2010–2019 (እ.አ.አ)
አንዳንድ ሴቶች
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


11:49

አንዳንድ ሴቶች

አንዳንድ ሴትች በአዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ መሀከል እንደሚገኙ ደቀመዛሙርቶች እና በእርሱ የኃጢያት ክፍያ የተስፋ ቃል በኩል ተስፋ እንዳላቸው ተምረናል።

ውድ እህቶቼ፣ ለቀዳሚ አመራር ግብዣና ለ#iwasastranger ጥረት በቸርነት እና በጉጉት ምላሽ በመስጠታችሁ እንዴት ነው የምንወዳችሁ እና የምናመሰግናችሁ። በመጸለይ፣ የመንፈስን ሹክሹክታ በማዳመጥ፣ እና ለምትቀበሉት መነሳሳት መልስ በመስጠት እባካችሁ ቀጥሉ።

በዚህ አካባቢም ይሁን በአለም አቀፍ ስጓዝ፣ አንድ ሰው “ያስታውሱኛልን?” የሚል ጥያቄ መጠየቃቸው አዲስ ነገር አይደለም። ምክንያቱም ፍጹም ስላልሆንኩኝ፣ ስሞችን በአብዛኛው ጊዜ እንደማላስታውስ አምኜ ተቀብያለሁ። ቢሆንም፣ የሰማይ አባት ከውድ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ጋር ስገናኝ እንዲሰማኝ የፈቀደውን እውነተኛ ፍቅር አስታውሳለሁ።

በቅርብ በእስር ቤት ውስጥ ያሉተወዳጅ እህቶችን ለመጎብኘት እድል ነበረኝ። ከልብ የመነጨ ስንብት ስናቀርብ፣ አንድ ውድ ሴት እንዲህ ለመነች፣ “እህት በርተን፣ እባክሽ አትርሺን።” መታወስ የሚፈልጉት እርሷ እና ሌሎች አንዳንድ ሀሳቦች ከእናንተ ጋር ስካፈል እንዲሁ እንዲሰማቸው ተስፋዬ ነው።

አንዳንድ ሴቶች በአዳኝ ቀን፥ በአዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ማእከል

በተለያዩ ዘመናት የነበሩ ውድ እህቶቻችን እኛም የምንጥርለትን ደቀመዛሙርትነት ታማኝ ንድፍ አሳይተዋል። “አዲስ ኪዳን ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በኃጢያት ክፍያው እምነት የነበራቸው፣ በትምህርቱን የተማሩና የኖሩበት፣ እና ስለአገልግሎቱ፣ ታዕምራቱ፣ እና ግርማው የመሰከሩ በስም የተጠሩ ወይም ስማቸው የማይታወቅ፣ [አንዳንድ] ሴቶች ነበሩ። እነዚህ ሴቶች ምሳሌ የሆኑ ደቀመዛሙርት እና የደህንነት ስራ ምስክሮች ሆኑ።”1

አንዳንድ ሴቶች

በመፅሐፈ ሉቃስ ውስጥ የነበሩትን ታሪኮች አስቡባቸው፥ መጀመሪያ በአዳኝ አገልግሎት ወቅት፥

“ከዚህም በኋላ … [ኢየሱስ] እየሰበከና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች እየተናገረ በየከተማይቱ በየመንደሩም ያልፍ ነበር፤ አሥራ ሁለቱም ከእርሱ ጋር ነበሩ፥

“እናም … አንዳንድ ሴቶች፣ … ማርያም፥ … ዮሐናም … ሶስናም ብዙዎች ሌሎችም ሆነው በገንዘባቸው ያገለግሉት ነበር።”2

ቅጥሎ፣ ከትንሳኤው በኋላ፥

“… ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች ነበሩ፤

“ሥጋውንም ባጡ ጊዜ፣ ሕያው ነው የሚሉ የመላእክትን ራእይ ደግሞ አየን ሲሉ መጥተው ነበር … ።”3

“አንዳንድ ሴቶች” የሚል ልዩ ያልሆነ አባባልን ለብዙ ጊዜ አንብቤ አልፈው ነበር፣ ግን በጥንቃቄ ሳሰላስላቸው፣ እነዚህ ቃላት ከገጹ ዘልለው የሚወጡ መሰሉ። ከአንዳንድ ሴቶች ጋር የተያያዘውን በእንግሊዘኛ ሰርተን የሚለውን ቃል ተመሳሳይ ቃላትን ተመልከቱ “እርግጠኛ፣” “አዎንታዊ፣” “እምነት፣” “ጽኑ፣” “ቁርጥ ያለ፣” “እርግጠኛ፣” እና “አስተማማኝ።”4

እነዚህን ገላጭ ቃላት ሳሰላስልበት፣ “አዎንታዊ፣” “እምነት፣” “ጽኑ፣” “ቁርጥ ያለ” የአዳኝ ምስክርነት ስላላቸው በአዲስ ኪዳን ስለሚገኙ ሁለት እርግጠኛ ሴቶች እንዳስታውስ አደረገኝ። እነርሱ፣ እንደእኛ፣ ፍጹም የሆኑ ሴቶች ባይሆኑም ምስክርነታቸው የሚያነሳሳ ነበር።

በውሀ ጉድጓድ አጠገብ የነበረች እና ከአዳኝ የተማረችውን እንዲመጡና እኒያዩ የጠራችን ስሟ የማይታወቅ ሴት ታስታውሳላችሁን? እርሷም እርግጠኛ ምስክሯን በጥያቄ መልክ ሰጥታ ነበር፥ “እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?” 5 ምስክርነቷ እና ግብዣዋ የሚገፋፉ ሆነው “በእርሱ  … ብዙ ሰዎች አመኑ።”6

ማርታ ስለአዳኝ ምስክሯን ሰጠች

ከወንድሟ፣ አልአዛር፣ ሞት በኋላ፣ የአዳኝ ውድ ደቀመዛሙር እና ጓዳኛ የነበረችው ማርታ ታላቅ በሆነ ስሜት እንዲህ አወጀች፣ “ጌታ ሆይ፥ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር፤” ስትቀጥልም እርግጠኛነቱን አስቡበት፣ “ነገር ግን፣ አሁንም ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰጥህ አውቃለሁ።” ቀጥላም መሰከረች፣ “አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ።”7

ከእነዚህ እህቶች አንዳንድ ሴትች በአዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ መሀከል እንደሚገኙ እና በእርሱ የኃጢያት ክፍያ የተስፋ ቃል በኩል ተስፋ እንዳላቸው ተምረናል።

አንዳንድ ቃል ኪዳን የሚጠብቁ የዳግም መመለስ ሴቶች፥ መስዋዕት ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን

በጥንት፣ አንዳንድ ሴቶች ሲመሰክሩ እና በኢየሱስ ትምህርቶች ሲኖሩ መስዋዕት አድርገዋል። በዳግም መመለስ የመጀመሪያ ቀናት ላይም አንዳንድ ሴቶች እንዲሁ አድርገዋል። ዱርሲላሂንድሪክስ እና ቤተሰቧ፣ እንደ አዲስ ተቀያሪዎች፣ በክሌይ አውራጃ ምዙሪ ውስጥ ቅዱሳናት ይሰደዱበት ከነበሩት መካከል ነበረች። ባለቤቷ በክሩክድ ወንዝ ጦርነት ምክንያት የተደነዘዘ ነበር። እርሱን ለመንከባከብ እና ቤተሰቧን ለመርዳት ብቻዋን የተተወች ነበረች።

“በሚያስጨንቅ አንድ ጊዜ፣ ቤተሰብ ምግብ ሳይኖረው፣ ‘አይዞሽ፣ ጌታ ይሰጣልና” የሚል ድምፅ እንደነገራት ታስታውሳለች።

ወንድ ልጇ ለሞርሞን ሻለቃ በፈቃደኝነት ለመሂድ ሲያስፈልገው፣ በመጀመሪያ ዱርሲላ ተከላከልች እና በድምጽ ‘ከፍተኛውን ግልማ አትፈልጊምን?’ እስከሚላት ድረስ ከሰማይ አባት ጋር በጸሎት ተታገለች። እንዲህም መለሰች፣ ‘አዎን፣’ እናም ድምጹ ቀጥሎም፣ ‘ታላቅ መስዋዕቶችን ከማድረግ በስተቀር እንዴት የምታገኚው ይመስልሻል’”8

ከዚህች አንድ ሴት ቃል ኪዳን መጠበቅ መስዋዕት ለማድረግ ፈቃደኛነታችን እንደሚያስፈልገው እንማራለን።

የዛሬ አንዳንድ ሴቶች፥ የእርሱን መመለስ ማስታወስ እና ለዚህም ክብር መዘጋጀት

በአዳኝ ዘመን እና በወንጌል ዳግም መመለስ ቀናት ስለነበሩ አንዳንድ ሴቶች ጠቅሻለሁ። በቀናችን ስለሚገኙ አንዳንድ ሴቶች ምሳሌስ?

እህት በርተን በእስያ ከሚኖሩ እህቶች ጋር

በቅርብ በኤስያ በተመደብኩበት ጊዜ፣ ተገናኝቼአቸው ከነበርኩት አንዳንድ ሴቶች እንደገናም ተነሳስቼ ነበርኩኝ። በህንድ፣ በማሌዥያ፣ እና በኢንዶኔዥያ ውስጥ በነበሩ፣ የወንጌል ኑሮ ከቤተሰብ እና ከሀገር ባህል ጋር በመጋጨቱ ታላቅ መስዋዕት በማድረግ በወንጌል ባህል በቤታቸው ውስጥ ለመኖር በሚጥሩ በመጀመሪያ ትውልድ አባላት ተደንቄ ነበርኩኝ። በሆንግ ኮንግ እና በታይዋን ውስጥ የነበሩ የብዙ ትውልድ አንዳንድ ሴቶች በአዳኝ መካከል በመሆን እና ቃል ኪዳኖችን ለመጠበቅ መስዋዕት በማድረግ የቤተሰባቸውን ህይወቶች፣ የቤተክርስቲያን አባላት፣ እና ህብረተሰቦች በመባረክ ቀጥለዋል። በዚህም ተመሳሳይ አንዳንድ ሴቶች በቤተክርስቲያኗ በሙሉ ይገኛሉ።

እህት በርተን በእስያ ከሚኖሩ እህቶች ጋር

ህይወቴን ለብዙ አመቶች የባረኩ አንድ ሴት ለ15 አመት አካለ ሰንኮል የሚያደርግ፣ አስቸጋሪ፣ እና የባሰ እየሆነ በሚመጣ Inclusion Body Myositis የሚባል በሽታን የምትታገል ነበረች። በጋሪዋ ላይ ሁልጊዜ የምትቀመጥ ብትሆነም፣ ምስጋና ያላት እና “ይቻላል ይቻላል የሚል ዝርዝር” የምትጠብቅ ነበረች—ይህም ለመተንፈስ እችላለሁ፣ ለመዋጥ እችላለሁ፣ ለመጸለይ እችላለሁ፣ የአዳኝን ፍቅር እንዲሰማኝ እችላለሁ የሚሉ ለማድረግ የምትችላቸው ነገሮች ዝርዝር ነው። በክርስቶስ ላይ የሚያተኩር እርግጠኛ ምስክርነቱን በየቀኑ ለቤተሰቧ እና ጓደኞቿ ትመሰክራለች።

በቅርብ የጀኒን ታሪክ ሰማሁ። በሚስዮን እያገለገለች እያለች ወላጆቿ የተፋቱባት ከሚስዮን የተመለሰች ነበረች። ወደቤት መመለስ “እስከ ሞት ድረስ እንዳስፈራት ተናገረች። ግን በጣሊያን ባገለገለችው ሚስዮን መጨረሻም፣ ወደ ዩ. ኤስ. በምትጓዝበት ጊዜ በሚስዮን ቤት ውስጥ ስታርፍ፣ አንድ ሴት፣ የሚስዮን ፕሬዘደንት ባለቤት፣ ጸጉሯን በማበጠር በርህራሄ አገለገለቻት።

ከአመቶች በኋላ፣ ሌላ አንድ ሴት፣ ቴሪ—የካስማ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘዳንት—ጄኒ እንደ ዎርድ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘዳንት በምትጠራበት ጊዜ ህይወቷን ባረከች። በዚያ ጊዜ፣ ጄኒ ለዶክትሬት ድግሪዋ መመረቂያዋን እየጻፈች ነበር። እንደ መሪ ቴሪ ለጄኒ እንደ አስተማሪ በማገልገል ብቻ ሳይሆን፣ እርሷም የሉኪምያ የሚያስፈራ የህክምና ውጤት ዜና በተነገራት ጊዜ ለ10 ሰዓት በሆስፒታል አብራት ተቀምጣ ነበር። ቴሪ በሆስፒታል ጎበኘቻት እናም ጄኒን ወደ ቀጠሮዋ ነድታ ወሰደቻት። ጄኒ እንዳለችው፣ “በመኪናዋ ውስጥ ለብዙ ጊዜ አስታውኬበት ነበር።”

የታመመች ብትሆንም፣ ጄኒ በጀግንነት እንደ ዎርድ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘደንት አገለገለች። በመጥፎ ጊዜዋም፣ ከመኝታዋ ስልክ ደወለች፣ የእጅ ስልክ መልእክት እና ኢሜል ላከች፣ እናም እህቶች መጥተው እንዲጎበኟት ጋበዘች። እህቶቿን ከሩቅ በማፍቀር፣ ፖስታዎች እና ማስታወሻዎች ለሰዎች ላከች። ዎርዷ ለዎርድ ታሪክ ለመጠቀም የአመራሯን ፎቶ እንድትሰጣቸው ሲጠይቁም፣ የተሰጣችሁ ይህ ነበር። ጄኒ ራሷን እርግጠኛ ሴት ስለነበረች፣ ሁሉም የሌሎችን ሸከም፣ እንዲሁም የራሷን፣ እንዲካፈሉ ጋበዘች።

የአጥቢያ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ኮፍያዎችን አድርገው

እንደ እርግጥኛ ሴት፣ ጄኒ መስክራለች፥ “ሌሎችን ለማዳንብቻ ሳይሆን ራሳችንን ለማዳን ነው በዚህ ያለነው። እና ያም ደህንነት የሚመጣው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ተባባሪ በመሆን፤ የእርሱን ጸጋ እና የእርሱን የኃጢያት ክፍያ እናም ለቤተክርስቲያኑ ሴቶች ያለው የፍቅር ስሜትን በመረዳት ነው። ያም የሚሆነው የሰውን ጸጉር በማበጠር፣ የሚያነሳሳ፣ ግልጽ፣ እና ራዕያዊ የተስፋ እና የጸጋ መልዕክት ማስታወሻ በመላክ፣ ወይም ሴቶች እንዲያገለግሉን በመፍቀድ ነው።”9

እህቶች፣ እኛ ትኩረት የለሽ፣ ተጠራጣሪ፣ ተስፋ ቆራጭ፣ ኃጢአተኛ፣ አዛኝ፣ ወይም ነፍስ-ዘረጋ ስንሆን፣ በውሀ ጉድጓድ ጥግ አንድ ሴት እንዳደረገችው የእርሱን የህይወት ውሀ እንድንጠጣ ጌታ የሚጋብዘንን፣ ሌሎች እንድሁ እንዲያደርጉ እንጋብዝ እናም የራሳችንን እርግጠኛ ምስክርነት እንሰጣለን፥ “እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?”

ማርታ ወንድሟ በሞተበት ጊዜ ይመስላት እንደነበረው፣ ህይወት ፍትሀዊ በማይመስልበት ጊዜ—የብቸኝነት፣ ልጅ ያለመውለድ፣ የሚወደድ ሰው ሞት፣ ለጋብቻ እና ለቤተሰብ የነበረን እድል ማጣት፣ የቤት መሰበር፣ አቅም የሚያሳጣ ጭንቀት፣ የአካል ወይም የአዕምሮ በሽታ፣ የሚገድብ ውጥረት፣ ጭንቀት፣ ሱስ፣ የገንዘብ ችግር፣ ወይም በሌሎች ብዙ ነገሮች ልብ መሰበር ሲያጋጥመን—ማርታን እናስታውስ እና በሚያመሳስል እርግጠኛ ምስክርነታችን እንዲህ እናውጅ፥ “ነገር ግን አውቃለሁ … [እና] አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ።”

ሴቶች በመስቀል አጠገብ

ውድ አዳኛችን በጣም በሚያም ሁኔታ በመስቀል ላይ ሲሰቃይ እርሱን ለመካድ እምቢ ያሉትን እና ከሰዓቶች በሁላም የእርሱ ግርማዊ ትንሳኤ የመጀመሪያ እርግጠኛ ምስክር ለመሆን እድል ስለነበራቸው ብዙ አንዳንድ ሴቶች እናስታውስ። በጸሎት እና በቅዱስ መጻህፍት ጥናት ወደ እርሱ እየቀረብን እንገኝ። የኃጢያት ክፍያውን መስዋዕት ቅዱስ ምልክት ለመቀበል በመዘጋጀት እና በየሳምንቱ በሚከናወነው የቅዱስ ቁርባን ስርአትን በመቀበል እና ሌሎችን እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ በማገልገል ወደ እርሱ እንቅረብ። ምናልባት እርሱ እንደገና በሚመጣበት ጊዜ የእርሱን በግርማ መመለስ ከሚደሰቱት አንዳንድ ሴቶች፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቶች፣ ክፍል ለመሆን እንችል ይሆናል።

አዳኝ በዳግም ምፅዓት ጊዜ

እህቶች፣ ስለሰማይ ወላጆቻችን፤ ስለአዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ለእኛ ጥቅም ስላደረገው መጨረሻ ስለሌለው የኃጢያት ክፍያ እመሰክራለሁ። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደ የዳግም መመለስ ነቢይ አስቀድሞ የተሾመ ነበር። መፅሐፈ ሞርሞን እውነት ነው እናም በእግዚአብሔር ሀይል ተተርጉሟል። በህያው ነቢይ፣ በፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ በቀናችን ተባርከናል። ስለእነዚህ እውነቶች፣ እርግጠኛ ነኝ! በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻ፥ በሚያዝያ 1፣ 2017፣ እህት በርተን ከሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ሀላፊነት ተለቅቀው ነበር።