2010–2019 (እ.አ.አ)
መንገዱን አዘጋጁ
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


12:14

መንገዱን አዘጋጁ

የተለያዩ ሚስዮኖች እና ስልጣኖች የተሰጧቸው ብሆንም፣ የአሮናዊ እና የመልከ ጼዴቅ ክህነት በደህንነት ስራ የማይለያዩ ተባባሪዎች ናቸው።

በ30 አመቴ፣ በፈረንሳይ ለሚገኘው የንግድ ቸርቻሪ ቡድን መስራት ጀመርኩኝ። አንድ ቀን የካምፓኒው ፕሬዘደንት፣ የሌላ እምነት ጥሩ ሰው፣ ወደ ቢሮው ጠረኝ ። ጥያቄው አስደነገጠኝ፥ “በቤተክርስቲያንህ ውስጥ ቄስ እንደሆንኩኝ አሁን ገና አወቅሁ። እውነት ነው?”

እንዲህ መለስኩኝ፣ “አዎን፣ ትክክል ነው። ክህነት ተሸካሚ ነኝ።”

በመልሴ ሲደነቅ እየታየ፣ እንዲህም ጠየቀ፣ “ነገር ግን በሀይማኖት ትምህርት ቤት አጥንተህ ነበርን?”

“በእርግጠም፣” ብዬ መለስኩኝ፣ “ከ14 እስከ 18 አመቴ የሰምነሪ ትህርቶችን በየቀኑ አጠና ነበር!” ከወንበሩ ሊወድቅ ነበር።

በሚደንቀኝ ሁኔታ፣ በካምፓኒዎቹ ቡድን አንዱ ውስጥ የአስተዳደሪያ ሀላፊነት ሊሰጠኝ ከብዙ ሳምንቶች በኋላ ወደ ቢሮው እንደገና ጠራኝ። ተገርሜ ነበር እናም እንደዚህ አይነት አስፈላጊ ሀላፊነት ለመያዝ ገና ወጣት እና ብዙ ልምምድ እንደሌለኝ ጥርጣሬዬን ነገርኩት። በበጎ ፈገግታው፣ እንዲህ አለ፣ “ይህም እውነት ይሆናል፣ ግን ግድ የለውም። እኔ መሰረታዊ መርሆችን አውቃለሁ፣ እናም በቤተክርስቲያንህ የተማርካቸውን አውቃለሁ። እኔ እፈልግሃለሁ”።

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ስለተማርኩት ትክክል ነበር። የሚቀጥሉት አመታት አስቸጋሪ ነበሩ፣ እናም ከወጣትነቴ ጀምሮ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በማገልገል ከነበረኝ ልምምዶች ውጭ ሌላ ምንም ውጤታማ ለመሆን እንደምችል አላውቅም ነበር።

በትንሽ ቅርንጫፍ ውስጥ በማደግ ተባርኬ ነበር። ቁጥራችን ትንሽ ስለነበር፣ ወጣቶች በቅርንጫፉ ሁሉም አይነት ድርጊቶች እንዲሳተፉ ይጠሩ ነበር። ብዙ ስራ ነበረብኝ እናም ጠቃሚ መሆንን እወድ ነበር። በእሁድ በቅዱስ ቁርባን ጠረጴዛ ላይ አገለግላለሁ፣ የክህነት ቡድኔን አገለግላለሁ፣ እናም በተለያዩ ጥሪዎችም እሰራ ነበር። በሳምንት ውስጥ አባቴ እና ሌሎች የክህነት ተሸካሚዎች አባላትን በቤታቸው ሲያስተምሩ፣ የታመሙትን እና የተሰቃዩትን ሲያፅናኑ፣ እና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሲረዱ አብሬአቸው እሄድ ነበር። ማንም እኔ ለማገልገል ወይም ለመምራት ወጣት ነው ብሎ የሚያስብ የለም ነበር። ለእኔ፣ ሁሉም የተለመደ እና የተፈጥሮ ይመስል ነበር።

በወጣትነቴ ያደረኳቸው አገልግሎቶች ምስክሪነቴ እንዲያድግ እና ህይወቴን በወንጌል እንድመሰርት አደረገ። ክህነታቸውን ሌሎችን በመባረክ ውሳኔ ባደረጉ በመልካም እና ርህራሄ ባላቸው ሰዎች ተከብቤ ነበር። እንደ እነርሱ ለመሆን እፈልግ ነበር። ከእነሱ ጋር ሳገለግል በጊዜው ከተገነዘብኩት በላይ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ እና ደግሞም በአለም ውስጥ መሪ ለመሆን ተማርኩኝ።

በዚህ ምሽት ስብሰባ ውስጥ የሚከፈሉ ወይም ይህን የሚያዳምጡ የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች የሆኑ ብዙ ወጣቶች አሉ። በዚህ ወደተሰበሰቡት ስመለከት፣ ብዙዎቻችሁ ሁሉም የመከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች ከሆኑ በጎልማሳ ወንዶች አጠገብ፣ ምናልባት በአባታችሁ፣ በአያታችሁ፣ በታላቅ ወንድሞቻችሁ፣ ወይም በክህነት መሪዎቻችሁ አጠገብ አያችኋለሁ። ይወዱዋችኋል፣ እናም በታላቅ ሁኔታም፣ በዚህ ምሽት ከእናንተ ጋር ለመሆን መጥተዋል።

ይህ ስብሰባ በሁለቱ ክህነቶች መካከል የሚገኘውን ወንድምነት እና አንድነት የሚያሳይ አስደናቂ እይታ ነው። የተለያዩ ሚስዮኖች እና ስልጣኖች የተሰጧቸው ብሆንም፣ የአሮናዊ እና የመልከ ጼዴቅ ክህነት በደህንነት ስራ የማይለያዩ ተባባሪዎች ናቸው። እጅ ለእጅ ተያይዘው ይሄዳሉ እናም ለእርስ በራስ ታላቅ ፍላጎት አላቸው።

በሁለቱ ክህነቶች መካከል ያለ የቅርብ ግንኙነት ፍጹም ሞዲል የሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመጥምቁ ዮሀንስ መካከል ያለው ግንኙነት ነው። ማንም መጥምቁ ዮሀንስን ያለ ኢየሱስ ሊያስበው ይችላልን? ያለ ዮሀንስ የዝግጅት ስራ የአዳኝ ሚስዮን ምን ይሆን ነበር?

መጥምቁ ዮሀንስ ከነበሩት ሚስዮኖች በላይ ሁሉ ታላቅ የሆነ ነበር የተሰጠው፥ “የጌታን መንገድ ለማዘጋጀት”1 እርሱን በውሀ ለመጥመቅ፣ እንድቀበሉት ህዝቡን ማዘጋጀት ነበር። ይህም “ጻድቅ … እና … ቅዱስ [ሰው]፣”2 በታናሹ ክህነት የተሾመ፣ የሚስዮኑን እና የስልጣኑ አስፈላጊነት እና መጠን በፍጹም ያወቀ ነበር።

ሰዎች እርሱን ለማዳመጥና በእርሱ ለመጠመቅ ወደ ዮሀንስ መጡ። እንደ እግዚአብሔር ሰው በመብቱ የተከበረ እና የተወደሰ ሰው ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ሲመጣ፣ ዮሀንስ ከእርሱ በላይ ለሆነው ክብርን አሳየ እናም እንዲህ አወጀ፣ “እኔ በውኃ አጠምቃለሁ፤ ዳሩ ግን እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሞአል፤ እኔ የጫማውን ጠፍር ልፈታ የማይገባኝ፥ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይልቅ የሚከብር ይህ ነው።”3

ለእርሱም በኩል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የአብ አንድያ ልጅ፣ ከፍተኛውን ክህነት የያዘው፣ በትህትና የዮሀንስን ስልጣን አሳወቀ። ስለእርሱም አዳኝ እንዲህ አለ፣ “ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም”4

የሁለቱ ክህነት ተሸካሚዎች መካከል ያለው ግንኙነት በኢየሱስ እና በመጥምቁ ዮሀንስ በተመሰረተው የሚያነሳሳ ምሳሌ የሚከናወን ቢሆን በክህነት ቡድኖቻችን ውስጥ ምን ሊፈጠር እንደሚቻል አስቡበት። ወጣት የአሮናዊ ክህነት ወንድሞቼ፣ እንደ ዮሀንስ፣ ሀላፊነታችሁ ለታላቅ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ስራ “መንገድን ማዘጋጀት”5 ነው። ይህን የምታደርጉት በብዙ የተለያዩ መንገዶች ነው። የጥምቀት እና የቅዱስ ቁርባን ስርዓቶችን ታከናውናላችሁ፡ ወንጌልን በመስበክ፣“የእያንዳንዱን አባል ቤትን [በመጎብኘት]”6 እና “ቤተክርስቲያኗን [በመጠበቅ]”7 ለጌታ ሰዎችን ታዘጋጃላችሁ። የጾም በኩራትን በመሰብሰብ ደሆችን ትረዳላችሁ፣ የቤተክርስቲያኗን የስብሰባ ቤቶች እና ንብረቶች በመንከባከብ ትሳተፋላችሁ። ስራችሁ አስፈላጊ እና ቅዱስ ነው።

አባቶች፣ ኤጲስ ቆጶሶስች፣ የወጣት ወንዶች አማካሪ፣ ወይም የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች የሆናችሁ ጎልማሳ ወንድሞቼ፣ ታናሹን ክህነት ወደተሸከሙት በመዞር እና ከእናንተ ጋር አብረው እንዲያገእግሉ በመጋበዝ የአዳኝን ምሳሌ ለመከተል ትችላላችሁ። በእውነትም፣ ይህ ግብዣ የሚመጣው ከጌታ ነው። እንዲህ ብሏል፣ “ስለዚህ፣ ከእናንተ ጋር በአነስተኛው ክህነት የተሾሙትን ውሰዱ፣ እናም ቀጠሮም ያድርጉ፣ እናም መንገድንም እንዲያዘጋጁላችሁ፣ እናም እናንተ ራሳችሁ ልታከናውኑት የማትችሉትን ቀጠሮ ያሟሉላችሁ ዘንድ በፊታችሁ ስደዷቸው።”8

ወጣት ወንድሞቻችሁን “መንገድን እንዲያዘጋጁ” ስትጋብዙ የያዙትን ቅዱስ ስልጣን እንዲያውቁ እና እንዲያከብሩ ትረዷቸዋላችሁ። ይህን በማድረግ፣ አንድ ቀን ከፍተኛ ክህነትን ለመቀበል እና ለመለማመድ መንገዳቸውን ለማዘጋጀት እርዳታ ትሰጣላችሁ።

የጸጥተኛ፣ አሳቢ፣ እና ጎበዝ ስለሆነው ወጣት ካህን አሎክስ እውነተኛ ታሪክን ልንገራችሁ። በአንድ እሁድ ቀን የአልክስ ኤጲስ ቆጶስ በታላቅ ሀዘን በክፍል ውስጥ ተቀምጦ አሌክስን አገኘው። ወጣቱ ልጅ አባል ስላልሆነ አባቱ ስናገር፡ ያለ አባቱ ወደ ቤተክርስቲያን መሄዱ እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነ ገለጸ። ከዚያም በእምባ ቤተክርስቲያኗን ትቶ መሄዱ እንደሚሻለው አመለከተ።

ለዚህ ወጣት በነበራቸው እውነተኛ ሀሳብ፣ ኤጲስ ቆጶስ ወዲያም አሌክስን እንዲረዱ የዎርድ ሸንጎን አደራጁ። እቅዱ ቀላል ነበር፥ አልክስ በተሳታፊነት እንዲቀጥል እና በልብ የሚሰማ የውንጌል ምስክርነት እንዲኖረው ለመርዳት፣ እርሱን “በመልካም ሰዎች መክበብ እና አስፈላጊ ስራዎችን መስጠት” ያስፈልጋቸው ነበር።

ወዲያው የክህነት ወንድሞች እና የዎርድ አባላት አሌክስን እርዳታ ሰጡት እናም ለእርሱ ያላቸውን ፍቅርና ድጋፍ ገለጹ። የታላቅ እምነት እና ፍቅር ሰው የሆነው የሊቀ ካህናት ቡድን መሪም የቤት ለቤት ጉብኝት ተባባሪ አስተማሪው እንዲሆንም ተመረጠ። የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባላትም እርሱን ደገፉ እናም የእነርሱ የቅርብ ደጋፊ አደረጉት።

ኤጲስ ቆጶስም እንዲህ አሉ፥ “አልክስ ስራ እንድበዛበት አደረግነው። በጋብቻ፣ በቅብር፣ ሰዎች የሚቀመጡበትን በማሳየት ረዳ፣ በመቃብር ቦታ ቅደሳ ረዳ፣ ብዙ አዲስ አባላትን ጠመቀ፣ ወጣት ወንዶችን በአሮናዊ ክህነት ሾመ፣ ወጣቶችን ትምህርት አስተማረ፣ ከሚስዮኖች ጋር አስተማረ፣ ህንጻዎችን ለጉባኤ ከፈተ፣ እናም ከጉባኤ በኋላም በምሽት ህንጻዎችን ቆለፈ። አገለገለ፣ በየሸመገሉ አባላትን በማረፊያ ቦታቻው ከእኔ ጋር ጎበኘ፣ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ንግግር አቀረበ፣ በሆስፒታል ለሚገኙት ወይም በቤታቸው ታመው ለነበሩት ቅዱስ ቁርባን በመባረክ አቀረበ፣ እናም እንደ ኤጲስ ቆጶስ ልመካቸው ከምችላቸው ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ ሆነ።”

አሌክስ እና ኤጲስ ቆጶሱ

ትንሽ በትንሽ፣ አሌክስ ተቀየረ። በጌታ እምነቱም አደገ። በራሱ እና በያዘው የክህነት ሀይል በራስ መተማመን አገኘ። ኤጲስ ቆጶሱም እንዲህ ፈጸሙ፥ “እንደ ኤጲስ ቆጶስ ባገለገልኩበት ጊዜ ውስጥ ከነበሩት አሌክስ ለእኔ ታላቅ በረከት ነበረም ነውም። ከእርሱ ጋር በመገናኘቴ እንዴት ታላቅ እድል ነበር። በእውነትም በክህነት አገልግሎቱ ከዚህ ወጣት በላይ በመዘጋጀት ወደ ሚስዮን የሄደ ሌላ ማንም እንደሌለ አምናለሁ።”9

ውድ ኤጲስ ቆጶሶች፣ ስትሾሙ እና ለዎርዳችሁ ስትለዩ፣ እንደ አሮናዊ ክህነት ፕሬዘደንት እና እንደ ካህን ቡድን መሪ የምታገለግሉበት ቅዱስ ጥሪ አላችሁ። ከባድ ሸከም እንደምትሸከሙ አውቃለሁ፣ ነገር ግን ለእነዚህ ወጣቶች ያላችሁን ሀላፊነት ከሁሉም በላይ ከፍተኛ ማድረግ ይገባችኋል። ይህን ችላ ለማለት ወይም የዚህ ሚናችሁን ለሌላ ለመስጠት አትችሉም።

በዎርዳችሁ ስለሚገኙት እያንዳንዱ የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች እንድታሰላስሉ እጋብዛችኋለሁ። ማንኛቸውም የተተዉ ወይም ጥቅም የሌላቸው እንደሆኑ ሊሰማቸው አይገባም። እናንተ እና ሌሎች የክህነት ወንድሞች ሊረዱ የሚችሉ ወጣት ሰው አለ? ከእናንተ ጋር አብሮ እንዲያገለግል ጋብዙት። በአብዛኛው ጊዜ፣ እምነታቸው እና ለወንጌል ያላቸው ፍቅር የክህነአቸውን በማጉላት ለመረዳት በሚቻልበት ጊዜ፣ ወጣት ወንዶችን ለማስደሰት እና የተመልካች ሀላፊነት እንዲኖራቸው ለማድረግ እንጥራለን። በደህንነት ስራ በመሳተፍ፣ ከሰማይ ጋር ይገናኛሉ እናም ለመለኮታዊ ችሎታቸው እውቀት ሊኖራቸው ይችላሉ።

የአሮናዊ ክህነት የእድሜ ቡድን፣ የማስተማሪያ ወይም የመሳተፊያ ፕሮግራም፣ ወይም የቤተክርስቲያኗን ወጣት ወንዶች የምንጠራበት ስም ከመሆን በላይ ነው። ይህም በታላቁ የነፍስ የማዳን—የወጣት ወንዶች ነፍስን እና የሚያገለግሉትን ነፍሶች የማዳን ስራ ውስጥ የሚሳተፍ ሀይል እና ስልጣን ነው። የአሮናዊ ክህነትን ለቤተክርስቲያኗ ወጣት ወንዶች በሙሉ እውነተኛ ቦታ፣ በምርጥ ቦታ፣ እናም በማገልገል በመዘጋጀትና በማከናወን ቦታ እናስገባው።

ውድ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ወንድሞቼ፣ ሁለቱን የእግዚአብሔር ክህነት አንድ የሚያደርገውን አስፈላጊ ግንኙነት እንድታጠናክሩ እጋብዛችኋለሁ። የአሮናዊ ክህነት ወጣቶቻችሁ መንገዱን በፊታችሁ እንዲያዘጋጁ ሀይል ስጧቸው። በልበ ሙሉነትም፣ “እንፈልጋችኋለን” በሏቸው። ለእናንተ ለወጣት የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎችም፣ ከታላቅ ወንድሞቻችሁ ጋር ስታገለግሉ የጌታ ድምፅ እንዲ ሲል እንዲሰማችሁ እጸልያለሁ፥ “ታላላቅ ነገሮችን ስለምታደረግ የተባረክ ነህ። እንደ ዮሀንስ፣ ከእኔ በፊት መንገዱ እንድታዘጋጅ ተልከሀል።”10 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።