ምንም ነገር ቢላችሁ አድርጉት
“እግዚአብሔር ያለንን” ለማድረግ ስንወስን፣ የየቀኑ ጸባያችንን ከእግዚአብሔር ፍላጎት ጋር አንድ ለማድረግ በቅንነት እንጥራለን።
አዳኝ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመዘገበውን ተአምሩን በቃና ዘገሊላ አደረገ። እናቱ ማርያም፤እና የእርሱ ደቀመዛሙርት እዛ ነበሩ። ማርያም ለድግሱ ስኬት ሀላፊነት ተሰምቷት ነበር። በአከባበሩ ወቅት፣ ችግር ተፈጠረ—የሰርግ ደጋሾቹ ወይን አለቀባቸው። ማርያም ተጨነቀች እና ወደ ኢየሱስ ሄደች። ጥቂት ተነጋገሩ፤ እና ማርያም ወደ አገልጋዮቹ ዞረች እና እንዲህ አለ፤
“የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ።
“እናም ስድስት የድንጋይ ጋኖች ተቀምጠው በዚያ ተቀምጠው ነበር። … [እነዚህ የድንጋይ ጋኖች ውሃ ለማጠራቀሚያ የሚጠቀሙባቸው አይደሉም ነገር ግን በሙሴ ህግ መሰረት ለእጥበት ነበሩየሚሆኑት።]
“ኢየሱስም ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።
“አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።
“አሳዳሪውም የወይን ተጅ የሆነውን ውሃ ቀመሰ” እናም መልካሙ ወይን ጠጅ በድግሱ መጨረሻ በመቅረቡ ተገረመ።1
ይህን ክስተት ሁሌም የምናስታውሰው ውሃን ወደ ወይን መቀየር የእግዚአብሔር ሀይል—ተአምር ታላቀ ማሳያ ስለሆነ ነው። ያ ታላቅ መልእክት ነው፣ ነገር ግን በዮሐነስ መጽሐፍ ውስጥ ታላቅ መልእክት አለ። ማርያም “እፁብ ድንቅ እና የተለየች፣” ነበረች፣2 የእራሱን የእግዚአብሔርን ልጅ እንድትወልድ፣ አንድትንከባከብ፣ እና እንድታሳድግ በእግዚአብሔር የተመረጠች ነበረች። ስለእርሱ በምድር ላይ ከማንም የበለጠ ታውቅ ነበር። ስለ ተአምራዊ ውልደቱ ታውቅ ነበር። ሀጠያት እንደሌለበት እና “እንደ ሌሎች ሰዎች እንደማይናገር፣ ወይም ማንም ሰው ያስተምረው እንደማይችል” ታውቅ ነበር።3 ለጋብቻ ድግስ ወይን የማቅረብ አይነት የግል አገልግሎት አይነት ለችግር መፍትሄ ለማግኘት ታላቅ ችሎታ እንዳለው ማርያም አውቃ ነበር። በእርሱ እና በመለኮታዊ ሀይሉ ላይ ጠንካራ መተማመንን ነበራት። እርሷ ለአገልጋዮቹ የሰጠችው ቀላል፣ ቀጥተኛ መመሪያ ቅድመሁኔታ፣ ገደብ አልነበረውም፥ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ።”
መልአኩ ገብርኤል ለእርሷ ሲገለጽላት ማርያም ወጣት ሴት ነበረች። በመጀመሪያ ላይ “እፁብ ድንቅ” እና “ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ ሲላት ደነገጠች። ይህ እንዴት አይነት ሰላምታ ነው ብላ አሰበች።” ገብርኤልም መልካም ዜና ይዞ እንደመጣ እና ምንም ሊያሳስባት እንደማይገባ አረጋገጠላት። እርሷ “ትፀንሻለሽ ... የልኡል ወንድ ልጅ። እናም “ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ… በያቆብ ቤትም ላ ለዘለአለም ይነግሳል።”
ማርያም ተገረመች፣ “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?”
መልአኩ አብራራ፣ ነገር ግን በትንሹ ብቻ ነበር፣ ለእርሷም ይህን አረጋገጠላት “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም።”
ማርያም እግዚአብሔር የጠየቀውን እንደምታደርግ በትህትና መለሰችለት፣ እያንዳንዱን ነገር ለማወቅ ሳጥጠይቅ እና በእርሷ ህይወት ላይ ስላለው ትርጉም ያለጥርጥር የማይቆጠሩ ጥያቄዎች ቢኖራትም ተቀበለችው። ለምን ይህን እንደሚጠይቃት ወይም ነገሮች እንዴት እንደሚከናወኑ ባታውቅም ይህን ለማድረግ ተቀበለች። የእግዚአብሔርን ቃላት ያለ ቅድመ ሁኔት እና አስቀድማ ተቀበለች፣4 ወደፊት ምን እንደሚሆን ፍፁም እውቀት ባይኖረትም እኳን። በእግዚአብሔር እምነት፣ ማርያም እንዲህ አለች፣ “እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ።5
“እግዚአብሔር ያለንን” ለማድረግ ስንወስን፣ የየቀኑ ጸባያችንን ከእግዚአብሔር ፍላጎት ጋር አንድ ለማድረግ በቅንነት እንጥራለን። በየቀኑ ቅዱሳት መፃህፍትን እንደማጥናት፣ በየጊዜው እንደመፆም፣ እና እንደ በእውነት ፍላጎት እንደመጸለይ ያሉት ቀላል የእምነት ተግባሮች ወደ ጥልቅ የመንፈሳዊ አቅም ይመራሉ። ከኢዜ በኋላም ቀላይ የእምነት ጸባያት ወደ ታዕምራታዊ ውጤት ይመራሉ። በህይወታችን ውስጥ እምነታችንን ከቡቃያነት ወደ ታላቅ ሀይል ለመልካም ይቀይሩታል። ከዚያም፣ ፈተናዎች ወደ እኛ ሲመጡ፣ በክርስቶስ ጋር መጣበቅ ለነፍሳችን አለመነቃነቅን ይሰጣል። እግዚአብሔር ድክመታችንን በመቀየር፣ ደስታችንን ጥልቅ በማድረግ፣ እናም “ሁሉም ነገሮች ለእኛ መልካም” እንዲሆኑ በማድረግ ቢባርከን ያስደስተዋል።6
ከጥቂት አመታት በፊት፣ በእያንዳንዱ ሳምንት በጥሪው ተጠምዶ፣ የአጥቢያውን አባላት በማማከር ሰአታትን የሚያሳልፍ ወጣት ኤጲስ ቆጶስ ጋር አወራሁ። እርሱ ድንቅ እይታን አድርጎ ነበር። እንዲህ አለ፣ የእርሱ አጥቢያ ውስጥ ያሉ አባላት የሚያጋጥሟቸው ችግሮች በየቦታው የቤተክርስቲያን አባላት የሚያጋጥማቸው ነው—እንደ ደስተኛ ትዳር የመመስረት ጉዳዮች፤ ስራን፣ ቤተሰብ፣ እና የቤተክርስቲያንን ሀላፊነት የማመዛዘን ትግሎች፤ የጥበብ ቃልን የመጠበቅ ችግሮች፤ ስራን ማስጠበቅ፣ ወይም የራቁጥ ፊልምን ማስወገድ፤ ወይም ስለ የቤተክርስቲያን ህገ-ሂደት ወይም ለእነርሱ ትርጉም ስለማይሰጡ የታሪክ ጥያቄዎች ዙሪያ ሰላም ማግኘት ሊሆን ይችላል።
ለአጥቢያ አባላት ያለው ምክር በብዛት ወደ ቀላል የእምነት ስራዎች ወደሆኑት፣ በፕሬእደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን እንደተመከርነው፣ እንደ መፅሐፈ ሞርሞንን ማንበብ፣ አስራትን መክፈል፣ እና በቤተክርስቲያኗ በመለኮታዊነት ማገልገል ነበር። በብዛት፣ ግን፣ እነርሱ የሚሰጡት መልስ ለእርሱ ከጥርጣሬ ውስጥ አንዱ ነበር። “ኤጲስ ቆጶስ፣ ከአንተ ጋር አልስማማም። እነዚያ መልካም ነገሮች መሆናቸውን እኛ ሁላችንም እናውቃለን። ሁል ጊዜ ስለነዚያ ነገሮች በቤተክርስቲያን ውስጥ እናወራለን። ነገር ግን አንተ እየተረዳሀኝ አልመሰለኝም። እነዚያ ሁሉ ነገሮች እኔን እያጋጠሙኝ ካሉት ነገሮች ጋር ምን ያገናኛቸዋል?”
መልካም ጥያቄ ነው። ከጊዜ በኋላ፣ አቅደው “ትንሽ እና ቀላል ነገሮችን”7 የሚያደርጉ ሰዎችን አስተዋልኩ—አስተዋልኩ—ትንሽ በሚስሉ መንገዶች የሚታዘዙ—በራሳቸው ከመታዘዝ ድርጊቶች በላይ በሚያስኬድ እምነት እና ጥንካሬ የተባረኩ ናቸው እናም፣ በእርግጥ፣ ከእነርሱ ጋር ምንም ግንኙነት ያለው ያለው ላይመስል ይችላል። በየቀኑ ባሉ የተለመዱ መታዘዞች እና ሁላችንም ለሚያጋጥሙን ታላላቅ የተወሳሰቡ ችግሮች መፍትሄ መካከል ያለውን ግንኙነትለማወቅ የሚከብድ ይመስላል። ነገር ግን ግንኙነት አላቸው። በእኔ ተሞክሮ፣ የየቀኑን ትንንሽ የእምነት ልምዶች እና ባህሪያት ማከናወን፣ በመንፈሳዊ አነጋገር፣ ከህይወት ፈተናዎች እራሳችንን የምናጠነክርበት የተሻለ አንድ መንገድ ነው። የእምነት ትንሽ ድርጊቶች፣ ጠቃሚ ባይመስሉም ወይም እኛ ካጋጠመን ችግር ጋር በፍጹም የማይገናኙ ቢመስሉም፣ በምናደርገው ነገር ሁሉ ይባርኩናል።
“የሶሪያ ሰራዊት መሪ...” እና “በቫሉር ውስጥ ሀያል ሰው” ነበር፣ ነገር ግን ለምፃም የነበርውን ናማን። አንድ አገልጋይ ሴት ልጅ ናማንን ሊያድን ስለሚችል አንድ ነብይ ተናገረች፣ እና አገልጋዮችን፣ ወታደሮችን፣ እና ለእራኤል ስጦታዎችን ይዞ ተጓዘ፣ በኋላም ወደ ኤልሳ ቤት ደረሰ። ኤልሳ እራሱ ሳይሆን፣ የኤልሳ አገልጋዮች፣ለላማን የጌታ ትእዛዝ “እንዲሄድ እና በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ እንዲታጠብ” እንደሆነ አሳወቁት። ተራ ነገር። በእርግጥም ይሄ ቀላል መመሪያ ሀያል ተዋጊውን ምክንያታዊ ያልሆነ፣ ቀሊል፣ ወይም ከእርሱ ክብር በታች መስሎ አስገረመው እናም መመሪያውን አናዳጅ ሆኖ አገኘው። በትንሹ፣ የኤልሳ መመሪያ ለናማን ትርጉም አልሰጠውም፣ “ስለዚህ ዞረ እና ሄደ።”
ነገር ግን የናማን አገልጋዮች በዝግታ ቀረቡት እና ኤልሳ የጠየቀው “ታላቅ ነገር” ቢሆን ኖሮ እንደሚፈፅመው አስተዋሉ። የተጠየቀው ግን አነስተኛ ነገር ስለሆነ፣ ማድረግ የለበትም፣ ለምን እንደሆነ ባይገባውም እንኳን? ናማን ውሰኔውን ደግሞ አሰበበት እና በጥርጣሬ፣ ነገር ግን በታዥነት፣ “ሄደ… እናም በየርዳኖስ ውስጥ እራሱን ሶስት ጊዜ ዘፈቀ” እናም በተአምራዊ ሁኔታ ዳነ።8
አንዳንድ የመታዘዝ ሽልማቶች ወዲያው ይመጣሉ፤ ሌሎች ከተሞከርን በኋላ ይመጣሉ። በእንቁ ታላቅ ዋጋ ውስጥ፣ መስዋእቶችን ለማቅረብ አዳም ስለነበረው ፅኑ ትጋት እናነባለን። መላዕኩ አዳምን መስዋዕት የሚያቀርበው ለምን እንደሆነ ሲጠይቀው፣ እንዲህ መለሰ፣ “እግዚአብሔር ስላዘዘኝ እንጂ፣ ለምን እንደሆነ አላውቅም።” መላእኩም መስዋእቱ “የአብ ብቸኛ ልጅ ለሆነው መስወእት ማሳያ” እንደሆነ አብራራ። መግለጫው የመጣው አዳም ለምን መስዋዕቶች ማቅረብ እንዳለበት ባያውቅም ለ”ብዙ ቀናት” በጌታ ታዛዥ ለመሆን መወሰኑንካሳየ በኋላ ነበር።9
ለእርሱ ወንጌል ባለን መታዘዝ እና ለቤተክርስቲያኑ ባለን ታማኝነት እግዚአብሔር ሁሌም ይባርከናል፣ ነገር ግን ያንን ለማድረግ ያለውን የጊዜ ቅደም ተከተል በብዛት አስቀድሞ አያሳየንም። ሙሉ ምስሉን ከመጀመሪያው አያሳየንም። ያኔ ነው በጌታ እምነት፣ ተስፋ እና መታመን የሚመጣው።
እግዚአብሔር እንድንታገስ—እንድናምነው እና እንድንከተለው ይጠይቀናል። “ስላላየን ብቻ እንዳንታበይ” ይማፀነናል። ከሰማይ ቀላል መልሶችን ወይም ፈጣን መስተካከሎችን እንዳንጠብቅ ያስጠነቅቀናል። “በእምነታችን መፈተን” ወቅት፣ ለመፅናት ምንም ያህል የከበደ ወይም ምላሹ የዘገየ ቢሆንም፣ ፀንተን ስንቆም ነገሮች ይስተካከላሉ።10 ስለ “የተዳፈነ መታዘዝ”11 አይደለም የምናገረው ነገር ግን በፍፁሙ የጌታ ፍቅር እና ሰአት ላይ ስላለ የማስተዋል መታዘዝ ነው።
የእምነታችን መፈተን ሁሌም ለቀላሉ፣ የየቀን እምነትን ይዞ በእውነት መቆየትን ያካትታል። ከዚያም፣ እና ከዚያም ብቻ፣ ነው የምንፈልገውን መለኮታዊ መልስ እንደምንቀበል ቃል ኪዳን የገባው። እኛ “የእምነታችንን እና የትጋታችንን፣ እና የትግስታችን፣ እና የእረጅሙ ስቃያችንን ሽልማት የምናጭደው” መቼ፣ እዴት፣ እና ለምን እንደሆነ ሳንጠይቅ እርሱ የሚጠይቀንን በማድረግ አንድ ጊዜ ብቻ አሳይተናል።12 ትክክለኛ መታዘዝ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ያለ ቅደም ሁኔታ እና አስቀድሞ መቀበል ነው።13
በማወቅ ወይም ባለማወቅ፣ ሁላችንም በየቀኑ “ማንን እንደምናመል” እንመርጣለን።14 በፅናት፣ በታማኝነት በየየቀን መሰጠት ጌታን ለማገልገል ያለንን ፍላጎት እናሳያለን። መንገዳችንን እንደሚመራ ጌታ ቃል ገብቷል፣15 ነገር ግን እርሱ ያንን እንዲያደርግ፣ እርሱ መንገዱን እንደሚያው በማመን ልንራመድ ይገባናል ምክንያቱም እርሱ “መንገድ” ነውና።16 እርሱን ስናምነው፣ ልክ ውሃው ወደ ወይን እንደተቀየረው፣ ህይወታችንም ይቀየራል። እርሱን ስናምን እና ስንከተል፣ ልክ ውሀ ወደ ወይን እንደተቀየረው፣ ህይወታችን ይቀየራል። እኛም በሌላ በኩል ለመሆን ከምንችለው በላይ፣ እናም የተሻለ ለመሆን እንችላለን። በጌታ ታመኑ፣ እና “እርሱ አድርጉ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ።” በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።