ፍጹም ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ ይጥላል
ፍርሀትን ወደጎን እናድርግ እናም በምትኩ በደስታ፣ በትህትና፣ በተስፋ፣ እና ጌታ ከእኛ ጋር እንደሆነ ባለ የሙሉ ልብ እምነት እንኑር።
ውድ ወንድሞችና እህቶች፣ ውድ ጓደኞች፣ እንደ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን በእምነትና በእግዚአብሔርና በልጆቹ ፍቅር አንድነት መገናኘታችን እንዴት የሚያስደስት እና ምን እድል ነው።
ውዱ ነቢያችን፣ ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ከእኛ ጋር በመገኘታቸው ምስጋና አለን። ፕሬዘደንት፣ እኛ የመመሪያ ቃላትዎን፣ ምክርዎን፣ እና ጥበብዎን ሁልጊዜም በልብ እንቀበላለን። እንወድዎታለን፣ ፕሬዘደንት ሞንሰን፣ እና እንደግፎታለን፣ እናም ለእርስዎ ዘወትር እንጸልያለን።
ከአመቶች በፊት፣ እንደ ፍራንክፈርት፣ ጀርመን የካስማ ፕሬዘደንት እያገለገልኩኝ እያለኑ፣ ውድ ግን ደስተኛ ያልሆነች እህት ከካስማ ስብሰባችን መጨረሻ ላይ ወደ እኔ መጣች።
“ይህ መጥፎ አይደለምን?” ብላ ጠየቀችኝ። “በንግግርህ ጊዜ ያንቀላፉ አራት ወይም አምስት ሰዎች ነበር!”
ለትንሽ ጊዜ አሰብኩኝና እንዲህ መለስኩኝ፣ “በቤተክርስቲያን መተኛት ከእንቅልፎች ሁሉ ጤንነት የሚሰጥ ማንቃለፍ ነው።”
አስደናቂዋ ባለቤቴ፣ ሄሪየት፣ ይህን ንግግር ሰማች እናም በኋላም ያ ከሰማሁት መልሱ ይበልጥ ጥሩ የሆነ ነው አልችኝ።
ታላቁ መነቃቃት
ከጥቂት መቶ አመታት በፊት በሰሜን አሜሪካ ውስጥ፣ “ታላቁ መነቃቃት” የሚባል ድርጊት በገጠሮች ሁሉ ተስፋፋ። የዚህ ዋና አላማ ስለሀይማኖት ጉዳይ እያንቀላፉ ያሉትን እንዲነቁ ለማድረግ ነበር።
ወጣቱ ጆሴፍ ስሚዝ በዚህ የሀይማኖት መነቃነቅ ክፍል ከነበሩት ሰባኪዎቹ በሰማው ነገሮች ተፅዕኖ ተሰምቶት ነበር። የእግዚአብሔርን ፍላጎት ለማግኘት የግል ጸሎትን ለማድረግ የወሰነበት ምክንያት አንዱ ይህ ነበር።
ኃጢያተኞችን ስለሚጠብቀው ሲዖል የሚያስፈራራ ስብከት በመስጠት ታዋቂ የሆኑት እነዚህ ሰባኪዎች አንድ ድራማዊ፣ ስሜታዊ ስብከት ቅጥ ነበራቸው።1 ንግግራቸው ሰዎች እንዲያንቀላፉ አያደርግም—ነገር ግን አንዳንድ በቅዠት እንዲመጣ አድርገዋል። ዓላማቸው እና አካሄዳቸው ሰዎችን ወደ ንስሃ እንዲመጡ የሚያስፈራራ ይመስል ነበር።
ፍርሃት እንደ መቆጣጠሪያ መንገድ
በታሪክ፤ ፍርሃት በአብዛኛው ጊዜ ሰዎች እርምጃ እንዲወስዱ ለማድረግ ይጠቀሙበት ነበር።. ወላጆች ልጆቻቸው ላይ፤ ቀጣሪዎች በተቀጣሪዎቻቸው ላይ፤ ፖለቲከኞችም በመራጮች ላይ ተጠቅመውበታል።
አዋቂ አሻሻጮች የፍርሃትን ሀይል ያውቃሉ እናም በአብዛኛው ይጠቀሙበታል። ለዛም ነው አንዳንድ ማስታወቂያዎች፤ የጥርስ መፋቂያ ታዋቂውን ምርት ካልገዛን፣ ወይምበድብቅ መልክት የቁርስ ምግባቸውን ካልገዛን የስቃይ ህይወት የምንመራ፣ እና ሳንደሰት ብቻችንን የምንሞት የሚያስመስል የስውር መልክት የሚያስተላልፉት።
በዚህ እንስቅ እና እኛ በእንደዚህ ያለ ዘዴያዊ ቁጥጥ ስር አንወድቅም ብለን እናስባለን፤ ነገር ግን እንወድቃለን። የባሰ፤ እኛ እነዚህን፣ ተመሳሳይ፣ መንገዶች ሌሎች እኛ የምንፈልገውን እነዲያደርጉልን እንጠቀምበታለን።
ዛሬ የእኔ መልክት ሁለት ዓላማ አለው። የመጀመሪያው ምን ያህል ድረስ ፍርሃትን ሌሎችን እራሳችንን ጨምሮ ለማነሳሳት እንደምንጠቀምበት እንድናሰላስል እና እንድናተኩር ለማበረታታት ነው። ሁለተኛው የተሻለ መንገድ አስተያት ለመሰንዘር ነው።
በፍርሃት ያለው ችግር
መጀመሪያ፤ በፍርሃት ስላለው ችግር እንነጋገር። ከሁሉም በኋላ፣ ማነው ከእኛ ውስጥ በፍርሃት ሳይገደድ ጤናማ ምግብ የሚበላ፤ የመቀመጫ ቀበቶውን የሚያደርግ፤ በብዛት እስፖርት የሚሰራ ሌላው ቀርቶ ንስሓ የሚገባ?
ፍርሃት በተግባራችን እና በባህሪያችን ላይ ሃይለኛ ተፅኖ ማረጉ እውነት ነው። ነገር ግን ያ ተፅኖ ጊዜአዊ እና ጥልቀት የሌለው ነው። ፍርሃት መቼም ልባችንን የመቀየር ሃይል የለውም፤ እናም ትክክለኛ ነገርን የምንወድ እና የሰማይ አባታችንን መታዘዝ ወደ እምንፈልግ ሰዎች አይቀይረንም።
የሚፈሩ ሰዎች ትክክለኛ ነገሮችን ሊሉ እና ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ነገር ግን ትክክለኛ ነገሮች አይሰማቸውም። በአብዛኛው ጊዜ እርዳታ አልባነት እና ብስጭት ይሰማቸዋል። ከጊዜ በኋላ፤እነዚህ ስሜቶች ወደ አለመተማመን ተከላካይነት፣ እንዲሁም አመፀኝነት ያመራል።
በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ይህ ለህይወት እና ለመሪነት ያለው የተሳሳተ አቀራረብ በአለምውስጥ ብቻ የተወሰነ አይደለም። በቤታቸው ውስጥም ይሁን በቤተክርስትያን ጥሪዎቻቸው በስራ ቦታ፤ ወይም ከሌሎች ጋር በሚያደርጉት የእለት ተለት ግንኙነት፤የቤተክርስትያን አባሎች ፃዲቅ ያልሆነ አገዛዝን ሲለማመዱ ስሰማ ያሳዝነኛል።
በአብዛኛው፤ እኚሁ ሰዎች በሌሎች ውስጥ በሰው ላይ ማፌዝን ሊያወግዙት ይችላሉ፣ ነገር ግን በራሳቸው ውስጥ ያለው አይታያቸውም። በራሳቸው ህግጋት ታዛዥ እንዲሆኑ ይጠይቃሉ፣ ነገር ግን ሌሎች የእነርሱም ህግ በማይከተሉበት ጊዜ፣ እነርሱን በቃል፣ በስሜት፣ እና አንዳንዴም በማጎሳቀል ይገስጻሉ።
ያልተረዱት ነገር ግን “በሰው ልጆች ህይወት ላይ በማኝኛውም ደረጃ ፃድቅ ያልሆነ፣ ቁጥጥር ወይም አገዛዝ፤ ወይም ማስገደድን ስንጠቀም፤ ሠማያት እራሳቸውን ያርቃሉ እናም የጌታ መንፈስም እጅግ ያዝናል።”2
አንዳንድ የራሳችንን ተግባር የመጨረሻው መነሻውን የሚያፀድቅ ነው ብለን በማመን ምግባራችንን ለመግለፅ የምንፈተንበት ግዚያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ተቆጣጣሪ፣ ተጫኝ እና አስቸጋሪ፣ መሆንን ለሌሎች መልካምነት ስንል ነው ብለን ልናስብ እንችላለን። እንደዚያ አይደለም፣ ጌታ ግልፅ አርጎታልና፥ “የመንፈስ ፍሬ፣ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ እርጋታ፣ ጥሩነት፣ እምነት፣ ትህትና እና ቁጥብነት” ነው።3
የተሻለው መንገድ
የሰማይ አባቴን የበለጠ እያወቅኩት በመጣሁ ቁጥር፣ ልጆቹን እንዴት እንደሚያነሳሳና እንደሚመራ በተጨማሪ አያለሁ። እሱምየሚናደድ፣ በቀለኛ፣ ወይም የብቀላ አይደለም።4 የሱ ፍፁም ዓላማው፤ ስራው እና ክብሩ እኛን ማስተማር፣ ከፍ ማረግ እና ወደሱ ሙሉነት መምራት ነው።5
እግዚኣብሔር ራሱን ለሙሴ እንዲህ ብሎ ገለፀ “ምህረተኛ እና ባለፀጋ፤ ትግስተኛ እና መልካምነቱ እና ጥሩነቱ የበዛ።”6
የሰማይ አባታችን ለእኛ ያለው ፍቅር፣ ለልጆቹ፤ ከመረዳት ችሎታችን በላይ እጅግ የላቀ ነው።7
ይህ ማለት እግዚአብሔር ከተእዛዙ በተቃራኒው የሚሄዱ ባህርዮችን ችላ ይላል ወይም አይመለከትም ማለት ነውን? አይደለም፣ በእርግጥም አይደለም!
ሆኖም ግን ከባህሪያችን የበለጠ ሊቀይረን ይፈልጋል። ተፈጥሮአችንን አንስቶ ሊቀይር ይፈልጋል። ልባችንን ሊቀይር ይፈልጋል።
ሌሎችን እንድንረዳ እና የብረቱን መንገድ አጥብቀን እንድንይዝ፤ ፍርሃታችንን እንድንጋፈጥ፤ እና በጉብዝና ወደፊት እና ወደላይ በቀጥተኛው እና በጠባቡ መንገድ ላይ እንድንራመድ ይፈልገናል ። ይህንን ለእኛ የሚፈልገው ስለሚወደን እና የደስታም መንገድ ይህ ስልሆነ ነው።
ስለዚህ፣ እንዴት ነው በእኛ ዘመን እግዚአብሄር ልጆቹ ይከተሉት ዘንድ የሚያነሳሳቸው?
ልጁን ላከ!
እግዚአብሔር አንድያ ልጁን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ትክክለኛ መንገዱን እንዲያሳየን ላከው።
እግዚአብሔር በማባበል፣ በትዕግሥት፣ በየደግነት፣ በየዋህነት፣ እና ግብዝነት በሌለው ፍቅር በኩል ያነሳሳናል።8 እግዚአብሔር በበኩላችን ነው። ይወደናል እናም ስንደናቀፍ እንደገና ተነስተን እንድንሞክር እና የበለጠ እየጠነከርን እንድንመጣ ይፈልገናል።
እሱ አስተማሪያችን ነው
እሱ ታላቁ እና የምንከባከበው ተስፋችን ነው።
በእምነት ሊያነሳሳን ይመኛል።
ከስህተታችን እንድንማር እና ትክክለኛ ምርጫዎች እንድናደርግ ያምነናል።
ይህም የሚሻል መንገድ ነው!9
የአለም ክፋቶችስ ምንስ ናቸው?
አንዱ ሰዎችን ከምንገዛበት መንገዶች አንዱ በኣለም ውስጥ ስላለ ክፋት በማተኮር እና አንዲሁም በማጋነን ነው።
በእርግጥ ኣለማችን ፍፁም ሆኖ አያnውቅም ወደፊትም ፍፀም አለመሆኑን ይቀጥላል። እጅግ በጣም ንፁሃን ሰዎች በተፈጥሮ ሁንታዎች እና በሰው ኢሰባዊነት ይሰቃያሉ። ይሰቃያሉ።በአሁን ዘመናችን ሙስና እና ውድቀቀት ልዩ እና አስጊ ነው።
እንደዚህ ሀሉ ቢሆንም እንኳን፣ በዚህ ጊዜ መኖርን በማንኛውም ሌላ የአለም ታሪክ ወቀት ጊዜ ለመኖር አለውጠውም። እኛ በማይገኝለት ብልፅግና፣ መገለለፅ እና ጥቅም ከአበከመጠን በለላይ ተባርከናል። ከሁሉም በላይ፣ በዓለም አደጋ ላይ ልዩ አመለካከትን የሚሰጠን እና እንዲሁም የትኛውን መጋፈጥ ወይም ማስወገድ እንዳለብን የሚያሳያን የኢየሱስ ክርስቶስ ሙሉ ወንጌል ስላለን ተባርከናል።
ስለነዚህ በረከቶች ሳስብ፣ እንድንበረከክ እና ለሰማይ አባታችን ለልጆቹ በሙሉ ላለው በምንም ለማያልቀው ፍቅሩ ምስጋና ለማቅረብ እፈልጋለሁ።
እግዚአብሔር ልጆቹ ፈሪ እንዲሆኑ ወይም በዚህ ዓለም ክፋት ውስጥ እንዲኖሩ ይፈልጋል ብዬ አላምንም። “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም።”10
ለመደሰት ብዙ ምክንያቶች ሰጥቶናል። ማግኘት እና ማወቅ ነው የሚያስፈልገን። ጌታ ሁልጊዜ እንደሚያስታውሰን “አትፍሩ፣” “ተደሰቱ”11 እናም “ትንሹ መንጋ፣ አትፍሩ።”12
ጌታ ጦርነታችንን ይዋጋል
ወንድሞች እና እህቶች፣ የጌታ “ትትንሽ መንጋ” ነን። እኛ የኋለኛው ቀኖች ቅዱሳን ነን። በስማችን ውስጥ መሰረቱም የአዳኝን መመለስ የመጠባበቅ እና ዓለምም ይቀበለው ዘንድ የማዘጋጀት ቃልኪዳን ነው። ስለዚህ፣ እግዚአብሔርን እናገልግል እናም ጎረቤቶቻችንን እናፍቅር። ይህንንም በልበ ሙሉነት፣ በትህትና፣ ሌላን ሀይማኖት ወይም ቡድን ዝቅ በማድረግ ሳንመለከት እናከናውነው። “የጊዜውን እና የሰው ልጅ መምጫውን ምልክቶች እናውቅ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል እንድናጠና” እና የመንፈስንም ድምፅ እንድናዳምጥ ተመክረናል።13
ስለዚህም እኛ ስለዚህ ዓለም ፈተኖች ግድየለሾች አይደለንም፤ ወይም የጊዜያችንን አስቸጋሪነት ሳናውቅ ቀርተን አይደለም። ነገር ግን ይህ ማለት እኛንም ሆነ ሌሎችን በፍርሃት ማክበድ አለብን ማለት አይደለም። በፈተናዎቻችን ታላቅነት ላይ በብዙ ከማሰብ፣ መጨረሻ ስለሌለው የእግዚአብሔራችን ታላቅነት፣ መልካምነት፣ እና ፍጹም ሀይል፣ እርሱን በማመን፣ እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ መመለስ በደስተኛ ልብ መዘጋጀት የሚሻል አይደለምን?
እንደ እንደ እርሱ የቃልኪዳን ህዝብነታችን፣ መጥፎ ነገር ሊከሰት ስለሚችሉ በፍርሃት መሽማደድ አያስፈልገንም። በምትኩ፣ፈተናዎች እና እድሎች ወደፊት ሲገጥሙን፤ በእምነት፥ በብርታት፤ በቁርጠኝነት እናም በእግዚአብሄር በማመን ወደፊት መራመድ እንችላለን።14
የደቀመዛሙርትን መንገድ ብቻችንን አይደለም የምንራመደው። “ጌታ አምላክህ…ካንተ ጋራ ይሄዳል፣ አይጥልህምም አይተውህምም።”15
“ጌታ ስለእናንተ ይዋጋላችኋል፤ እናም ሰላማችሁን ታገኛላችሁ።”16
በፍርሃት ፊት፣ ብርታታችንን እናግኝ፤ እምነነታችንን እናዳብር፣ እናም “አንተን ሊጣረር የተሰራ ምንም አይነት መሳሪያ …አይበለፅግም።17
በአስጊ እና ግራ በሚያጋባ ጊዜ ነውን የምንኖረው? በእርግጥም አዎ እንኖራለን።
እግዚአብሄር እራሱ ብሎታል፤ “በዓለም ፈተና ይኖራችኋል፤ ነገር ግን አይዟችሁ፤ እኔ ዓለምን ተወጥቼዋለሁና።”18
በዛ መልኩ የማመንን እና የመተግበርን እምነትን ልንለማመድ እንችላለንን? ቃል በገባንበት እና በቅዱስ ቃል ኪዳኖቻችን ለመኖር እንችላለን? የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን በአስቸጋሪ ጉዳዮች ለመጠበቅ እንችላለን? አዎን እንችላለን።
እግዚአብሔር ቃል ስለገባ፣ “በቅንነት ከተራመዳችሁ እና እርስ በራስ ቃል ኪዳን የገባችሁበትን ቃል ኪዳን ካስታወሳችሁ፣ ሁሉም ነገሮች ለእናንተ በጎነት አብረው ይሰራሉ።”19 ስለዚህ፣ ፍርሀታችንን እንተው እናም በደስታ፣ በትህትና፣ በተስፋ፣ እና ጌታ ከእኛ ጎን እንደሚገኝ ባለን በልበ ሙሉ እምነት እንኖር።
ፍጹም ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ ይጥላል
ውድ ጓደኞቼ፣ በክርስቶስ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ በፍርሀት እና በችንቀት ራሳችን እየኖርን ካገኘን፣ ወይም ቃላቶቻችን፣ ሰባያችን፣ ወይም ስራችን በሌሎች ፍርሀት የሚፈጥሩ ከሆኑ፣ በመለኮት የተሰጠውን ይህን የፍርሀት መዳኒት እናስብበት፥ የክርስቶስ ንጹህ ፍቅር፣ “ፍጹም ፍቅር ፍርሀትን ያሸሻልና።”20
የክርስቶስ ፍፁም ፍቅር የመጉዳትን፣ የማስፈራራትን፣ የመተንኮስን ወይም ሌሎችን የመጨቆንን ፈተናን ይሸረሽራል።
የክርስቶሰ ፍፁም ፍቅር በትህትና፣ በክብር እንደ ተወዳጁ አዳኛችን ደቀመዛሙርትነታችን በደመቀ እምነት እነራመድ ዘንድ ይረዳናል። የክርስቶስ ፍፁም በፍርሃቶቻችንመካከል እንድንገፋ እና ሙሉ እምነታችንን አስተማሪያችን፣ ተስፋችን በሆነው በሰማይ አባታችን ላይ አድርገን እንድንጓዝ ይህን ደማቅ እምነት ይሰጠናል።
በቤታችን ውስጥ፤ በስራቦታችን ውስጥ፣ በቤተክርስትያን ጥሪዎቻችን ውስጥ፣ በሁሉም ከእመነት ሰዎች ጋር ባለን ግንኝነት ውስጥ፣ እናም በራሳችን ልቦናዎቻችን ውስጥ፣ ፍርሃትን በተወዳጃችን ክርስቶስ ፍፁም ፍቅር እንተካ። የክርስቶስ ፍቅር ፍርሀትን በእምነት ይተካል!
የእርሱ ፍቅር በሠማይ አባታችን መልካምነት፣ መለኮታዊ እቅድ፣ በወንጌሉ፣ እና በትእዛዛቱ እምነት ይኑረን።21 በዚህ መንገድ ለእግዚአብሄር ትእዛዛቶች መታዘዛችንን ከሸክም ይልቅ ወደ በረከት ይቀይረዋል። የክርስቶስ ፍቅር ትንሽ ደግ፣ በተጨማሪ መሀሪ፣ የሚንከባከብ፣ እና ለስራው መከናወን ታማኝ የሆንን እንድንሆን ይረዳናል።
ልባችንን በክርስቶስ ፍቅር ስንሞላ፣ በታደሰ መንፈሳዊ ንጹህነት እንነቃለን እናም በደስታ፣ በታማኝነት እናም በውድ አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ብርሀን እና ግርማ ህያው ሆነን እንራመዳለን።
ከሐዋርያው ዮሃንስ ጋር እመሰክራለሁ፣ “በክርስቶስ ፍቅር ውስጥ ፍርሃት የለም።”22 ወንድሞችና እህቶች፣ እግዚአብሔር እናንተን በፍጹም ያውቃችኋል። በፍጹምነት ይወዳችኋል። ወደፊታችሁ ምን እንዳለው ያውቃል። እናንተ “እንዳትፈሩ፣ ግን እንድታምኑ”23 እና “[በፍጹም] ፍቅሩ እንድትኖሩ”24 ይፈልጋችኋል። ይህም ጸሎቴና በረከቴ የሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።