ መንገዶች እረስቶታል እናም ትቶታል።

በእያንዳንዱ ሳምንት ቅዱስ ቁርባን ስንካፈል፣ “ሁልጊዜ እርሱን” ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እና መስዋትነቱን “ለማስታወስ” ቃል እንገባለን። ይህን ቅዱ ቃል ኪዳን በመጠበቅ፣ “መንፈስ ቅዱሱ ሁሌም [ከእኛ] ጋር እንደሚሆን ቃል ተገብቶልናል።”5

እንዴት ነው ያንን ማድረግ የምንቸለው?

መጀመሪያ፣ ለመንፈሱ ብቁ የሆነ ሕይወት እንኖራለን።

መንፈስ ቅዱስ “ጌታ አምላካቸውን ቀን ወደ ቀን ለማስታወስ ጥብቅ የሆኑትን”6 ሰዎች ይከተላል። ጌታ እንደመከረው፣ “የዚህን ዓለም ነገሮች ወደ ጎን ትተን መልካም ነገሮችን መፈለግ አለብን።”7 ምክንያቱም “መንፈስ ቅዱስ ንፁ ባሆነ ቤተ-መቅደስ ውጥ አይኖርምና።”8 የእግዚአብሔርን ህግጋት ለመከተል ሁሌም መሞከር፣ ቅዱስ መጽሐፍቶችን ማጥናት፣ ቤተ-መቅደስ መካፈል እና ለአስራ ሶስተኛው የእምነት አንቀፅ፣ “ታማኝ፣ እውነተኛ፣ ንፁ፣ ቅን፣ ምግባር ያለው እና ለሁሉም ሰው መልካም አድራጊ ሆነን መኖር አለብን።”

ሁለተኛ፣ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ፍቃደኛ መሆን አለብን።

ጌታ እንዲህ ቃል ገብቷ፣ “በመንፈስ ቅዱስ በአዕምሮአችሁ ምን መምጣት እንዳለበት እና በልባችሁ ምን መኖር እንዳለበት እነግራችኋለሁ።”9 ይህን መረዳት የጀመርኩት እንደ ወጣት ሚስዮናዊ በኒው ጀርዚ፣ በስኮታዊ ሜዳዎች ላይ በሆንኩበት ሰዓት ነው። በአንድ ሞቃታማ የሐምሌ ጠዋት ላይ ጓደኛዬ እና እኔ ከቤተ-መቅደስ አደባባይ የሆኑ አባል የልሆኑ ሰዎችን ለመመልከት ተነሳሳን። የኤልዉድ ሻፈር ቤትን አንኳኳን። ወ/ሮ ሻፈር በትህትና መለሰችን።

በሩን በምትዘጋው ጊዜ፣ ከዚ ቀደም አድረጌው የማላውቀውን አንድ ነገር ለማድረግ ተሰማኝ። እግሬን በበሩ መንገድ ላይ እድርጌ፣ “በምልዕክታችን ፍላጎት የሚኖረው ሰው ይኖር ይሆን ወይ ብዬ ጠየቅኩኝ።” የ16 ዓመት ሴት ልጇ ማርቲ ፍላጎት ነበራት እና ከዛ ቀን በፊት ለምሪት በትህትና ፀልያ ነበር። ማርቲ ከእኛ ጋር ተገናኘች እና በውይይቱ ተሳተፈች። ሁለቱም ቤተክርስቲያኑን ተቀላቀሉ።

ሽማግሌ ራዝባንድ እንደ ሚስዮን

ከማርቲን ጥምቀት በመነሳት፣ 136 ሰዎች ብዚ ቤተሰቦችዋን ጨምሮ ተጠመቁ እና የወንጌል ቃል-ኪዳኖችን አደረጉ። በዛ ሞቃታማ የሀምሌ ጠዋት እግሬን በበሩ መንገድ ላይ እንዳደርግ የመንፈስ ቅዱሱን ምሪት በማዳመጤ ምን አይነት ደስታ ይሰማኛል። ማረቲንና ብዙ የሆኑት የእሷ ቤተሰቦች ዛሬ በዚህ ይገኛሉ።

ሶስተኛ፣ መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ መገንዘብ አለብን።

እንደ ልምዴ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ብዙን ጊዜ እንደ ስሜት ነው የሚናገረው። በምታቁት፣ ለእናንተ ትርጉም ባለው፣ በሚያነሳሳችሁ ቃላቶች ውስጥ ይሰማችኋል። ጌታ ለእነሱ ሲፀልይላቸው የሰጡትን የኔፋወያንን ምላሽ ተመልከቱ፥ “እናም ህዝቦቹ አዳመጡ እናም መሰከሩ፣ ልባቸውም ተከፈተ፣ እናም የፀሎቱን ቃላት በልባቸው ተረዱት።”10 የፀሎቱን ቃላት በልባቸው ተሰማቸው። የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ የተረጋጋ እና ዝቅተኛ ነው።

በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ኤሊያስ ከባል ካህናት ጋር ተጋጨ። ካህናቱ የባልን “ድምፅ” እንደ መብረቅ መጥቶ መስዋዕታቸውን እንዲያበራላቸው ጠበቁ። ነገር ግን ምንም ድምፅ አልነበረም፣ እንዲሁም ምንም እሳት አልነበረም።11

በሌላ ሰዓት፣ ኤሊያስ ፀለየ። “እነሆም እግዚአብሔር አለፈ፣ በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮችን ሰነጠቀ ዓለቶችንም ሰባበረ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱም በኋላ የምድር መናወጥ ሆነ፣ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም።

“ከምድር መናወጥ በኋላ እሳት ሆነ፣ እንግዚአብሔር ግን በእሳት ውስጥ አልነበረም። ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ።”12

ያንን ድምፅ ታውቁታላችሁን?

ፕሬዘደንት ሞንሰን እንዲህ አስተማሩ፣ “የሕይወትን ጎዳና ስንከተል፣ የመንፈስን ቋንቋ እንማር።”13 መንፈስ የሚሰማንን ቃላት ይናገራል። እነኚ ስሜቶች ቅን፣ ተግባራዊ የማድረግ ግፊት፣ የሆነ ነገር የማደረግ፣ የሆነ ነገር የማለት፣ በተወሰነ መንገድ ምላሽ የመስጠት ናቸው። በአምልኮአችን የተለመደ ወይም የምንኩራራ ከሆንን፣ ዓለምን በመከተል ከተሳብን እና ካቀለልነው፣ የመሰማት ችሎታችን ቀንሶ እናገኘዋለን። ስለ መንፈስ ቅዱስ ኔፊ ለላማን እና ለላሙኤል እንዲህ አለ፣ “ድምፁንም በየጊዜው ሰምታችኋል፣ እናም በለሰለሰ ድምፅ ተናግሮአችኋል፣ ነገር ግን እናንተ ደንዝዛችኋል፣ ስለዚህ ቃሉ ሊሰማችሁ አልቻለም።”14

ባለፈው ሰኔ በደቡብ አሜሪካ ለስራ ሄጄ ነበር። ጠባብ በሆነ የኮሎምቢያ፣ ፔሩ እና ኢኳር የ10 ቀናት ጉብኝት ላይ ነበርን። በፖረቶቬሆ እና ማንታ በሚባሉ የኢኳዶር ከተሞች ላይ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏቸው፣ በአስር ሺ የሚቆጠሩትን አቁስሏቸው፣ ቤታቸውን አፈራርሶባቸው ነበር። በዕቅዳችን ውስጥ በእነዚህ ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ አባላትን ለመጎብኘት ተገፋፋሁ። መንገዱ በመበላሸቱ እዛ መድረሳችንን እርግጠኞች አልነበርንም። በእርግጥ፣ እዛ መድረስ እንደማንችል ተነግሮን ነበር፣ ነገር ግን መገፋፋቱ ሊሄድ አልቻለም። በመቀጥ፣ ተባረክን እና ሁለቱንም ከተሞች መጎብኘት ቻልን።

በዚህ አጭር ማሳሰቢያ፣ በፍጥነት የተዘጋጀውን ስብሰባ ትንሽ የሚሆኑ የክህነት መሪዎች ይገኛሉ ብዬ ነበር። ይሁን እንጂ፣ በእያንዳንዱ ካስማ ፀሎት ቦታዎቹ እስከ መድረኩ ድረስ ሞልቶ አገኘናቸው። አንዳንዶቹ የሐይማኖት ታማኞች፣ ከቤተክርስቲያኑ ጋር አብረው የቆዩ መስራቾች፣ ሌሎችን በአምልኮ እንዲቀላቀሏቸው ያበረታቱ እና በሕይወታቸው ውስጥ መንፈስ እንዲሰማቸው ያደረጉ ሰዎች ነበሩ። በፊት ለፊት መቀመጫ ላይ የተቀመጡት በመሬት መንቀጥቀጡ የሚወዱትን ሰዎችና ጎረቤቶች ያጡ ነበሩ። በዛ ለተገኙት ሰዎች በሙሉ የመጀመሪያውን ሐዋርያዊ በረከትን ለመስጠት ተገፋፋሁ። በክፍሉ ፊት ለፊት ላይ ብቆምም፣ በእያንዳንዱ እራስ ላይ እጆቼ እንዳረፉ ያህል እና የጌታ ቃላት ሲፈሱ ነበር የተሰማኝ።

ሽማግሌ እና እህት ራስባንድ በደቡብ አሜሪካ

በእዛ አላለቀም። ልክ ኢየሱስ ክርስቶስ በአሜሪካዎች ያሉትን ሰዎች ሲጎበኝ እንደተናገረው ለመናገር ተገፋፋሁ። “ህፃናቶቻቸውን ወሰዳቸው... እናም ባረካቸው፣ እና ስለእነርሱ ወደ አብ ጸለየ።”15 በኢኳዶር ነበርን፣ በአባታችን ስራ ላይ ነበርን እናም እነኚህ የእርሱ ልጆች ነበሩ።

አራተኛበመጀመሪያው መገፋፋት ላይ መተግበር አለብን።

የኔፊ ቃላትን አስታውሱ፥ “ማድረግ ያለብኝን ነገሮች ቀድሜ ሳላውቅ በመንፈስ ተመራሁ። ይሁን እንጂ እኔም ወደ ፊት ሄድኩ።”16

እኛም ወደ ፊት መሄድ አለብን። በመጀመሪያ ግፊታችን ላይ መተማመን አለብን። አንዳንዴ እናስተባብላን፣ መንፈሳዊ ግፊት እየተሰማን እንደሆነ ወይም ዝም ብሎ የራሳችን ሃሳብ እንደሆነ እናስባለን። ለሁለተኛ ጊዜ ስናስብ፣ ለሶስተኛም ጊዜ ስናስብ...ሁላችንም አድርገነው እናውቃለን...መንፈስን እያስወገድነው ነው። መልኮታዊ ምክሮችን ጥያቄ ውስጥ እያስገባን ነው። ነብዩ ዪሶፍ ስሚዝ እዲህ አለ፤ የመጀመሪያ መገፋፋትን ከሰማችሁ፣ ከአስር ዘጠኝ ጊዜ በትክክል ታገኙታላችሁ።17

አሁን ማሳሰቢያ፤ ለመንፈስ ቅዱስ ምላሽ ስለሰጣችሁ እርችቶችን አትጠብቁ። አስታውሱ፣ የለሰለሰ እና የትንሽ ድምፅ ስራ ላይ ነው ያላችሁት።

በኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ እንደ ሚስዮን ፕሬዘዳንት ሆኜ ሳገለግል፣ በብሮንክስ ውስጥ ከተወሰኑ ሚስዮናችን ጋር ነበርኩኝ። አንድ ወጣት ቤተሰቦች ገቡ እና በአቅራቢያችን ተቀመጡ። ለወንጌሉ ወርቃማ ሄነው ታዩ። ሚስዮናችን ከእኔ ጋር ሲጎበኙ ተመለከትኩ፣ ከዛ እነዚ ቤተሰቦች ምግባቸውን ጨርሰው በበሩ ሲወጡ አየሁ። ከዛም እንዲህ አልኩኝ፣ “ሽማግሌዎች፣ ዛሬ እዚህ ትምህርት ነበር። ተወዳጅ ቤተሰቦች ወደ ምግብ ቤቱ ሲገቡ ተመልክታችኋል። ምን ማድረግ ነበረብን?”

አንደኛው ሚስዮን በፍጥነት እንዲህ ተናገረ፥ “ተነስቼ ከእነሱ ጋር ለመነጋገር አስቤ ነበር። ግፊቱ ተሰምቶኝ ነበር ነገር ግን ምላሽ አልሰጠሁም።”

እንዲህም አልኩኝ፣ “ሚስዮኖች፣ ሁሌም በመጀመሪያው መገፋፋት ላይ ተግባራዊ ማድረግ አለብን።” የተሰማህ መገፋፋት መንፈስ ቅዱስ ነበር!”

የመጀመሪያ መገፋፋት ንፁ የሰማይ መነሳሳት ናቸው። ለእኛ ሲያረጋግጡ ወይም ሲመሰክሩ፣ ምን እንደሆኑ ልናውቅ እና ላናሳልፋቸው ይገባል። በተደጋጋሚ በችግር ላይ ያሉ ሰዎችን፣ ቤተሰብን እና ጓደኞችን ለመርዳት የሚያነሳሳን መንፈስ ነው። “ስለሆነም የሚያንሸኳሽከው እና ሁሉንም ነገሮች የሚሰረስረው ለስላሳው እና ትንሽዬው ድምፅ ወንጌልን እንድናስተምር፣”18 ስለ መመለስ እና ኢየሱስ ክርስቶስ እንድንመሰክር፣ እርዳታ እና እንክብካቤ እንድንሰጥ እና የእግዚአብሔር ውድ ልጆችን ለማዳን ወደ እድሎች ይጠቁመናል።

ቀድሞ ደራሾች በሚለው ውሰዱት። በብዙ ማህበረስብ ውስጥ ለሃዘን፣ ለአደጋ፣ ወይም ለድንገተኛ ነገሮች ቀድሞ ደራሾች የእሳት አደጋ ሰዎች፣ ፖሊሶች፣ የህክምና ሰዎች ናቸው። መብራት አብርተው ይደርሳሉ፣ ለእነሱ በጣም አመስጋኝ እንደሆንን መጨመር እፈልጋሁ። የጌታ መንገድ ትንሽ ግልፅ አይደለም፣ ነገር ግን አፋጣኝ ምላሽ ይጠይቃል። አምላክ የሁሉንም ልጆቸሁን ፍላጎት ያውቃል...እናም ለመርዳት ማን ዝግጁ እንደሆነ ያውቃል። በጠዋት ፀሎታችን ጌታን ዝግጁ መሆናችንን ከነገርነው፣ ምላሽ ለመስጠት ይጠራናል። ምላሽ ከሰጠን፣ በተደጋጋሚ እራሳችንን ምሬዘዳንት ሞንሰን እንደሚጠሩት “በጌታ ተልዕኮ”19 ላይ ሆነን እናገኘዋለን። እርዳታን ከሰማይ የሚያመጡ መንፈሳዊ ቀድሞ ደራሾች እንሆናን።

ወደ እኛ ለሚመጡት መገፋፋቶች ልብ ብለን ካደመጥን፣ በራዕይ መንፈስ እናድጋለን እናም የበለጠ በመንፈስ የሚገፉ ሃሳቦችን እና አቅጣጫዎችን እንቀበላለን። ጌታ እንደዚህ አለ፣ “እምነታችሁን መልካም እንድታደርጉ በሚመራችሁ በዛ መንፈስ ላይ አድርጉ።”20

“ተደሰቱ እኔ እመራችኋሁና”21 የሚለውን የጌታን ጥሪ ከልብ አድርገን እንውሰደው። በመንፈስ ቅዱስ ይመራናል። ወደ መንፈስ ቀርበን እንኑር፣ በመጀመሪያ መገፋፋታችን ላይ ቀድመን እንተግብር፣ ከእግዚአብሔር እንደሚመጡ እንወቅ። የመንፈስ ቅዱስን የመምራት፣ የመንከባከብ፣ አብሮን የመሆን ኃይል የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።