ለቤተክርስቲያኗ ጓደኞች እና መርማማዎች
የራዕይ ዋጋን ከከፈላችሁ፣ ትሁት ከሆናችሁ፣ ካነበባችሁ፣ ከጸለያችሁ፣ እና ንስሀ ከገባችሁ፣ ሰማያት ይከፈታሉ እናም ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ታውቃላችሁ።
በአርብ ከሰዓት በኋላ፣ በመስከረም 16፣ 1988 (እ.አ.አ)፣ በቪንቸንተ ሎፔዝ የዎርድ ስብሰባ ቤት ውስጥ በቦይነስ አይረስ፣ አርጀንቲና፣ እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ተጠምቄ ነበር። ጥሩ ጓደኛዬ፣ አሊን ስፓናኡስ፣ በዚህ ቀን አጠመቀኝ፣ እኔም ደስተኛነትና፣ ለመማር ተጨማሪ ፍላጎት ተሰማኝ።
ዛሬ፣ ወደ ጥምቀት በተጓዝኩበት የተማርኳቸውን አንዳንድ ትምህርቶች ላካፍላችሁ እፈልጋለው—ትምህርቶቹም የቤተክርስቲያኗ አባላት ላልሆናችሁ ለምታዳምጡት እንዲረዷችሁ ተስፋ አለኝ። የእኔ እንደነበረው፣ ልባችሁ በመንፈስ እንዲነካ እጸልያለሁ።
መጀመሪያ፣ ከሚስዮኖች ጋር መገናኘት
ያለ ከባድ ፈተናዎች፣ ፍላጎቶች፣ ወይም ጥያቄዎች ከሚስዮኖች ጋር ለመገናኘት እና ትምህርታቸውን ለማዳመጥ ሰው ለምን ይፈልጋል? ለእኔ ምክንያቱ ፍቅር ነበር—የሴት ፍቅር፣ ስሟ ረኔ ነበር። አፈቀርኳት፣ እናም ላገባት እፈልግ ነበር። ልዩ ነበረች እናም ከማውቃቸው ወጣት ሴቶች የተለየ መሰረታዊ መርሆ ነበራት። ነገር ግን ወደድኳት እናም እንድታገባኝ ጠየኳት—እርሷም እምቢ አለች።
ግራ ገባኝ። እርሷን ማግኘቴ መልካም እንደሆነ አውቅ ነበር። ቆንጆ፣ የ24 አመት፣ ከዩንቨርስቲ የተመረቅኩኝ ስራ ያለኝ ነበርኩኝ። ስለአላማዋ ተናገረች—ወደ ቤተመቅደስ ሊወስዳት እና የዘለአለም ቤተሰብ እንዲኖራት የሚያስችlትን ሰው ስለማግባት—እናም ያቀረብኩላትን እምቢ አለች። ግንኙነታችንን ለመቀጠል ፈለኩኝ፣ ስለዚህ ሚስዮኖችን ለማዳመጥ ተስማማሁ። ከሚስዮኖች ጋር ለመገናኘት ይህ ጥሩ ምክንያት ነውን? ለእኔ ነበር።
ከሚስዮኖች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ስገናኝ፣ ያሉትን ብዙ አልገባኝም ነበር፣ እናም ላሉትም ብዙ ትኩረት አልሰጠሁም ነበር። ልቤ ለአዲስ ሀይማኖት ተዘግቶ ነበር። እነርሱ ትክክል እንዳልሆኑ ለማረጋገጥ እና ረኔ እንድታገባኝ ለማሳመን ጊዜ ለማግኘት ብቻ ነበር የፈለኩትኝ።
ዛሬ ልጆቼ በሚስዮን አገልግለዋልም እያገለገሉም ናቸው፣ እናም እነዚህ ወጣት ወንዶች እና ወጣት ሴቶች የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማስተማር መስዋዕት የሚያደርጉበትን ተረድቻለሁ። አሁን ያስተማሩኝን አስደናቂ ሚስዮኖች ሽማግሌ ሪቻርድሰንን፣ ሽማግሌ ፌረልን፣ እና ሽማግሌ ሀይላንድን በትጋት ባዳምጣቸው ኖር ብዬ እመኛለሁ።
ስለዚህ ለመጀመሪያው ትምህርት፥ ለቤተክርስቲያኗ ጓደኞች እና መርማሪዎች፣ ከሚስዮኖች ጋር ከተገናኛችሁ በኋላ፣ እባካችሁ ለሚሉት ትኩረት ስጡ፤ አስፈላጊ የህይወት ጊዜአቸውን በመስዋዕት አሳልፈው የሚሰጡ ናቸውና።
ሁለተኛ፣ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ
ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ስብሰባ ስሄድ፣ ሊገቡኝ ያልቻሉ ቃላቶችን ሰማሁ። ቢሀይቮች ማን ናቸው? አሮናዊ ክህነት ምንድን ነው? የሴቶች መረዳጃ ማህበር ምንድን ነው?
ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያኗ ስብሰባ የምትሄዱ ከሆነ እና በማትረዱት ነገር የምትምታቱ ከሆናችሁ፣ አታስቡበት! እኔ ምንም አላውቅም ነበር። ነገር ግን ያጋጠመኝን አዲስ የሰላም እና የደስታ ስሜት አስታውሳለሁ። በዚያ ጊዜ አላወቅኩትም ነበር፣ ግን መንፈስ ቅዱስ በጆሮዬ እና በልቤ፣ “ይህ ትክክል ነው” ብሎ ያሾከሽክልኝ ነበር።
ስለዚህ ይህን ትምህርት በአንድ አንቀጽ እናስቀምጠው፥ የምትምታቱ ከህናችሁ፣ አትጨነቁ—ያጋጠማችሁን ስሜት አስታውሱ፤ እነርሱ ከእግዚአብሔር የሚመጡ ናቸው።
ሶስተኛ፣ መፅሀፈ ሞርሞንን አንብቡ
ከሚስዮኖች ጋር ለብዙ ከተገናኘሁ በኋላ፣ እድገት አልነበረኝም። የወንጌሉ እውነትነት ማረጋገጫ እንደተሰጠኝ አልተሰማኝም።
አንድ ቀን ረኔ እንዲህ ጠየቀችኝ፣ “መፅሐፈ ሞርሞንን እያነበብክ ነህን?”
እኔም “አይደለሁም” ብዬ መለስኩኝ። ሚስዮኖችን እያዳምጥኩኝ ነበር—ያ ብቁ አይደለምን?
በአይኗ እምባ ኖሯት፣ ረኔ መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ አረጋገጠችልኝ እናም እውነት እንደሆነ ለማወቅ ከፈለኩኝ፣ የሚደረግበት ብቸኛ መንገድ ይህን በማንበብ ነው! ብላ ገለጸችልን። ከዚያም ጠይቅ!
አንብቡ፣ በልባችሁ አሰላስሉ፣ እናም “ዘለዓለማዊ አብ እግዚአብሔርን በክርስቶስ ስም፣ ... በቅን ልባችሁ፤ ከእውነተኛ ፍላጎት፣ በክርስቶስ አምናችሁ [ጠይቁ]” (ሞሮኒ 10፥4) መፅሐፈ ሞርሞን እውነት ከሆነ፣ ይህች እውነተኛ ቤተክርስቲያን ነች።
ስለዚህ ሶስተኛ ትምህርትን በአንድ አንቀፅ እናስቀምጥ፥ እነዚህን ነገሮች ስትቀበሉ—መፅሐፈ ሞርሞንን—እንድታነቡት እና እውነት እንደሆኑ እግዚአብሔርን እንድትጠይቁ ስትለምኑ፣ ይህን አደርጉ!
በመጨረሻም ንስሀ መግባት
ለመካፈል የምፈልገው የመጨረሻ አጋጣሚም ንስሀ ስለመግባት ነው። የሚስዮን ትምህርትን ለመውሰድ ከጨረስኩኝ በኋላም፣ በህይወቴ ነገርን ለመቀየር እንደሚያስፈልገኝ ተቀባይ አልነበርኩም። አንድ ቀን እንዲህ ያለኝ የእስፔን ቋንቋ በደንብ መናገር የማይችለው ወጣት ሚስዮን ሽማግሌ ከትለር ነበር፣ “ዋኪን፣ አብረን አልማ 42ን እናንብብ፣ እናም ይህን ስናነብ ስምህን በዚህ እናገባለን።”
ይህ የማይረባ ነው ብዬ አሰብኩኝ፣ ነገር ግን ሽማግሌ ከትለር ጠየቀ እና በቁጥር 1 ውስጥ አነበበ፥ “እናም እንግዲህ ልጄ [ዋኪን]፣ ስለተነገሩት ዳግም መመለስ በተመለከተ በመጠኑ የምለው አለኝ።” ኦ! መፅሐፉ ለእኔ እየተናገረ ነው።
እናም በቁጥር 2 ውስጥ አነበብን፥ “እንግዲህ እነሆ ልጄ [ዋኪን] ይህንን ነገር ለአንተ እገልፅልሃለሁ።፣” እናም የአዳም መውደቅ ተገለጸ።
እናም በቁጥር 4 ውስጥ አነበብን፥ “እናም ለ[ዋኪን] የንስሃ ጊዜ እንደተሰጠም እንመለከታለን።”
በቀስታ፣ አንቀጽ በአንቀጽ፣ ወደ መጨረሻው ሶስት ቁጥሮች እስከምንደርስ ድረስ ማንበብ ቀጠልን። ከዚያም በሀይለኛ ሀይል ተመታሁ። መፅሀፉ ለእኔ በቀጥታ ተናገረኝ፣ እናም ማልቀስ ጀመርኩኝ፣ “እናም አሁን ልጄ [ዋኪን፣] እነዚህ ነገሮች ከእንግዲህ እንዳያስቸግሩህ እፈልጋለሁ፤ እናም ኃጥያትህ ብቻ በዚያ ወደ ንስሃ በሚያመጣህ ጭንቀት ያስጨንቅህ።” (ቁጥር 29)።
አሁን ዋጋ ባለመክፈል ራዕይ ለመቀበል እጠብቅ እንደነበር ተረዳሁ። እስከዚያ ጊዜ ድረስ ለእግዚአብሔር በእውነት አልተናገርኩም ነበር፣ እናም በአካል በማይገኝ ሰው ጋር የመነጋገር ሀሳብ ሞኝነት ነበር። ራሴን ማዋረድ እና በአለማዊ አዕምሮዬ ምንም ሞኝነት ቢመስልም እንዳደርግ የተጠየኩትን ማድረግ ነበረብኝ።
በዚያ ቀን ልቤን ለመንፈስ ከፈትኩኝ፣ ንስሀ ለመግባት ፍላጎት ነበረኝ፣ እናም ለመጠመቅ ፈለግኩኝ። ከዚያ ጊዜ በፊት ግን፣ ንስሀ መግባትን እንደ መጥፎ፣ ከኃጢያት እና ስህተት ከማድረግ ጋር የተያያዘ እንደሆነ አስብበት ነበር፣ ግን በድንገት በተለየ ብርሀን—ለእድገት እና ለደስታ መንገድን እንደሚያጸዳ ጥሩ ነገር ተመለከትኩት።
ሽማግሌ ከትለር በዚህ ይገኛል፣ እናም አይኖቼን በመክፈቱ አመሰግነዋለሁ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በህይወቴ ያደረኳቸው ውሳኔዎች በሙሉ ራሴት ትሁት ባደረኩበት፣ ለምህረት በጸለይኩበት፣ እና ለእኔ የከፈለው የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ የህይወቴ ክፍል በሆነበት በዚያ ጊዜ ተፅዕኖ ያለበት ነው።
ስለዚህ ሶስተኛ ትምህርትም፣ በአንድ ዓረፍተ-ነገር ንስሀ መግባትን ተለማመዱ፤ ለመቀየር ከመፈለግ ይበልጥ ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚስባችሁ ምንም ነገር የለም።
ውድ መርማሪዎች፣ የቤተክርስቲያኗ ጓደኞች፣ ዛሬ የምታዳምጡ ከሆናችሁ፣ ከሁሉም ይበልጥ ታላቅ ወደ ሆነው ደስታ በጣም ቀርባችኋል። ቅርብ ናችሁ!
በልቤ ሀይል እና ከነፍሴ ጥልቅ፣ እጋብዛችኋለኑ፥ ሂዱ እና ተጠመቁ! ይህም ከምታደርጉት ሁሉ በላይ የሚበልጥ ነው። የእናንተ ህይወት ብቻ ሳይሆን ደግሞም የልጆቻችሁን እና የልጅ ልጆቻችሁን ህይወት የሚቀይር ነው።
ጌታ በቤተሰብ ባርኮኛል። ረኔን አገባሁ፣ እናም አራት ቆንጆ ልጆች አሉን፡ በጥምቀቴ ምክንያት፣ እንደ ጥንት ነቢይ ሌሂ፣ እነርሱን፣ የእግዚአብሔር ፍቅር የሆነውን፣ የህይወት ዛር ፍሬን እንዲቀበሉ ልጠይቃቸው እችላለሁ (1 ኔፊ 8፥15፤ 11፥25 ተመልከቱ)። ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ እጋብዛቸዋለሁ።
ስለዚህ አጋጣሚዎቼን አስቡባቸው፣ እናም (1) ሚስዮኖች ለሚሉት ትኩረት ስጡ፣ (2) ወደ ቤተክርስቲያን ሂዱ እናም መንፈሳዊ ስሜታችሁን አስታውሱ፣ (3) መፅሐፈ ሞርሞንን አንብቡ እናም ጌታን እውነት እንደሆነ ጠይቁ፣ (4) ንስሀ መግባትን ተለማመዱ እናም ተጠመቁ።
የራዕይ ዋጋን ከከፈላችሁ፣ ትሁት ከሆናችሁ፣ ካነበባችሁ፣ ከጸለያችሁ፣ እና ንስሀ ከገባችሁ፣ ሰማያት ይከፈታሉ እናም ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ፣ እርሱም አዳኜ እንደሆነ፣ እና የእናንተም እንደሆነ እንደማውቀው፣ እናንተም ታውቃላችሁታውቃላችሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።