ዙሪያችሁን አትመልከቱ፣ ወደ ላይ ተመልከቱ!
ሌሎችን ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መጋበዝ እቅዳችን ነው፣ እናም ይህን እቅድ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በመመልከት ለማሟላት እንችላለን።
አላማዬ “ሌሎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መጋበዝ” ነው።1 ይህ የናንተም አላማ ነው። ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በማተኮር ይህን ዓላማ መፈጸም እንችላለን።
የ16 ዓመት ልጅ ሳለሁ ከወላጆቼ ጋር ተጠመኩኝ። ወጣት ወንድሜ፣ ክዩንግ-ህዋን፣ የ14 አመቱ በሆነ ጊዜ፣ በአጎቴ፣ ያንግ ጅክ ሊ፣ አማካኝነት ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቀለ እናም ወደሱ ቤተክርስቲያን ጋበዘን። በቤተሰባችን ውስጥ አስሩም አባላት እያንዳንዱ የተለያየ ቤተክርስቲያን ነበረን፣ ስለዚህም እውነቱን በማግኘታችን ተደሰትን እናም ከተጠመቅን በኋላ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ የሚገኘውን ደስታ ለማካፈል ፈለግን።
አባቴ ለመማር እና እውነትን ለመካፈል ከእኛ መካከል አብልጦ ተደስቶ ነበር። በየቀኑ ከሁለት ሰዓታት በላይ ቅዱስ መጻህፍትን ለማጥናት በማለዳ ከእንቅልፉ ይነሳ ነበር። ከሥራ በኋላ በየቀኑ የእኛ ቤተሰብን፣ ጓደኞችን፣ ጎረቤቶችን ለመጎብኘት ከሚስዮናውያን ጋር ይሄድ ነበር። ከተጠመቅን ሰባት ወራት በኋላ ከቤተሰቦቼ እና ከዘመዶቻችን መካከል 23ቱ የቤተክርስቲያን አባላት ሆኑ። ይህም አባቴ በአባል የሚስዮናዊ ሥራው አማካኝነት በቀጣዩ ዓመት ውስጥ የተጠመቁ 130 ሰዎች የማየት ተአምርን ተከትሎ ነበር።
ለእርሱ የቤተሰብ ታሪክ በጣም አስፈላጊ ነበር፣ የዘራችንን ስምንት ትውልዶች ሞልቶ ጨረሰ። ከዚያም ወቅት ጀምሮ፣ የቤተሰባችን የመለወጥ ፍሬ፣ በ14 አመቱ ወንድሜ የጀመረው፣ በህይወት ብቻ ላሉት ሳይሆን ለሞቱትም ከቁጥር በላይ እየጨመረ ሄደ። በአባቴ እና በሌሎች ሥራ ላይ በመገንባት፣ የቤተሰብ የዘር ሃረግ አሁን እስከ 32 ትውልድ ይዘልቃል፤ እና አሁን ለብዙ ቅርንጫፎች የቤተ መቅደስ ስራን በማጠናቀቅ ላይ ነን። ዛሬ እኔ ትውልዶቻችንን እና የዘሮቻችንን በማገናኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል።
ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ ሒንክሊ በኮሎምበስ ኦሃዮ ቤተመቅደስ ውስጥ ተመሳሳይ ተሞክሮን መዝግበው ነበር፥
“በቤተመቅደስ ውስጥ ተቀምጬ ሳለ [የእኔ ቅድመ-አያቴ፣ አያት፣ እና አባት] ሕይወት ላይ በማሰላሰል፣ የእኔ ሴት ልጅ ላይ፣ ... የሷ ልጆቿ ላይ፣ የእኔ የቅድመ የልጅ ልጆቿ ላይ ተመለከትኩኝ። ከእነዚህ ሰባት ትውልዶች፣ ሦስት ከእኔ በኋላ እና ሦስት ከእኔ በፊት መካከል ላይ መቆሜን በድንገት ተገነዘብኩኝ።
“በዛም በቅዱስ እና በጸደቀ ቤት ውስጥ በአይምሮዬ ውስጥ ከእኔ በፊት ካሉት ትውልድ የተቀበልኩትን ውርስ ለቀጣዩ ትውልድ የማሳለፍ ከፍተኛ የግዴታ ስሜት ተሰማኝ።”2
ሁላችንም በዘላለማዊ ቤተሰብ መካከል ላይ ነው ያለነው። የኛ ሚና አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ለውጥን የሚያመጣ ከፍተኛ ተጽእኖ ሊሆን ይችላል። ፕሬዘደንት ሒንክሊም ሲቀጥሉ “በፍጹም በእናንተ ትውልዶች ሰንሰለት ውስጥ ደካማ አቋራኝ አትሁኑ።”3 በወንጌል ውስጥ የእናንተ ታማኝነት ቤተሰባችሁን ያጠናክራል። ታዲያ እኛስ በዘላለማዊ ቤተሰባችን ውስጥ ጠንካራ አቋራኝ መሆናችንን ማረጋገጥ የምንችለው እንዴት ነው?
አንድ ቀን፣ ከጥምቀቴ ጥቂት ወራት በኋላ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ እርስ በርስ ሲነቃቀፉ የተወሰኑ አባላትን ሰማሁ። በጣም ቅሬታ ተሰማኝ። ወደ ቤት ሄድኩና ምናልባት እኔ ከአሁን በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ እንደሌለብኝ አባቴን ነገርኩት። አባላት በዚህ መልኩ ሌሎች ሰዎችን ሲተቹ ማየት አስቸጋሪ ነበር። ከሰማሁ በኋላ፣ አባቴ ወንጌል መመለሱን እና ፍጹም እንደሆነ አስተማረኝ ነገር ግን ምእመናኑ፣ እሱም ቢሂን እኔንም ጨምሮ ገና ፍሱማን አይደሉም። እሱም በጥብቅ እንዲህ አለ፣ “ባንተ ዙሪያ ባሉት ሰዎች አማካኝነት እምነትህን አትጣ፣ ነገር ግን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ጠንካራ ዝምድናን ገንባ። ዙሪያችሁን አትመልከቱ፣ ወደ ላይ ተመልከቱ!
ወደላይ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከት የሚለው ጥበበኛው የአባቴ ምክር ፈተናዎችን በምጋፈጥበት ጊዜ እምነቴን ያጠናክራል።። የሱን ቃላት እንደምናነበው፣ የክርስቶስን ትምህርቶች እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደምቻል አስተምሮኛል። “በሁሉም አስተሳሰባችሁ ወደ እኔ ተመልከቱ፣ አትጠራጠሩም፣ አትፍሩም።”4
በዋሺንግተን የሲያትል ሚስዮንን በማስተዳድርበት ጊዜ፣ በዓመት ውስጥ ካሉት ቀናት ብዙ ጊዜ ይዘንብ ነበር። ያም ሆኖ፣ የእኛ ሚስዮናውያን በዝናብ ውስጥ ወጥተው እንዲሰብኩ መመሪያ ተሰጥቷቸው ነበር። “በዝናብ ውስጥ ውጡ፣ ወደ ሰማይ ተመልከቱ፣ አፋቸውን በመክፈት ዝናቡን ጠጡት!” እላቸው ነበር። ወደላይ ስትመለከቱ፣ ምንም ያለ ፍርሃት ለሁሉም ሰው አፋችሁን ለመክፈት ብርታት ታገኛላችሁ።” ከወንጌል አገልግሎታቸው እንኳ በኋላ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሲገጥማቸው ወደላይ መመልከት እንዲችሉ ምሳሌያዊ ትምህርት ነበር። እባካችሁ በተበከለ አካባቢዎች ይህን አትሞክሩ።
አሁንም የሲያትል ተልዕኮ ውስጥ በማገልገል ላይ ሳለሁ፣ የፒያኖ ተጫዋች የሆነው የበኵር ልጄ፣ ሰንቢም፣ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። እሱም የዓለም አቀፍ ውድድር በማሸነፉ ምክንያት፣ በኒው ዮርክ ውስጥ በካርኒጌ አዳራሽ የማከናወን እድል እንደሚኖረው ተናገረ። እኛም ለእርሱ በጣም ተደስተኞች ነበርን። ሆኖም ግን፣ በዛ ምሽት፣ በምስጋና ጸሎት ላይ እያለች፣ ባለቤቴ በሱ ዝግጅት ላይ መገኘት እንደማንችል ተገነዘበች እናም ለሰማይ አባት እንዲህ አለች፥ “የሰማይ አባት ሆይ፣ ለሰንቢም ስለሰጠሀው በረከት አመስጋኝ ነኝ። በነገራችን ላይ፣ እዛ መሄድ ባለመቻሌ አዝናለሁ። ይህን በረከት ከዚህ የሚስዮን አገልግሎት በፊት ወይም በኋላ ሰተክቢሆን ኖሮ መሄድ እችል ነበር አለች። ማጉረምረሜ ሳይሆን፣ ትንሽ የሃዘን ስሜት ስለተሰማኝ ነው” አለች።
እሷም ይህንን ጸሎት እንደጨረሰች፣ ግልጽ የሆነ ድምፅ ሰማች፥ “መሄድ ባለመቻልሽ ምክንያት ልጅሽ ይህን እድል ተሰጥቶታል። ከዚህ ይልቅ መቀየር ትፈልጊያለሽን?”
ባለቤቴ በጣም ተገረመች። እሷም ልጆች በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ በወላጆቻቸው ታማኝ ሥራ አማካኝነት እንደሚባረኩ አወቀች፣ ነገር ግን በእንደዚህ ዓይነት ግልጽነት የነበራትን ሚና ስትረዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። እሷም ወዲያውኑ ወደ እርሱ መለሰችለት፥ “አይ፣ አይ፣ የእኔ ያለመሄዴ ለመልካም እርሱ ያንን ክብር ያግኝ” አለች።
ውድ ወንድሞችና እህቶች፣ በጊዜያዊ ዓይናችን ዙሪያችንን ከተመለከትን የሰማይ አባትን ፍቅር ለማወቅ ቀላል አይሆንም። ምክንያቱም መጀመሪያ የሚታየን አለመመቸት፣ ማጣት፣ ሸክም፣ ወይም ብቸኝነት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ፣ እኛም ቀና በምንልበት ጊዜ በረከቶችን አርቀን ማየት እንችላለን። ጌታ እንደገለጸው፣ “ከእግዚአብሔር ማንኛውንም በረከት ስንቀበል፣ በዛ ህግ ላይ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ በመታዘዝ ነው።”5 በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ለሚሳተፉ ሁላ፣ ከእናንተ በፊት እና በኋላ ላሉ ትውልዶች ለታላቅ በረከታቸው ጠንካራ አቆራኝ እንደሆናችሁ እወቁ።
ዛሬ፣ ብዙ የቤተሰባችን አባላት በቃል ኪዳን መንገድ ላይ ታማኝ በመሆናቸው አመስጋኝ ነኝ እና ከእኛ ቀጥሎ ባዶ መቀመጫዎችን ሳስብ ቅር ይለኛል። ሽማግሌ ኤም. ራስል ባለርድ እንዲህ አሉ፥ እናንተ ተሳታፊ ላለመሆን ወይም በዳግም የተመለሰውን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ለመለየት ከመረጣችሁ፣ ወዴትስ ትሄዳላችሁ? ምንስ ታደርጋላችሁ? ከቤተክርስቲያን አባላት እና በጌታ ከተመረጡ መሪዎች ጋር ‘ከእንግዲህ ወዲህ አብሮ ላለመራመድ’ መወሰን ሁልጊዜ በጊዜው ሊታይ የማይችል ነገር ግን የረጅም ጊዜ ተፅዕኖ ይኖረዋል።”6 ፕሬዝደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን እንደመከሩን፣ “ቀላል የሆነ ስተትን ከመምረጥ ይልቅ ከባድ የሆነ ሃቅን እንምረጥ።”7
ኢየሱስ ክርስቶስን ለመመልከት መቼም ዘግይቶ አያውቅም። እጆቹ ሁልጊዜ ክፍት ናቸው። ከእኛ በፊት እና በኋላ ያሉ የአምላክ ዘላለማዊ ቤተሰብ ለመሆን፣ ክርስቶስን እንድንከተል በእኛ ላይ ሃላፊነትን የጣሉ ትውልዶች አሉ።
እኔ ከካስማ ፕሬዘደንትነት ጥሪዬ ስሰናበት፣ ልጆቼ ከእኔ ጋር ተጨማሪ ጊዜ ለማሳለፍ በጣም ተደስተው ነበር። ከሦስት ሳምንት በኋላ እኔ ከሰባዎቹ እንዱ እንድሆን ተጠራሁ። መጀመሪያ ላይ እነርሱ ሊከፋቸው ይችላል ብዬ አሰብኩ፣ ነገር ግን የእኔ ታናሽ ወንድ ልጅ የትሑት ምላሹ፣ “አባዬ፣ አትጨነቅ። እኛ የዘላለም ቤተሰብ ነን” የሚል ነበር። ምን አይነት ቀላል እና ግልጽ እውነት ነበር! በዚህ ሟች ህይወት ላይ ብቻ በመመልከቴ፣ እኔ ትንሽ ተጨንቄ ነበር፣ ነገር ግን ልጄ ደስተኛ ነበር ምክንያቱም አካባቢውን ሳይሆን ወደ ዘላለምና ወደ ጌታ እቅድ ቀና ብሎ ተመለከተ።
ወላጆችህ ወንጌልን በሚቃወሙበት ጊዜ፣ የትንሽ ቤተክርስቲያን ምእመን መሆን፣ ባለቤታችሁ አባል ሳይሆን፣ ለማግባት ብትጥሩም ያላገባችሁ ስትሆኑ፣ ልጃችሁ ከመንገድ ሲወጣ፣ ብቸኛ ወላጅ ሆናችሁ እራሳችሁን ስታገኙ፣ በአካል ወይም በስሜት ችግር ካለባችሁ፣ ወይም በአደጋ ጊዜ ሰለባ ስትሆኑ እናም እንዲ በመሳሰሉ ጊዜ ቀና ብሎ መመልከት ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። በነዚያ አስቸጋሪ ጊዜያት ላይ ያለችሁን እምነት አጥብቃችሁ ያዙ። ጥንካሬን፣ ሚዛንን፣ እና ፈውስን ለማግኘት ወደ ክርስቶስ ተመልከቱ። በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ኃይል አማካኝነት “ሁሉም ነገሮች ለናንተው መልካምነት ይሰራሉ።”8
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝአችን እና ቤዛችን መሆኑን እመሰክራለሁ። ሕያው ነቢይ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰንን በምንከተልበት ጊዜ ወደ ክርስቶስ እየተመለከትን ነው። በየቀኑ ስንጸልይ እና ቅዱሳት መጻህፍትን ስናጠና እና በየሳምንቱ ቁርባንን ከልብ ስንካፈል፣ ሁልጌዜ ወደሱ ለመመልከት እንችል ዘንድ ጥንካሬን እናገኛለን። የዚህ ቤተክርስቲያን አባል በመሆኔ እንዲሁም የዘላለም ቤተሰብ አካል በመሆኔ ደስተኛ ነኝ። ከሌሎች ጋር ይህን ታላቅ ወንጌል ማካፈል እወዳለሁ። ሌሎችን ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ መጋበዝ እቅዳችን ነው፣ እናም ይህን እቅድ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በመመልከት ለማሟላት እንችላለን። ስለዚህ በትህትና የምመሰክረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።