ደግነት፣ ልግስና፣ እና ፍቅር
ህይወታችንን እንፈትሽ እናም የአዳኝን ምሳሌ ደግ፣ አፍቃቲ፣ እና ለጋስ በመሆን ለመከተል እንወስን።
ውድ ወንድሞች፣ በዚህ ኣለም አቀፍ የእግዚአብሔር ክህነት ተሸካሚዎች ስብሰባ እናንተ ለማነጋገር ባለኝ እድል ክብር ይሰማኛል። በዚህ ምሽት ከዚህ በፊት ተናግሬበት የነበረን ርዕስ ለመጥቀስ እፈልጋለሁ።
ነቢዩ ሞርሞን የአዳኝን ዋና ባህሪዎች እናም የትኛውን ደቀመዛምርቱ እንደሚከተሉ ዘርዝሮ ነበር። እንዲህ አለ፥
“እናም ሰው የዋህ እናም በልቡ የሚራራ፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ከሆነ እርሱ ልግስና ሊኖረው ይገባዋል፤ ልግስና ግን ከሌለው እርሱ ከንቱ ነውና፤ ስለሆነም ልግስና ሊኖረው ይገባል።
እናም ልግስና ይታገሳል፣ እናም ደግ ነው፣ እናም አይቀናም፣ እናም በኩራት አይወጠርም፣ የራሷን አትፈልግም፤ በቀላሉ አይቆጣም። …
“ስለዚህም፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ልግስና ከሌላችሁ ከንቱዎች ናችሁ፣ ልግስና አትወድቅምና። ስለሆነም ከሁሉም በላይ ታላቅ የሆነውን ልግስናን ያዙ፤ ሁሉም ነገሮች መውደቅ አለባቸውና—
“ነገር ግን ልግስና ንፁህ የክርስቶስ ፍቅር ነው፣ እናም እስከዘለዓለም ይፀናል፤ እናም በመጨረሻው ቀንም እርሱን የያዘ መልካም ይሆንለታል።”1
ወንድሞች፣ ለሌሎች ገግ ካልሆንን የእግዚአብሔር ክህነትን የምናከብር አይደለንም።
ውድ ጓደኛዬ እና የስራ ተባባሪዬ ሽማግሌ ጆሴፍ ቢ. ዎርዝልን በእውነትም ደግ ሰው ነበር። እንዲህ አለ፥
“ደግነት የሰለስቲያል ህይወት ባህርይ ነው። ደግነት እንደ ክርስቶስ አይነት ሰው ሌላን እንዴት የሚንከባከብበት ነው። ደግነት ቃላቶቻችንን እና በስራ፣ በትምህርት ቤት፣ በቤተክርስቲያን፣ እና በልዩ በቤቶቻችን ውስጥ በምናደርገው በሙሉ የሚሰራጭ ነው።
“አዳኛችን ኢየሱስ የደግነት እና የርህራሄ ጥሩ ምሳሌ ነበር።”2
ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚያስተምሩን ክህነት በጻድቅነት መጠቀም የሚመካው በደግነት፣ በልግስና፣ እና በፍቅር መርሆች በመኖር ነው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ እንደምናነበው፣
“በማሳመን፣ … በትእግስት፣ በደግነት፣ እና በትህትና፣ እና ግብዝነት በሌለው ፍቅር ካልሆነ በስተቀር፣ ምንም ሀይል ወይም ተጽዕኖ በክህነት ስልጣን ዘዴ ሊደገፍ አይቻልም ወይም አይገባውም፤
“ይህም በርህራሄ፣ እና ያለግብዝነትና ያለተንኮል መንፈስን በታላቅ በሚያሳድግ ንጹህ እውቀት ብቻ ነው ሊደገፍ የሚችለው።3
ወንድሞች፣ ህይወታችንን እንፈትሽ እናም የአዳኝን ምሳሌ ደግ፣ አፍቃቲ፣ እና ለጋስ በመሆን ለመከተል እንወስን። እናም ይህን ስናደርግ፣ ለቤተሰቦቻችን፣ እና ወደሰማይ ቤታችን ለመመለስ በምንጓዝበት አንዳንዴ አስቸጋሪ በሆኑት ጉዞ አብረው ለሚጓዙት የሰማይ ሀይልን ለመጥራት በሚያስችል በተሻለ ቦታ ላይ እንሆናለን። ስለዚህ የምጸልየው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።