ይህች የዘላለም ህይወት ናት
እግዚአብሔር እናንተን ያውቃል እናም እናንተ እርሱን ታውቁ ዘንድ ይጋብዛል።
ቀጣይ ትውልዶች፣ ወጣት እና ጎልማሶች፣ ያላገባችሁ ወይም ያገባችሁ፣ የወደፊት የጌታ የቤተክርስቲያን መሪዎች ለእናንተ እናገራለሁ። በዛሬው ጊዜ ባሉት የዓለም ላይ ክፋት ሁሉ፣ ብጥብጥ፣ ፍርሃት፣ እንዲሁም ግራ መጋባት፣ አምላክን ስለ ማወቅ ግርማ እና በረከት በተመለከተ በግልጽ በማብራራት ከእናንተ ዘንድ ይህን እናገራለሁ።
ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይ አባት የደስታ እቅድስ እና እናንተ በዚህ ያላችሁን ቦታ ብዙ እውነቶችን አስተማረ። የእናንተን ማንነት እንድትረዱ የሚረዱ እነዚህን እንደ እግዚአብሄር ልጅ እና አላማችሁን በዚህ ምድር እንድታውቁ የሚያደርጉት ላይ አተኩራለሁ።
መጀመሪያ፥ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”1
ሁለተኛ፥ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”2
እባካችሁ እነዚህን እውነታዎች አእምሮአችሁ ውስጥ አቆዩ—የሚያስተምሩት ለምን—ሁኔታውን ስገልጽ እንዴት እኔና ሁላችንም እግዚአብሄርን ወደ ማወቅ እንመጣለን።
ጸሎት በኩል እርሱን እወቁ
ወጣት ጓደኞቼ፣ እኛም በጸሎት አማካኝነት አምላክን ማወቅ መጀመር እንችላለን።
በሚያዝያ 7፣ 1829 (እ. አ. አ) የ 22 ዓመቱ ኦሊቨር ካውደሪ ለ23 ዓመቱ ጆሴፍ ስሚዝ ጸሃፊ በመሆን ጥረቱን ጀመረ። ልክ እንደ እናንተ ወጣት ነበሩ። ኦሊቨር ስለ ወንጌል መመለስ እና በዚህም ውስጥ ስላለው የራሱ ሚና በተመለከተ ከአምላክ ማረጋገጫ ለማግኘት ጠይቀዋል በምላሹም፣ እሱ የሚከተለውን መገለጥ ተቀበለ፤
“እነሆ፣ አንተ እንደ ጠየከኝ ታውቃለህ፣ እናም እኔ አይምሮህን አብርቼልህ ነበር …
“አዎን፣ ሃሳብህንና የልብህን ፍላጎት ከእግዚአብሄር ይልቅ ማንም የሚያውቅ እንደሌለ እንድትረዳ እነግርሃለሁ። …
“… ተጨማሪ ምስክርነትን ከፈለክ፣ በልብህ ወደ እኔ የጮኽበትን በዚያ ሌሊት ላይ አእምሮህን ጣል። …
“ለአእምሮህ እኔ ሰላምን ተናግሬ አልነበረን … ? ከእግዚአብሔር ከመጣ ምስክርነት ይልቅ ምን አይነት ምስክርነት ልትቀበል ትችላለህ?”3
በእምነት እናንተ ስትጸልዩ፣ መንፈሱ ለእናንተ ሲያነጋግር የእግዚአብሔር ፍቅር ይሰማችኋል። ምንም ያህል አንዳንድ ጊዜ ብቸኝነት ወይም እርግጠኛ አለመሆን ቢሰማችሁም፣ በዚህ ዓለም ላይ ብቻችሁን አይደላችሁም። እግዚአብሄር እናንተን በግል ያውቃል። በምትጸልዩ ጊዜ እሱን ወደማወቅ ትመጣላችሁ።
ቅዱሳት መጻሕፍትን በማጥናት እርሱን እወቁ
ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠኑ፣ ስለ አዳኝ ብቻ ሳይሆን የምትማሩት፣ አዳኝን ለማወቅ ትችላላችሁ።
በሚያዝያ 1895 (እ.አ.አ)፣ ሽማግሌ ብሩስ አር. መካንኪ በአጠቃላይ ጉባኤ ተናገሩ—ከ13 ቀናት በኋላም ሞቱ። ምስክራቸውንም እንዲህ ፈጸሙ፥
“እኔ ከምስክሮች አንዱ ነኝ፣ እናም በሚመጡት ቀናት ውስጥ እኔ በእጁ ላይ እና በእግሮቹ ላይ ያለውን የምስማር ምልክቶች እዳሣለሁ እናም በእንባዬም እግሮቹን አርሳለሁ።
“ነገር ግን አሁንከማውቀው በላይ እርሱ የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ልጅ እንደሆነ፣ የእኛ አዳኝ እና ቤዛ እንደሆነ፣ እናም ቤዛ እና አዳኝ እንደሆነና ስርየት በቤዛው ደሙ አማካኝነት እንጂ ሌላ ምንም መንገድ የለም።”4
በዛ ቀን ሽማግሌ መኮንኬ ሲናገሩ የሰማን በፍጹም እንዴት እንደተሰማን አልረሳንም። ንግግራቸውን ሲጀምሩ፣ ምስክርነታቸው ለምን ሃያል እንደሆነ ገለጹ። እንዲህ አሉ፥
“እነዚህን ድንቅ ነገሮች ስናገር የቅዱሳን መጽሃፍት ቃላትናቸው ብላችሁ ብታስቡም፣ የራሴን ቃላት እጠቀማለሁ። …
“እርግጥ ነው ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ በሌሎች ታውጇል ነገር ግን አሁን የእኔ ናቸው፣ የእግዚአብሔር መንፈስ እነርሱ እርግጥ እንደሆኑ ለእኔ መስክሮአል እናም አሁን ጌታ እንደአዲስ እንደገለጠልኝ ይቆጠራልና። እኔም ድምጹን ሰምቻለሁ እናም ቃሎቹን አውቃለሁ።”5
ቅዱሳን መጽሃፍትን በምታጠኑ እና በምታሰላስሉ ጊዜ፣ የእግዚአብሄርን ድምጽ ትሰማላችሁ፣ ቃላቱን ታውቃላችሁ እናም እሱንም ለማወቅ ትችላላችሁ። እግዚአብሄርም የዘላለም እውነቱን በግል ይገልጽላችኋል እነዚህ ትምህርቶች እና መሰረተ መርሆች የማንነታችሁ አካል ይሆናሉ እናም ከውስጥ ነፍሳችሁ ይመነጫሉ።
ከግል ጥናት በተጨማሪውም፣ ቅዱሳን መጻህፍትን እንደ ቤተሰብ ማጥናት አስፈላጊ ነው።
በቤታችን ውስጥ ልጆቻችን የመንፈስን ድምጽን ለማስተዋል እንዲማሩ ፈልገናል። በየቀኑ እንደ ቤተሰብ መጽሃፈ ሞርሞንን ስናጠና ይህ ተከስቷል ብለን እናምናለን። ምስክርነታችን ቅዱስ እውነታዎችን ስንነጋገር ተጠናክሯል።
ቅዱሳን መጽሃፍት ማጥናት ለእያንዳንዳችን በግል የሚሆነንን ትምህርት ለማምጣት መንገድ ይሆናል። በየቀኑ ቅዱሳን መጽሃፍትን በምታጠኑ ጊዜ፣ ብቻችሁንም ሆነ ከቤተሰ ጋር፣ የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ለመገንዘብ ትማራላችሁ እናም እግዚአብሄርን ታውቃላችሁ።
የሱን ፍቃድ በሟሟላት እወቁት
ከመጸለያችን እና ቅዱሳን መጽሃፍትን ከማንበባችን በተጨማሪ፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማከናወን አለብን።
አዳኝ የእኛ ፍጹም ምሳሌ ነው። እንዲህም አለ፣ “ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።”6
ከትንሳኤ የተነሳው አዳኝ ለኔፋውያን ሲገለጽ፣ እንዲህ አለ፣ “እናም እነሆ እኔ የአለም ብርሃን እናም ህይወት ነኝ፤ እናም አብ ከሰጠኝ መራራ ፅዋም ጠጥቻለሁ፣ እናም የአለምን ሓጢያት ለመቀበልም አብን አክብሬአለሁ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ በሁለም ነገሮች የአብን ፈቃድ ፈጽሜአለሁ።”7
እናንተ እና እኔ ቃል ኪዳናችንን በማክበር፣ ትእዛዛቱን በመጠበቅ፣ እናም እግዚአብሔርን እና ሰዎችን በማገልገል የአብን ፈቃድ እናፈጽማለን።
ባለቤቴ፣ ሮንዳ፣ እና እኔ ምናልባት ከናንተው ወላጆች ጋር የሚመሳሰሉ መደበኛ ሰዎች የሆኑ ወላጆች አሉን። ነገር ግን እኔ ስለ ወላጆቻችንን አንድ የምወደው ነገር ቢኖር አምላክን ለማገልገል ሕይወታቸውን የወሰኑ መሆናቸው ነው፣ እናም እንዲሁ እንድናደርግ አስተማሩን።
የሮንዳ ወላጆች ለሁለት ዓመታት ብቻ በትዳር እንደቆዩ፣ የ23 አመቱ አባቷ የሙሉ ጊዜ እንዲያገለግሉ ተጠሩ። እሱም ወጣት ሚስቱን እና የ2 ዓመት የሆናትን ሴት ልጃቸውን ትቶ ሄደ። ከዛን ሴት ልጃቸውን ለዘመድ በመተው፣ የአገልግሎቱን የመጨረሻ 7 አመታት ከሱ ጋር እንድታገለግል ሚስቱም ተጠራች።
ከጥቂት አመታት በኋላ፣ አሁን ከአራት ልጆቻቸው ጋር፣ ሚሱላ ሞንታና በሚባል ቦታ አባቷ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ቦታ ሲሉ ቀየሩ። ሆኖም ግን፣ ጥቂት ወራት በዛ እንደቆዩ ፕሬዚዳንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል እና የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ማርክ ኢ ፒተርሰን ለአማቼ አዲሱ ለተከፈተው ካስማ ፕሬዚደንት እንዲሆኑ የአገልግሎት ጥሪ ሰጧቸው። እርሳቸውም 34 አመታቸው ብቻ ነበሩ። የራሱን ፍቃድ ሳይሆን የጌታን ፈቃድ በመሻታቸው፣ የዩኒቨርሲቲው ሐሳብ ወደ ኋላ ቀረ።
ወላጆቼ ከ30 አመት በላይ በቤተመቅደስ ውስጥ አገልግለዋል—አባቴ እንደ አታሚ፣ እናቴ እንደ ስርዓት አከናዋኝ። አምስት የሙሉ ጊዜ አገልግሎትን በሪቨር ሳይድ ካሊፎርኒያ፣ በኡላንባታር ሞንጎሊያ፣ በናይሮቢ ኬንያ፣ በናቩ እልኖይ ቤተመቅደስ፣ እና ሞንተሪይ ሜክሲኮ ቤተመቅደስ አብረው ፈጽመዋል። በሜክሲኮ አዲስ ቋንቋን ለመማር ጠንክረው ተማሩ፣ ይህም በ80 አመት ቀላል አይደለም። ነገር ግን የራሳቸውን የህይወት መሻት ከመከተላቸው ይልቅ የጌታን ፈቃድ ለመፈጸም ፈለጉ።
ለእነርሱም፣ እና እራሳችሁን አሳልፋችሁ ለሰጣችሁ በአለም ዙሪያ ለምታገለግሉ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሁሉ፣ ጌታ ለሐላማን ልጅ፣ ለነቢዩ ኔፊ የተናገረውን ቃላት አስተጋባለሁ፥ “ባደረግሃቸው ነገሮች… አንተ የተባረክህ ሰው ነህ፤ አልፈራሃቸውም፣ እናም ለህይወትህም አልሰሰትህም፤ ነገር ግን የእኔን ፈቃድ እናም ትእዛዛቴን ለመጠበቅ ይህን አድርገሃልና … ።”8
እኛ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በታማኝነት እሱን እና ሌሎችን ሰዎች በማገልገል ለመፈጸም ስንፈልግ፣ የእርሱን ሞገስ ይሰማናል እናም ከልብ እርሱን ወደማወቅ እንመጣለን።
እንደሱ በመምሰል እወቁት
አዳኛችን ሲነግረን እግዚአብሔርን ለማወቅ በጣም የተሻለው መንገድ እንደ እርሱ መሆን ነው። እንዲህ አስተማረ፥ “ስለዚህ፣ እናንተ ምን አይነት ሰዎች ትሆኑ ዘንድ ይገባችኋ? እውነት እላችኋለሁ እንደ እኔ ሁኑ።”9
ልክ እንደሱ ለመሆን ብቁ መሆን አስፈላጊ ነው። እሱም ሲያዝ፣ “አንዳነጻችሁ ዘንድ፣ እራሳችሁን አንጹ፤ አዎ፣ ልባችሁን አጥሩ፣ እጃችሁንም አጽዱ።”10 እሱን የመምሰልን መንገድ ስንጀምር፣ ንስሃ እንገባለን፣ ምህረቱን እንቀበላለን፣ እናም እርሱም ነፍሳችንን ያነሳል።
ወደ አብ ስንጠጋ እኛን ለመርዳት፣ የሚከተለውን ቃል ገባልን፤ “እያንዳንዱ ነፍስ ሃጢያቶቹን ጥሎ ወደ እኔ የሚመጣ፣ እናም ስሜንም የሚጠራ፣ ድምጼንም የሚታዘዝ፣ እናም ትእዛዛቴንም የሚጠብቅ፣ ፊቴን ያያል እናም እኔ መሆኔን ያውቃል።”11
በእርሱ የቤዛነት ማስተስሪያ ላይ ባለን እምነት አማካኝነት፣ ጌታ ያነጻናል፣ ይፈውሰናል፣ እናም እሱን በመምሰልእንድናውቀው ያስችለናል። ሞርሞን እንዳስተማረው፣ “በሃይል ከልባችሁ ወደ አብ ጸልዩ፤ የእግዚአብሄር ልጅ ትሆኑ ዘንድ፣ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ እንደ እርሱ ፍጹም እንደሆነ እኛም ፍጹማን እንሆናለንና።”12 እኛም እንደ አምላክ ለመሆን ስንጥር፣ እርሱም እኛ ለዘላለም ለራሳችን ማድረግ ከምችለው በላይ ማድረግ ይችላሉ
አማካሪ ሰዎችን በመከተል እርሱን እወቅ
በጥረታችን ላይ ይረዳን ዘንድ፣ እግዚአብሔር ለእኛ አርዓያ የሚሆኑ እና አማካሪዎች ሰጥቶናል። ለእኔ ከሆኑት መካከል ስለ አንዱ ያለኝን ስሜት ላካፍላችሁ፣ እኚህም የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ኒል ኤ ማክስዌል ናቸው። እርሱ እንደ አምላክ ለመሆን ባለው ጥረት ውስጥ ከራሱ ፈቃድ ይልቅ የአብን ፈቃድ ዘወትር ፈለገ።
ከሃያ አመታት በላይ በፊት፣ የካንሰር ህመም እንዳለበት ከታወቀ በኋላ ያለውን ስሜት አካፈለኝ። እንዲህም አለኝ፣ “በመጋረጃው በዚህም በኩል ሆነ ወይም በዚያ በኩል በቡድኑ ላይ መሆን እፉልጋለሁ።” በተመልካች ቦታ ላይ መቀመጥ አልፈልግም። ጨዋታው ላይ መጫወት እፈልጋለሁ።”13
ለሚቀጥሉት ቀጣይ ሳምንታት፣ አምላክ እንዲፈውሰው ለመጠየቅ ቸላ አለ፤ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ብቻ ለማከናወን ነው የፈለገው። የሱም ባለቤት ኮሊን፣ እንዳመለከተችው፣ በጌተ ሰማኒ ውስጥ የኢየሱስ የመጀመሪያ ለቅሶ፣ “ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ” የሚለው ነበር። ከዚያም ቀጥሎ አዳኝ እንዲህ ነው ያለው፣ “ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን።”14 ሽማግሌ ማክስዌል ያዳኝን ምሳሌ ተከትለው፣ እፎይታን እንዲጠይቁ፣ እናም ከዛን ፍቃዳቸውን ለአምላክ አሳልፈው እንዲሰጡ መከረች፣ እሳቸውም እንዲሁ አደረጉ።15
ለአንድ ዓመት ያህል ሰፊ የሆነ፣ አቅም ከሚያሳጣ ሕክምና በኋላ፣ እርሳቸው በፍጹምና በሙሉ ወደ ቀድሞው “ጨዋታቸው ላይ ተመለሱ።” ለሰባት ተጨማሪ አመታት አገለገሉ።
በእነዚያ በቀጣይ ዓመታት ከእርሳቸው ጋር በርካታ አላፊነት ነበረኝ። የእርሱ ደግነት፣ ርህራሄ፣ እና ፍቅር ተሰማኝ። በቀጣዩ ህመማቸውና አገልግሎታቸው፣ እንደ አዳኝ ለመምሰል ባላቸው ጥረት ተጨማሪ መንፈሳዊ ማሻሻያ ሲቀበሉ ተመልክቻለሁ።
ለሁሉም የሚገኘው፣ የመጨረሻው ምሳሌ እና አስተማሪ፣ እንዲህ ያለው ጌታችን እና አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፥ “እኔ መንገድና እውነት ህይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”16 “ኑ ተከተሉኝ።”17
ወጣት ወንድሞቼና እህቶቼ፣ አምላክን ማወቅ የህይወት ዘመን ጥረት ነው። “እናም ይህ እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ” [እኛ] እንድናውቅ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”18
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ ተልእኮ ላይ መሳተፍ አይኖርብንም? … ድፍረት፣ [የእኔ ወጣት ጓደኞች]፤ ወደ ላይ፣ ወደ ድል እንሂድ!”19
እግዚአብሔር እናንተን ያውቃል እናም እናንተእርሱን ታውቁ ዘንድ ይጋብዛል። ቅዱስ መጻህፍትን አጥኑ፣ ወደ አብ ጸልዩ፣ የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ ፈልጉ፣ እንደ አዳኝ ለመሆን ጣሩ፤ ጻድቅ አማካሪን ተከተሉ። ይህንን ስታደርጉ፣ እናንተ እግዚአብሄርንና ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማወቅ ትመጣላችሁም የዘላለም ህይወትንም ትወርሳላችሁ። ይህም ከእነርሱ ወገን የተሾምኩ ልዩ መስካሪ እንደመሆኔ መጠን፣ ለአንተ የምሰጠው ግብዣ ነው። ህያው ናቸው። ያፈቅሯችኋል። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።