2010–2019 (እ.አ.አ)
ለስራው ተጠርታችኋል
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


16:13

ለስራው ተጠርታችኋል

በአንድ ቦታ ለማገልገል መመደብ አስፈላጊ ነው ነገር ግን ለመስራት ከመጠራት ጋር ሲመዛዘን ሁለተኛ ጉዳይ ነው።

ፕሬዘደንት ሞንሰን፣ ድምፅዎን ስለሰማን እና መመሪያዎች ስለተቀበልን በጣም ተደስተናል። እንወዶታለን እና እንደግፎታለን፣ እናም ለእርስዎ ዘወትር እንጸልያለን።

ታላቅ የሆነውን ወንጌልን ለእያንድንዱ አገር፣ ነገድ፣ ቋንቋ፣ እና ህዝብ ከመስበክ ጋር የተያያዙ መመሪያዎችን አብረን ስንመለከት የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ አብሮን እንዲሆን ጸሎቴ ነው።1

ለማገልገል መጠራት እና ለመስራት መመደብ

በየአመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ወንዶችና ሴቶች እናም ብዙ አዛውንት ጥንዶች ከሶልት ሌክ ሲቲ የሚመጣውን ልዩ ደብዳቤ ለመቀበል በጉጉት ይጠባበቃሉ። የደብዳቤውም ይዘት የተላከለትን ሰው፣ እንዲሁም የቤተሰቡን አባላት እናም ብዙ ሌሎች ሰዎች ላይ እስከመጨረሻ ተጽዕኖ ያደርጋል። በሚደርስበትም ጌዜ፣ ደብዳቤው በጥንቃቄ እና በትግስት ሊከፈት ወይም ከደስታ እና ከታላቅ ፍጠነት ብዛት ሊገነጣጠል ይችላል። ይህንን ልዩ ደብዳቤ ማንበብ ፈጽሞ ሊረሳ የማይገባ ተሞክሮ ነው።

ደብድቤው በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ፕሬዝደንት የተፈረመ ነው፣ እናም የመጀመሪያው ሁለት አረፍተ ነገሮ እንዲህ ይላሉ፥ “የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሚስዮናዊ ሆነህ እንድታጋለግል ተጠርተሃል። በ ______ የሚሲዮን ክልል ውስጥ እንድትተጋ ተመድበሃል።”

እባካችሁ አስታውሱ የመጀመሪያው አረፍተ ነገር ተመልሶ በተቋቋመው የጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ የሙሉ ጌዜ ሚሲዮናዊ ሆኖ የማገልገል ጥሪ ነው። ሁለተኛው አረፍተ ነገር በተወሰነ ቦታ እና የአገልግሎት አካባቢ እንደሚያገለግሉ ያሳያል። በነዚህ ሁለት አረፍተ ነገሮች ውስጥ ያለውን ልዩነት መረዳት ለሁላችንም ጠቃሚው ነው።

በቤተክርስቲያኗ ባህል፣ አብዛኛውን ጊዜ ወደ አርጀንቲና፣ ፖላንድ፣ ኮሪያ ወይም አሜሪካ የመሳሰሉት አገራት ሄዶ ስለማገልገል እናወራለን። ነገር ግን አንድ ሚስዮናዊ ወደ አንድ ቦታ እንዲሄድ ሳይሆን የሚጠራው ነገር ግን እሱ ወይም እሷ እንዲያጋለግሉ ነው። Aበ1829 (እ.ኤ.አ) ጌታ ለነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳወጀው፣ “ጌታን ለማገልገል ፍላጎት ካለህ ለስራው ተጠርተሃል።”2

እያንዳንዱ የሚስዮን ጥሪ እና ምደባ፣ ወይም ድግሞ የሚመደቡትም፣ ለጌታ አገልጋዮች የተሰጠ ራእይ ውጤት ነው። የስራው ጥሪ ደግሞ የሚመጣው ከቤተ ክርስቲያኗ ፕሬዝዳንት ነው። ከ 400 በላይ ከሆኑት በአለም ዙሪያ በስራ ላይ እየዋሉ ካሉ የወንጌል ተልእኮ ክልሎች አንዱ ውስጥ ምደባ የሚመጣው ከእግዚአብሄር በህይወት ባለ ነብይ ስልጣን በተሰጣቸው አስራ ሁለቱ ሐዋሪያት አማካኛነት ነው። በሁሉም የተልዕኮ ጥሪዎች እና ሃላፊነቶች ላይ የትንቢት እና የመገለጥ መንፈሳዊ ስጦታዎች ይገኛሉ።

በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል 80፣ በ1832 (እ.አ.አ) ውስጥ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለስቲፈን በርኔት ስለሰጠው የሚሲዮን ጥሪ መዝገብ የያዘ ነው። ይህንን ለወንድም በርነት ስለተሰጠው ጥሪ ማጥናት (1) እንደ ሚስዮናዊ “ለስራው መጠራት” እና በተወሰነ ክልል “ተግቶ ለመስራት መመድብን” በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽነት እንድንረዳ ያስችለናል እናም (2) የግላችንና የመለኮታዊ ጥሪ የሆነውን ወንጌልን የማወጅ ሃላፊነት በሙሉነት እንድናደንቅ ያግዘናል።

የዚህ ክፍል ቁጥር 1 ስለ ማገልገል ጥሪ ነው፥ “እውነት, እንዲሁ አንተ አገልጋዬ ስቲፈን በርኔት፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ ሂድ፣ አንተም ወደ ዓለም ሂድህ በድምፅህ ስር ለሚመጣ ፍጥረት ሁሉ ወንጌልንም ሁሉ ስበክ”3

የሚገርመው ነገር፣ ቁጥር 2 ወንድም በርኔት ስለተመደበለት የሚስዮናዊ ጓደኛው ያስረዳል፥ “የሚስዮናዊ ጓደኛ እንደፈለክ ሁሉ እኔ ባሪያዬን ዔደን ስሚዝን እሰጥሃለሁ።”4

እነዚህ ሁለት ሚስዮናውያን በትጋት የት እንደሚሰሩ ቁጥር 3 ይጠቁማል፥ “ስለዚህም፣ በስተ ሰሜን ወይም በስተ ደቡብ, በስተ ምሥራቅ ወይም በስተ ምዕራብ ቢሆን፣ የእኔን ወንጌል ለመስበክ ሂድ፣ ምንም ልዩነት የለውም እናም ብኩን አትሆኑም።”5

በዚህ ጥቅስ ላይ፣ “ምንም ልዩነት የለውም” የሚለው ሐረግ ጌታ አገልጋዮቹ የት እንደሚሰሩ ግድ የማይሰጠው እንደሆነ ያሳያል ብዬ አላምንም። እንዲያውም እርሱ በጥልቅ ይገደዋል። ነገር ግን ወንጌል የመስበኩ ሥራ የጌታ ሥራ ስለሆነ እርሱ ስልጣን የተሰጣቸውን አገልጋዮች ያነሳሳል እናም ይመራል። ሚስዮናውያን በተቻላቸው መጠን ብቁ እና በእርሱ እጁ ውስጥ ጠቃሚ መሳሪያ በመሆን፣ ከዚያም በተቻላቸው መጠን በታማኝነት ሃላፊነታቸውን ከተወጡ፣ ከዚያም በእርሱ እርዳታ “ብኩን አትሆኑም።” ምናልባትም አዳኝ በዚህ ራእይ ውስጥ እያስተማረን ያለው ትምህርት አንዱ፣ በተወሰነ ቦታ ላይ ተመድቦ ማገልገል አስፈላጊ እና ጠቃሚ ቢሆንም ነገር ግን የአገልግሎት ጥሪውን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው።

የሚቀጥለው ጥቅስ ለሁሉም ሚስዮናውያን አስፈላጊ የሆኑትን ቅድመ ሁኔታዎችን አጉልቶ ያሳያል፥ “ስለሆነም፣ የሰማችኋቸውን፣ እናም በእውነቱ ያመናችኋቸውን፣ እናም እውነት መሆናቸውን የምታውቁትን6 አውጁ።

የመጨረሻው ቁጥር ውንድም በርነትን እና ሁላችንንም በእውነት የማገልገል ጥሪ ከየት እንደሚመጣ ያስታውሰናል። “እነሆ፣ ይህ የአዳኛችሁና የጠራችሁ እንዲሁም የእየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ነው። አሜን።”7

አለመግባባትን ማሸነፍ

አንዳንዶቻችሁ በአጠቃላይ የክህነት ጉባኤ ላይ ለምን ተጠርቶ ስለመስራት እና ለመትጋት ስለመመደብን ግልጽ ልዩነት ያላቸንው ነገሮች ለምን ለመወያየት እንደመረጥኩኝ ይሆናል። ለእናንተ ያለኝ መልስ ቀጥተኛ ነው፥ ያለኝ ተሞክሮ እነዚህ መመሪያዎች በብዙ የቤት ክርስቲያን አባላት በተገቢው ሁኔታ አልገባቸውም።

ይህንን ጉዳይ ለማድረስ የፈለኩበት ብቸኛውና ታላቁ ምክንያቴ በተለያዩ ምክንያቶች የአገልግሎት ጥሪያቸው የተቀየረባቸው ሚስዮናውያንን የተሰማቸውን የስጋት፣ ጭንቀት እና እንዲሁም የጥፋተኝነት ስሜት ስለተማርኩኝ ነው። በአካል ጉዳት እና አደጋዎች፣ የቪዛ መዘግየት እና ለማግኘትም ባለው ውጣ ውረድ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ አዲስ ተልእኮዎችን መፍጠር እና በሰው ሃይል መሙላት፣ ወይም ወንጌልን በአለም ዙሪያ ለማወጅ ተቀያያሪ እና የማያቋርጡ ተለዋዋጭ ፍላጎቶች በሚመጡ ክስተቶች እና በሁኔታዎች እንደዚህ ያሉ የአገልግሎት ቅያሬዎች አንዳንድ ጊዜ በጣም አስፈላጊ ናቸው።8

አንድ ሚስዮናዊ በተለየ አካባቢ እንዲሰራ ሲመደብ፣ ሂደቱ በትክክል ከመጀመሪያው ምደባ ጋር ተመሳሳይ ነው። የአሥራ ሁለቱ ቡድን አባላት እንዲህ ያሉ ቅያሬዎችን ሲያደርጉ የመንፈስ መነሳሳት እና ምሪትን ይሻሉ።

በቅርቡ ከእኔ ጋር የልቡን ጥልቅ ስሜት ካጋራኝ አንድ ታማኝ ሰው ጋር ተነጋግሬ ነበር። በስብሰባ ላይ ለስራ ስለመጠራትና ለመትጋት በመመደብ መካከል ያለውን ልዩነት ገልጬ ነበር። ይህ ጥሩ ወንድም እጄን በመጨበጥ እና እንባ በሞሉት ዓይኖቹ እንዲህ አለኝ፣ “ዛሬ እንድማር የረዱኝ ነገሮች ከሰላሳ አመታት በላይ በትከሻዬ ላይ የተሸከምኳቸውን ሸክሞች አንስተውልኛል። ወጣት ሚስዮናዊ እያለሁ የእኔ የመጀመሪያ ምደባ በደቡብ አሜሪካ ውስጥ ተግቼ እንድሰራ ነበር። ነገር ግን ቪዛ ማግኘት ሳልችል ስቀር የእኔ ምድብ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተቀየረ። ለዚህ ሁሉ አመታት ለምን የተጠራሁበት ቦታ ላይ ማገልገል አልቻልኩም ብዬ አስብ ነበር። አሁን እኔ ሥራ እንድሰራ እንጂ የተጠራሁት ወደ አንድ አካባቢ እንድሄድ እንዳልሆነ አወኩኝ። እኔ ይህን መረዳቴ ምን ያህል እንደረዳኝ ልገልጽሎት አልችልም።”

ልቤ ለዚህ ጥሩ ሰው ተነካ። በመላው ዓለም እነዚህን መሠረታዊ መርሆዎች ሳስተምር፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ግለሰቦች ወደ እኔ በግል መተው ተመሳሳይ ስሜትን ልክ እንደገለጽኩት ሰውዬ አስቀምጠዋል። እኔ ዛሬ በዚህ ጉዳይ ስናገር፣ አንድ እንኳ የቤተ ክርስቲያን አባል የማያስፈልጉ አለመግባባትን, አለመረጋጋትን, ጭንቀትን, ወይም የጥፋተኝነት ስሜትን ሊሸከም ስለማይገባ ነው።

“ስለዚህም፣ በስተ ሰሜን ወይም በስተ ደቡብ, በስተ ምሥራቅ ወይም በስተ ምዕራብ ቢሆን፣ የእኔን ወንጌል ለመስበክ ሂድ፣ ምንም ልዩነት የለውም እናም ብኩን አትሆኑም።”9 የዚህን ጥቅስ ቃል ስታስቡና ልባችሁን ስትከፍቱ፣ መንፈስ ቅዱስን እንድትጋብዙትና የሚያስፈልጋችሁን መረዳት፣ ፈውስ እና መመለስ ወደ ልባችሁ እንዲያመጣ ጸሎቴ ነው።

ይህን ርዕስ ለመወያየት አብዝቶ የተሰማኝ አንድ ተጨማሪ ምክንያት ቢኖር፣ ለብዙ ዓመታት ሚስዮናውያን የመመደብ የግል ተሞክሮ ስላለኝ ነው። ለእኛ ለአስራሁለቱ፣ ሚስዮናውያንን በየራሳቸው መስኮች ለመመደብ የእኛን ኃላፊነት ለመወጣት የጌታን ፈቃድ መረዳት ቀጣይ የሆነውን የኋለኛው ቀን መገለጥ እውነታነት ከዚህ በላይ የሚያረጋግጥ ነገር የለም። አዳኝ እያንዳንዳችንን አንድ በአንድ እና በስም እንደሚያውቀን እና እንደሚያስብልን እመሰክራለሁ።

ለስራው ለመጠራት መዘጋጀት

አሁን በአጭሩ መሠረታዊ ነገር ግን በተደጋጋሚ በቸልታ የሚታለፍን ለሥራው ጥሪ የመዘጋጀትን ገጽታ መወያየት እንፈልጋለን።

ሦስት የተቆራኙ ቃላት የእግዚአብሔር ልጆች ዝግጅት እና የዕድገት መንገድ ይገልጻሉ፤ እነዚህም ክህነት፣ ቤተ መቅደስ፣ የወንጌል ተልዕኮ ናቸው። ክህነት፣ ቤተመቅደስ፣ ሚስዮን። አንዳንድ ጊዜ እንደ ወላጆች፣ ጓደኞች፣ እና የቤተ ክርስቲያን አባላት የወጣት ወንዶችን የሚስዮናዊ ዝግጅት ላይ በጣም ትኩረት አድርገን ሌሎች አስፈላጊ እርምጃዎችን የቃል ኪዳን የመተላለፍያ መንገድ የሆኑትን የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ከመጀመሩ በፊት መሟላት ያለባቸውን ነገሮች በተወሰነ መንገድ ችላ እንላለን። እንደ ሚስዮናዊ ማገልገል በእርግጥ የህይወት ዘመን መንፈሳዊ እድገት እና አገልግሎትን በመፍጠር ሂደት ላይ ጥንካራ መሰረትን ለመፍጠር አንዱ ጠቃሚ መገንቢያምሰሶ እንጂ ብቸኛው አይደለም። ክህነት እና የቤተ መቅደስ በረከቶች ወደ ማገልገያ ክልል ከመሄድ አስቀድመው የሚመጡት በህይወታችን ሁሉ በመንፈስ እኛን ለማበርታት እና ለማጠንከር አስፈላጊዎች ናቸው።

ውጣት ወንዶች፣ የአሮን ወይም ትንሹን የክህነት ስልጣን ሃላፊነታችሁን ስታሟሉ እና ስታከብሩ የመልከጸዲቅን ወይም የከፍተኛውን የክህነት ስልጣን መሀላና ቃልኪዳን ለመቀበል እና ላማጉላት እየተዛጋጃሁ ነው።10 ከፍተኛ ክህነትን ለመቀበል የግል ብቁነት ከሁሉም በላይ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነው። እራስን ትቶ የዕድሜ ዘመን የክህነት አገልግሎትን መስጠት ከፊታችሁ ይገኛል። በተደጋጋሚ ትርጉም ያለው አገልግሎት ለመስጠት አሁን ተዘጋጁ። እባካችሁ ብቁ መሆንን እና እንደዛ ሆኖ ለመቅረት መውደድን ተማሩ። ብቁ ሁኑ። ብቁ ሆናችሁ ቀጥሉ።

የመልከጸዲቅ ክህነትን እና የአገልግሎትን ጥሪ ከተቀበለ በኋላ፣ አንድ ወጣት11 በቤተ መቅደስ ቃልኪዳኖችና ስነስራቶች ሂደት ላይ በሃይል ሊታጠቅ ይችላል። ወደ ቤተ መቅደስ መሄድና የቤተ መቅደስ መንፈስ በውስጣችሁ መሄዱ ውጤታማ የሆነ የሙሉ ጊዜ የሚስዮናዊ አገልግሎትን ይቀድማል። ለእናንተ ወጣት ወንዶች እና የቤተ ክርስቲያን አባላት የግል ብቁነት የቤተ መቅደስን በረከቶች ለመቀበል ብቸኛው በጣም ጠቃሚ ቅድመ ሁኔታ ነው። ልክ እንደ የወንጌል መስፈርቶች መሠረት ስትኖሩ፣ በጌታ ቤት ውስጥ መግባት ትችላላችሁ እና በመላው በአሥራዎቹ እድሜዎቻችሁ ቅዱስ የሆነውን ስነ ስራቶች ላይ ትሳተፋላችሁ። ስለ ቤተ መቅደስ ስነ ስርአቶች ያላችሁ ፍቅር እና መረዳት ይጠነክራል እናም በዘመናችሁም ይባርካችኋል። እባካችሁ ብቁ መሆንን እና እንደዛ ሆኖ ለመቅረት መውደድን ተማሩ። ብቁ ሁኑ። ብቁ ሆናችሁ ቀጥሉ።

ብዙ ወጣት ወንዶች እና ወጣት ሴቶች ውስን-ፍቃድ ያለውን የቤተ መቅደስ መግቢያ ፍቃድ አላቸው። እንደ የአሮን የክህነት ስልጣን ተሸካሚ የራሳችሁን ቤተሰብ ስም በመፈለግ እና ጥምቀትና ማረጋገጫን ለቤተሰብ አባላቶቻችሁ በቤተ መቅደስ ውስጥ እያከናወናችሁ ነው። የቤተ መቅደስ መግቢያ ፍቃድን ውቅታዊ አድርጎ መጠበቅ የእናንተን ብቁነት ያሳያል እናም ሌሎችን በቤተ መቅደስ ማገልገል ለመልከጽዲቅ ክህነት ለመዘጋጀት ጠቃሚ የሆነ አካል ነው።

ወጣት ወንዶች፣ እያንዳንዳችሁ በአሁኑ ጊዜ ሚስዮናዊ ናችሁ። በዙሪያችሁ ያለው ሁሉ፣ በየቀኑ፣ ጓደኞቻችሁ እና ጎረቤቶቻችሁ “እውነትን የት ማግኘት እንደሚችሉ ባለማወቃቸው ምክንያት ከእውነቱ የተገደቡ” ናቸው።”12 እናንተ በመንፈስ ስትመሩ፣ ጓደኞቻችሁን ወደተመለሰው ወንጌል እውነታ ለማስተዋወቅ ሃሳባችሁን ማካፈል ትችላላችሁ፣ መጋበዝ፣ የስልክ መልእክት ውይም ትዊት ማድረግ ትችላላችሁ። ወደ ሚስዮናዊ አገልግሎት በጉጉት ለመሳተፍ፣ በይፋ እስክትጠሩ መጠበቅ የለባችሁም።

ክህነት፣ ቤተ መቅደስ፣ እና የወንጌል ተልዕኮ በረከቶች “በክርስቶስ ... በአንድ ላይ” እንደሚሰበሰቡ ሁላ13 እናም ከአንድ ወጣት ሚስዮናዊ ከልብ፣ አእምሮ እና ነፍስ ጋር በጋራ ሲጣመሩ፣ ለስራው ብቁ ይሆናል።14 በሥልጣን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲወክል ኃላፊነቱን ለመወጣት የእሱ አቅም ይጨመርለታል። የመንፈሳዊ ኃይለኛ ጥምረት ያለውን የክህነት እና የቤተ መቅደስ ቃል ኪዳኖችን ማክበር፣ “የአምላክነትን ሃይል”15 በክህነት ስልጣን16 ያለ ራስ ወዳድነት በማገልገል፣ እና የእግዚአብሔር ልጆች ዘንድ የዘላለም ወንጌል መስበክ አንድን ወጣት “በእምነቱ ጠንካራና የማይነቃነቅ” እንዲሆን ያስችለዋል17 እናም “[በክርስቶስ] ስር እንዲሰድ እና እንዲገነባ ያደርገዋል።”18

በቤታችን ውስጥ እና በቤተክርስቲያን፣ ለጌታ የመዘጋጃ መንገዶች እና ለታመኑት የእግዚአብሄር ልጆች የማደጊያ ሦስት ነገሮች ሚዛናዊ ትኩረት መስጠት አለብን። ክህነት፣ ቤተመቅደስ፣ ሚስዮን። ሶስቱም ብቁ መሆንን እና እንዲሁ መቆየትን መውደዳችንን ይፈልጋሉ። ብቁ ሁኑ። ብቁ ሆናችሁ ቀጥሉ።

ቃል ኪዳን እና ምስክርነት

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ የወንጌልን ስራ ለማወጅ የሚሰጣችሁን ጥሪ እና ወደተወሰነ አካባቢ ውይም የስራ ቦታ የመንፈስ ምሪት ከናንተ ጋር ይሆናል። በትጋት አሁን ራስ ወዳድነት በሌለው የክህነትና የቤተመቅደስ አገልግሎት በትጋት ስትዘጋጁ የጌታ ህያውነት እውነታ ላይ ያላችሁ ምስክርነት ይጠነክራል። ለሱ እና ለሱ ስራ ያላችሁ ፍቅር ልባችሁን ይሞላል። ብቁ መሆንን ማፍቀር ስትማሩ፣ በጌታ እጅ ብዙ ሰዎችን ለመባረክና ለማገልገል ሃያል መሳሪያ ትሆናላችሁ።

በደስታም፣ የሰማዩ አባታችን እና የተወደደው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው እንደሆኑ እመሰክራለሁ። በእነርሱ ስራ መሳተፍ ልንቀበላቸው ከምንችላቸው ታላቅ በረከቶች መካከል አንዱ ነው። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።