“ከእኔ ጋር ተራመዱ”
የክህነት ትሹመታችን ከጌታ ጋር እንድንራመድ፣ እርሱ እንደሚያደርገው ለማድረግ፣ እርሱ እንደሚያገለግለው እንድናገለግል የሚጋብዘን ነው።
ውድ የክህነት ወንድሞቼ፣ የዚህ ቀን አላማዬ በክህነት አገልግሎታችሁ እንደገና ለእናንተ ለማረጋገጥ፣ እና እናንተን ለማበረታታት ነው። በአንዳንድ መንገዶች፣ ይህም አዳኝ “ የዘለአለም ህይወትን አገኝ ዘንድ፣ ምን መልካም ነገር ላድርግ?” ብሎ ከጠየቀው ከሀብታሙ ወጣት ሰው ጋር በተገናኘበት ጊዜ እንደነበረው እቅድ ጋር አንድ አይነት ነው ቤይ አምናለሁ። (ማቴዎስ 23፥23)። ምናልባት ወደዚህ ጉባኤ የመጣችሁት፣ ይህ ወጣት ሰው ወደ አዳኝ እንደሄደው፣ አገልግሎታችሁ ተቅባይነት እንዳለው አያሰባችሁ ይሆናል። እና በዚህም ጊዜ፣ተጨማሪ መደረግ የሚያስፈልገው እንዳለ—እንዲሁም በጣም የበዝ እንዳለ ይሰማችሁ ይሆናል። ላደረጋችሁት የጌታን አፍቃሪ ተቀባይነት ልነግራችሁ፣ እናምይህን እያደረኩም እያለሁ፣ ከእርሱ እርዳታ ጋር እንደ ቅዱስ የክህነት ተሸካሚዎች ምን ለማከናወን እንደምትችሉ የሚያበረታታ እይታ ልሰጣችሁ እችል ዘንድ እጸልያለሁ።
ሀብታሙ ወጣት ሰው ያለውን ሁሉ እንዲሸጥ እና ለደሀ እንዲሰጥ እና አዳኝን እንዲከተል ተጠይቆ ነበር፤ የወደፊት እድገታችሁ ይህ አያስፈልገውም ይሆናል፣ ግን ይህም ልክ ያለው መስዋዕት ሊያስፈልገው ይችላል። ይህም ቢሆን፣ መልእክቴ እንደ ወጣቱ ሰው “በሀዘን [እንድትሄዱ]” እንዳያደርግ ተስፋዬ ነው። (ማቴዎስ 19፥20–22 ተመልከቱ።) ቢቻል፣ “በደስታ እንደምትሄዱ” ተስፋ አለኝ (ት. እና ቃ. 84፥105) ምክንያቱም እናንተ ለመሻሻል ትፈልጋላችሁና።
ይህም ቢሆን፣ ጌታ እንድናደርግ የጠራንን ስናስብበት ብቁ ያለመሆን ስሜት ሊሰማን ይቻላል። በእርግጥም፣ የክህነት ሀላፊነታችሁን በፍጹም ማማላት እንደምትችሉ ብትነግሩኝ፣ እናንተ ሀላፊነታችሁን አትረዱትም ብዬ አስባለሁ። በሌላም በኩል፣ ስራው ከችሎታችሁ በላይ ነው በማለት ለመተው እንደሰባችሁ ከነገራችሁኝ፣ ከዚያም ጌታ የክህነት ተሸካሚዎቹ በብቻቸው በምንም ለማድረግ የማይችሉትን ለማከናወን እንዴት እንደሚያጎላ እና እንደሚያጠናክር እንድትረዱ መርዳት እፈልጋለሁ።
ይህም በጥሪዬ እውነት እንደሆነው በእናንተም ጥሪ እውነት ነው። በራሳችን ጥበብ እና ችሎታ ብቻ በመመካት የክህነት ስራን ለመስራት፣ እናም በደንብ ለማከናወን፣ ማንኛችንም አንችልም። ለዚያም ምክንያት ይህ የኛ ስራ አይደለም—ይህም የጌታ ስራ ስለሆነ ነው። ስለዚህ፣ ወደ ቅዱስ ቁርባን ስርዓት የመንፈስ ሀይል ለማምጣት ስራ በእምነት የተሰጣችሁ አዲስ የተጠራችሁ ዲያቆናት ብትሆኑም፤ ወይም የማታውቋቸውን እና የእናንተን ፍቅር ወይም አገልግሎት የማይፈልጉ ለሚመስሉት ቤተሰቦች እንድታፈቅሩና እንድታገለግሉ የተጠራችሁ ወጣት የቤት ለቤት አስተማሪዎች ብትሆኑም፤ ወይም በቤታችሁ በጻድቅ መምራት እንዳለባችሁ የምታውቁ፣ ግን ይህን እንዴት እንደምታደርጉ የማታውቁ፣ ምክንያቱም ልጆች በፍጥነት ስለሚያድጉ እና አለም በጣም ሀይለኛና ጥለኛ የሚመስልበት አባት ብትሆኑም፣ ውጤታማ የምትሆኑበት መንገድ በእርሱ መመካት ነው።
ስለዚህ ትንሽ የምትጥለቀለቁ ስሜት ከኖራችሁ፣ ይህን እንደ መልካም ምልክት እዩት። ይህም እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ያለውን ታላቅ እምነት የሚያመለክት እንደሆነ ሊሰማችሁ ይችላል። ይህም እናንተ ክህነት በእውነት ምን እንደሆነ ትንሽ ግንዛቤ አላችሁ ማለት ነው።
አለም ውስጥ ይህ ግንዛቤ ያላቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው። ጥሩ የሆነ ትርጉም ለመስጠት የሚችሉትም በእውነት ላይረዱት ይችላሉ። በሚሸከሙት የመንፈስ ሀይል በኩል፣ ስለቅዱስ ክህነት የዘለቀ ድንቀት እንዲኖረን የሚያደርጉ አንዳንድ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሰቶች አሉ። ከእነዚያ የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሰቶች አንዳንዶቹ በዚህ ይገኛሉ፥
“ ... የመልከጼዴቅ ክህነት፣ ሀይል እና ስልጣን በቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ በረከቶች ላይ ሁሉ ቁልፎችን መያዝ ነው—
“በተጨማሪም፣ የመንግስተ ሰማያትን ሚስጥራት ለመቀበል ልዩ መብት እንዲኖረው፣ ሰማያት ለእነርሱ እንዲከፈቱላቸው፣ ከበኩሩ ቤተክርስቲያንና ከአጠቃላይ ተሰብሳቢዎች ጋር እንዲገናኝ፣ እና ከእግዚአብሔር አብ እና ከአዲስ ኪዳን አማላጅ ከሆነው ከኢየሱስ ጋር መገናኘትን እና በእነርሱም መገኘት ለመደሰት ነው።
“የአሮናዊ ክህነት፣ ሀይል እና ስልጣን፣ የመላእክትን አገልግሎት ቁልፎች መያዝ ... ነው” (ት. እና ቃ. 107፥18–20)።
“ስለዚህ፣ በዚህም ስርዓት ውስጥ፣ የአምላክ አይነት ሀይል ይታያል። …
“ካለዚህ ማንም ሰው የእግዚአብሔርን ፊት፣ እንዲሁም አብን፣ ለመመልከት እና ለመኖር አይችልም” (ት. እና ቃ. 84፥20፣ 22)።
“ይህም ታላቁ ክህነት ከአለም መፈጠር ጀምሮ ከነበረው ከወልድ ሥርዓት መሰረት ነው፤ ወይም በሌላ አነጋገር፣ መነሻ ቀናት ሆነ ፍፃሜ አመታት የሌለው፤ ለሁሉም ነገር በቀደመው እውቀቱ መሰረት ከዘለዓለም እስከዘለዓለም የተዘጋጀ ነው” (Alma 13:7).
“እያንዳንዱ በዚህ ስርዓት የሚሾመውና የሚጠራው በእምነት ተራራዎችን ለመስበር፣ ባህሮችን ለመከፋፈል፣ ውሀዎችን ለማድረቅ፣ ከመንገዳቸው ለማዞር፤
“የህዝቦችን ሰራዊቶች በግልፅ ለመቃወም፣ ምድርን ለመከፋፈል፣ እያንዳንዱን ቡድን ለመስበር፣ በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም፣ ሁሉንም ነገሮች በፍላጎቱ መሰረት፣ በትእዛዙ መሰረት ለማድረግ፣ ግዛትንና ሀይላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል፤ እና ይህም ከአለም መሰረት በፊት በነበረው በእግዚአብሔር ልጅ ፍላጎት ነው” (የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘፍጥረት 14፥30–31 [in the Bible appendix])።
ለእነዚህ ድንቀት ለሚያመጡ የክህነት ሀይል መግለጫዎች መልስ ለመስጠት የሚቻልበት አንዱ መንገድ እነዚህ እኛ ልንተገብራቸው የማንችላቸው ናቸው ብሎ ማሰብ ነው። ሌላ መልስ የሚሰጥበት መንገድ ነፍስን በሚፈትሽ ጥያቄዎች እንደዚህ አይነት ጥያቆእዎች በልባችን ውስጥ በመጠየቅ ነው፥ ሰማያት ለእኔ ተከፍተውልኝ እንደነበረ ተሰምቶኛልን? የክህነት አገልግሎቴን “የመላእክት አገልግሎት” ብሎ ማንም ሊገልጸው ይችላልን? “የአምላክነት ሀይልን” ወደ ማገለግላቸው ሰዎች ህይወት አመጣለሁን? በምሳሌም ቢሆን፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማሟላት ተራራን ሰብሬ፣ ሰራዊትን ተቃውሜ፣ የሰውን እስራት ሰብሬ፣ ወይም አለማዊ ሀይሎችን አሸንፌ ነበርን?
እንደዚህ አይነት ራስን መመርመር በጌታ አገልግሎት ውስጥ ተጨማሪ ለማድረግ የምንችልበት ስሜት ሁልጊዜም ያመጣል። ይህም ደግሞ እናንተ ተጨማሪ ለማድረግ እንድትፈልጉ የሚያስፈልግ ስሜት እንዲኖራችሁ—በጌታ ታዕምራዊ ስራ በሙሉ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዲኖራችሁ ተስፋ አለኝ። እንደዚህ አይነት ስሜት የክህነት አገልግሎት እንዲፈጥር የሚያደርገው አይነት ሰው ለመሆን የምትወስዱት የመጀመሪያው እርምጀ ነው።
ቀጣዩ እርምጃም በያህዌ እና በሔኖክ መካከል በነበረው ግንኙነት ተገልጿል። ሔኖክ በታላቅ ክፋት መካከል ፅዮንን የመሰረተ ሀይለኛ ነቢይ እንደነብር ኣውቃለን። ሀይለኛ ነቢይ ከመሆኑ በፊት ግን፣ ሔኖክ ራሱን “እንደ ልጅ፣ … አፉ ኮልታፋ” እናም በሁሉም ሰው የማይወደድ እንደሆነ ይመለከት ነበር (ሙሴ 6፥31)። ሔኖክን ለማበረታታት ጌታ የተጠቀማቸውን ቃላት አድምጡ። እነዚህም እንደ ክህነት ተሸካሚዎች ሌሎችን ለማገልገል ለተጠራችሁት ያሱ ቃላትም ናቸው።
“ጌታም ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ ሂድና እንዳዘዝኩህ አድርግ፣ እናም ማንም አይጎዳህም። አፍህን ክፈት፣ እናም ይሞላል፣ እኔም የምትናገረውን እሰጥሀለሁ፣ ሁሉም ስጋ ለባሽ በእጄ ላይ ነውና፣ እና መልካም እንደሚመስለኝም አደርጋለሁ። …
“እነሆ መንፈሴ በአንተ ላይ አርፏል፣ ስለዚህ ቃላትህን ሁሉ አጸድቃለሁ፤ ተራሮችም ከአንተ ፊት ይሸሻሉ፣ እናም ወንዞችም ከመንገዳቻው ይዞራሉ፤ አንተም ከእኔ ጋር ኑር፣ እና እኔም ከአንተ ጋር፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር ተራመድ።” (ሙሴ 6፥32፣ 34)።
ወንድሞች፣ የክህነት ትሹመታችን ከጌታ ጋር እንድንራመድ ግብዣ ነው። ከጌታ ጋር መራመድ ምን ማለት ነው? ይህም እርሱ እንደሚያደርገው ማድረግ፣ እርሱ እንደሚያገለግለው ማገልገል ነው። ሌሎች በሚያስፈልጋቸው ለመባረክ የራሱን ምቾት መስዋዕት አደረገ፣ ስለዚህ ይህንን ነው መድረግ የሚንፈልገው። የተረሱትን እናም በህብረተሰብ የተወገዱትን ሰዎች ላይ ልዩ ትኩረት አደረገ፣ ስለዚህ እኛም እነዚያን መሞከር ያስፈልገናል። ምንም እንኳን ታዋቂ ባይሆንም፣ በጀግንነት ቢሆንም በፍቅር ከአባቱ ስለተቀበለው ትምህርት እውነትነት መሰከረ፣ እናም እኛ እንደዚህ ማድረግ ይገባናል። እርሱም ለሁሉም “ወደ እኔ ኑ” (ማቴዎስ 11፥28) አለ፣ እናም እኛ ለሁሉም “ወደ እርሱ ኑ” እንላለን። እንደ ክህነት ተሸካሚዎች፣ እኛ የእርሱ ወኪሎች ነን። የምንሰራው ለራሳችን ሳይሆን ለእርሱ ነው። የምንናገረ የራሳችንን ቃላት ሳይሆን የእርሱን ነው። በአገልግሎታችን ምክንያት የምናገለግላቸው ሰዎች እርሱን በተሽለ ያውቁታል።
“ከእኔ ጋር ሂዱ” የሚለውን የጌታን ግብዣ ልክ እንደተቀበልን፣ የክህነት አገልግሎታችን ሁኔታ ይቀየራል። ሁሉም በአንዴ ከፍተኛ እና ደግሞም የሚቻልበት ይሆናል፣ ምክንያቱም እኛ ብቻችንን እንዳልሆንን እናውቃለንና። ይህም የተሰማኝ ከዘጠኝ አመት በፊት ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን በራሴ ላይ እጆቻቸውን ጭነው አሁን በማገለግልበት ጥሪ አገልግሎቴን ስጀምር ነበር። በዚያ በረከት ውስጥ፣ የአዳኝን ቃላት ደግመው አሉ፥ “እናም የሚቀበሏችሁም፣ በእዚያም እገኛለሁ፣ በፊታችሁ እሄዳለሁና። በቀኛችሁ እና በግራችሁ እሆናለሁ፣ እናም መንፈሴም በልቦቻችሁ ውስጥ ይገኛል፣ እናም መላእክቶቼም እንዲያዝሏችሁ ይከብቧችኋል” (ት. እና ቃ. 84፥88)።
በዚያ የተስፋ ቃል ላይ ለብዙ ጊዜያት እመካለሁ፣ እናም በ72 አመት አገልግሎቴ ይህም በብዙ መንገዶች ሲሟላ ተመልቻለሁ። ይህም ቅዱስ ቁርባል የማካፍልበት ሀላፊነት በነበረብኝ እንደ አዲስ የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚ በነበርኩበት ጊዜም ደረሰ። ስህተት እሰራለሁ ብዬ በመፍራት፣ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት በመሰብሰቢያው ውጪ መጣሁ እናም እግዚአብሔር እንዲረዳኝ በጣም በመፈለግ ጸለይኩኝ። መልሱም መጣ። ጌታ ከእኔ ጋር እንደሚገኝም ተሰማኝ። በእኔ ላይ ያለው እምነት ተሰማኝ፣ እና ስለዚህ በስራው ባለኝ ክፍልም እምነት ተሰማኝ።
ይህም እንደ ኤጲስ ቆጶስ ሳገለግል እንደገና ሆነ። ትልቅ ስህተት ካደረገች እና አሁን ታላቅ አስቸጋሪ፣ ህይወት የሚቀይር ውሳኔ ከገጠማት አንዲት ሴት የስልክ ጥሪ ተቀበልኩኝ። ከእርሷ ጋር ስገናኝ፣ ለችግሯ መልስ ምን እንደሆነ እንደማውቅ ተሰማኝ፣ ነገር ግን እኔ ያን መልስ መስጠት እንደማይገባኝ ጠንካራ ስሜት ተሰማኝ—ይህንን ራሷ ማግኘት ያስፈልጋታልና። ለእርሷ የሰጠኋት ቃላትም “ከጠየቅሽው እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንደሚገባሽ ይነግርሻል” የሚል ነበር። በኋላም እርሱን እንደጠየቀችና፣ እርሱ እንደነገራት ነገረችኝ።
በሌላ ወቅት፣ ኤጲስ ቆጶስ እያለሁ ሌላ የስልክ ጥሪ መጣ፣ እናም በዚህ ጊዜ ከፖሊስ ነበር። የሰከረ መኪና ነጂ መኪናውን የባንክ መተላለፊያ ገጭቶ በመስኮቱ እንደገባ ተነገረኝ። የደነገጠው መኪና ነጂ ወታደሩ መሳሪያውን ማውጣቱን ሲመለከት ጊዜ፣ እንዲህ ጮኸ፣ “አትተኩስ! “እኔ ሞርሞን ነኝ!”
የሰከረው የመክና ነጂ በቅርብ የተጠመቀ የዎርዴ አባል ነበር። በኤጲስ ቆጶስ ቢሮዬ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ስጠብቅ፣ ቃል ኪዳኑን በመስበሩ እና ቤተክርስቲያኗን በማሳፈሩ ምክንያት ፀፀት እንዲሰማው ለማድረግ ምን እንደምለው እቅድ ነበረኝ። ነገር ግን ልክ ስመለከተው፣ በአዕምሮዬ፣ ልክ አንድ ሰው እኔን እንደሚያናግረኝ አይነት፣ “እርሱን እኔ እንደምመለከተው እንድታየው አደርግሀለሁ” የሚል ድምፅ ሰማሁ። ከዚያም፣ ለጥቂት ጊዜ፣ የእርሱ መልክ ለእኔ በሙሉ ተቀየረ። የማየው የደነገጠ ወጣት ሰው ሳይሆን፣ ግን ብሩህ፣ ክብር ያለው የእግዚአብሔር ልጅ ነበር። ጌታ ለእርሱ ያለው ፍቅር በድንገት ተሰማኝ። ያም ራዕይ ንግግራችንን ቀየረው። ይህም እኔን ቀየረኝ።
ከጌታ ጋር ስራውን በመስራት በነበሩኝ ከእነዚህ አጋጣሚዎች አስፈላጊ ትምህርቶችን ተማርኩኝ። ከእናንተ ጋር ሶስቱን ለመካፈል እፈልጋለሁ። የመጀመሪያው እግዚአብሔር አዲስ እና ከሁሉም ታናሽ የሆነውን ዲያቆን ያያል እናም ይደግፋል። እናንተን ወይም በእርሱ ስም የምትሰጡትን አገልግሎት ለማየት እናንተ ከሁሉም ያነሰን እና አስፈላጊ ያልሆንን ነን ብላችሁ በምንም አታስቡ።
ሁለተኛው ትምህርትም የጌታ ስራ ለችግሮች መፍትሄ ማግኘት ብቻ አይደለም፤ ይህም ሰዎችን መገንባት ነው። በክህነት አገልግሎት ከእርሱ ጋር ስትራመዱ፣ አንዳንዴ ከሁሉም ይበልጥ መልካም የሚመስለው መፍትሄ በጌታ ይሚፈለገው መፍትሄ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፣ ምክንያቱም ይህ ሰዎች እንዲያድጉ አይፈቅድምና። ካዳመጣችሁ፣ እርሱ መንገዱን ያስተምራችኋል። የእግዚአብሔር ስራ እና ክብር ውጤታማ የሆነ ድርጅት ማስተዳደር ብቻ አይደለም፤ ይህም “የሰውን አለሟችነት እና የዘላለም ህይወት ለማምጣት ነው”(ሙሴ 1፥39)። ለዚህ ነው የክህነት ሰልጣኑን እንደ እናንተ እና እኔ አይነት ፍጹም ላልሆኑ ሟቾች የሰጠው እናም በስራው እንድንሳተፍ የሚጋብዘን። እድገታችን የእርሱ ስራ ነው!
አሁን ሶስተኛው ትምህርት ከአዳኝ ጋር በክህነት አገልግሎቱ በመሄድ ሌሎችን የምትመለከቱበት መንገድ ይቀየራል። በእርሱ አይን እንድትመለከቷቸው ያስተምራችኋል፣ ይህም ማለት የውጪ አስተያየትን ችላ በማለት በልብ ውስጥ ያለውን ማየት ነው (1 ሳሙኤል 16፥7 ተመልከቱ)። ለዚህ ነው አዳኝ ስምዖንን እንደ ቸኳይ የአሳ አጣምጅ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ፣ እንደ ቤተክርስቲያኗ ወደፊት መሪ ያየው (ሉቃስ 5፥1–11 ተመልከቱ)። ለዚህ ነው እርሱ ዘካሪያስን ሌሎች እንደሚያዩት እንደተበላሸ ቀረጥ ሰብሳቢ ሳይሆን እንደ ታማኝ፣ ጎበዝ፣ እና መልካም የአብርሐም ልጅ ነው ለማየት የቻለው (Luke 19:1–9 ተመልከቱ)። ከአዳኝ ጋር ለረጅም ጊዜ ከሄዳችሁ፣ ሁሉንም ያለፈው ታሪካቸው ምንም ቢሆን፣ ለችሎታቸው ገደብ የሌላቸው፣ እንደ እግዚአብሔር ልጆች ለማየት ትማራላችሁ። ከአዳኝ ጋር ለመሄድ ከቀጠላችሁ፣ እርሱ ያለውን ሌላ ስጦታ ታደብራላችሁ—ይህም ሰዎች በራሳቸው ውስጥ ያላቸውን ችሎታ ለማየት እንዲችሉ እና ንስሀ እንዲገቡ ማድረግ ነው።
ውድ የክህነት ወንድሞቼ፣ በብዙ መንገዶች፣ እኛ በዚያች የመጀመሪያ ትንሳኤ እሁድ ወደ ኤማሁስ እንደተጎዙት ሁለቱ ደቃ መዛሙርት ነን። ይህ የትንሳኤ ጠዋት ነበር፣ ነገር ግን ትንሳኤ እንደነበር ወይም ትንሳሔ ምን ማለት እንደሆነ ጥርጣሬ ነበራቸው። “እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ” አደርገው ነበር፣ ግን ቅዱሳት መጻህፍት ስለትንሳኤ ያስተማሩትን ነገሮች “በልብ ለማመን” ዘግይተው ነበር። አብረው ሲጓዙ እና አብረው ሲያሰላስሉ፣ “ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።” (ሉቃስ 24፥13–32 ተመልከቱ።)
በክህነት አገልግሎት መንገድ ስንጓዝ፣ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር እንደሚጓዝ እመሰክራለው፣ ይህም የእርሱ መንገድ፣ የእርሱ ጎዳና ነውና። ብርሀኑ በፊታችን ይሄዳል፣ እናም መላእክቱ ይከብቡናል። ክህነት ምን እንደሆነ ወይም እርሱ እንደሚያደርገው እኛ እንዴት እንደሚጠቀምበት ሙሉ ግንዛቤ አይኖረን ይሆናል። ነገር ግን “ልባችን በሚቃጠልበት” (ሉቃስ 24፥32) ጊዜዎች ትኩረት ከሰጠን, አይኖቻችን ሊከፈቱ ይችላሉ፣ እናም እጁን በህይወታችን እና በአገልግሎታችን ውስጥ እናያለን። እርሱን በደንብ ለማወቅ የምንችለው ከእርሱ ጋር በመስራት እና ደህንነትን ለእግዚአብሔር ልጆች ለማምጣት ባለው ታላቅ ስራ እርሱን በማገልገል ነው። “ያላገለገለውን አለቃ፣ እና እንግዳውን ከልቡ ስሜትና ሀሳብ የራቀውን፣ አንድ ሰው እንዴት ያውቃል?” (ሞዛያ 5፥13)። ኢየሱስ ክርስቶስ መምህራችን ነው። ይህችም ቤተክርስቲያኑ ነች። የተሸከምነው ክህነትም የእርሱ ነው። እናንዳንዳችን ከእርሱ ጋር ለመሄድ እና እርሱ እንዴት ከእኛ ጋር እንደሚሄድ ለማወቅ እንቻል።
ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ከሞት የተነሳው ጌታ እንደሆነ የልብ ምስክሬን እሰጣችኋለሁ። ለእኛ በእምነት የሰጠው ክህነት በእርሱ ስም የመናገር እና የመስራት ሀይል እንደሆነ እመሰክራለሁ። ጸሎትን የሚመልስ እና እንድናገኘው በተበረክነው በእያንደንዱ የክህነት ሀላፊነት እኛን ሊያጠናክረን መንፈስ ቅዱስን የሚልክ የአፍቃሪ የሰማይ አባት ልጆች ነን። ጆሴፍ ስሚዝ አብ እና ወልድን አይቷል። ወደ ፕሬዘደንት ቶማስ ሴስ. ሞንሰን የተላለፉትን፣ እና አሁንም የሚጠቀሙባቸውን፣ የክህነት ቁልፎች ተቀብሏል። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።