2010–2019 (እ.አ.አ)
ማስጠንቀቂያ ድምፅ
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


15:15

ማስጠንቀቂያ ድምፅ

የማስጠንቀቅ ሀላፊነት በነቢያት በጥብቅ የሚሰማ ቢሆንም፣ ይህም የሚካፈሉት ሀላፊነት ነው።

ነቢዩ ሕዝቅኤል ሌሂ ከኢየሩሳሌም ከመውጣታቸው ሀያ አመታት በፊት ነበር የተወለደው። በ597 ም.ዓ.፣ በ25 አመቱ፣ ሕዝቅኤል በናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከተወሰዱት ብዙዎች መካከል አንዱ ነበር፣ እናም ለማወቅ በምንችለው ያህል፣ ህይወቱን በሙሉበዚያ ነበር ያሳለፈው።1 እርሱም የአሮናዊ ክህነት ትውልድ ነበር፣ እናም በሰላሳ አመቱ ነቢይ ሆነ።2

ሕዝቅኤልን በመመደብ፣ ያህዌ የጠባቂ ምሳሌን ተጠቀመ።

“[ጉበኛውም] በምድር ላይ የመጣውን ሰይፍ ባየ ጊዜ መለከትን ቢነፋ ሕዝቡንም ቢያስጠነቅቅ፤”

“የመለከቱን ድምፅ የሚሰማ ሰው ባይጠነቀቅ፥ ሰይፍ መጥቶ ቢወስደው፥ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል።”3

በሌላም በኩል፣ “ጕበኛው ግን ሰይፍ ሲመጣ ቢያይ መለከቱንም ባይነፋ ሕዝቡንም ባያስጠነቅቅ ሰይፍም መጥቶ አንድ ሰው ከእርሱ ቢወስድ፥ … ደሙን ግን ከጕበኛው እጅ እፈልጋለሁ።”4

ከዚያል ለሕዝቅኤል በቀጥታ በመናገር፣ ይህዌ እንዲህ አወጀ፣ “አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ጕበኛ አድርጌሃለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ ከእኔም ዘንድ አስጠንቅቃቸው።5 ማስጠንቀቂያውም ከኃጢያት እንዲዞር ነው።

“ኃጢአተኛውን። ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ ታስጠነቅቅ ዘንድ ባትናገር ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።

“ነገር ግን ከመንገዱ ይመለስ ዘንድ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል። …

“እኔም ኃጢአተኛውን። በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፤ …

“የሠራው ኃጢአት ሁሉ አይታሰብበትም፤ ፍርድንና ቅን ነገርን አድርጎአል፤ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።”6

በሚያስገርም ሁኔታ፣ ይህ ማስጠንቀቂያ ለጻድቅነትም ለመጠቀም ይቻላል። “እኔ ጻድቁን፣ በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ በጽድቁ ታምኖ ኃጢአት ቢሠራ በሠራው ኃጢአት ይሞታል እንጂ ጽድቁ አይታሰብለትም።”7

ልጆቹን በመለመን፣ እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን ነገረው፣ “እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ?”8

ለማውገዝ የሚጨነቅ ሳይሆኑ፣ “ክፉት በፍጹም ደስታ ሆኖ ስለማያውቅ”9 የሰማይ አባታችን እና አዳኛችን ደስታችንን ፈለጉ እናም ንስሀ እንድንገባ ለመኑን። ስለዚህ ሕዝቅኤል እና ከእርሱ በፊትና በኋላ የነበሩ ነቢያት፣ ከሞላ ልብ የእግዚአብሔርን ልብን በመናገር፣ ፈቃደኛ የሆኑትን ሁሉ፣ ከነፍሳቸው ጠላት፣ ከሰይጣን እንዲዞሩ እና “በሚማልደው አማካኝነት ነፃነትን ወይም ዘለዓለማዊ ህይወትን”10 እንዲመርጡ አስጠንቅቅውዋል።

የማስጠንቀቅ ሀላፊነት በነቢያት በጥብቅ የሚሰማ ቢሆንም፣ ይህም የሚካፈሉት ሀላፊነት ነው። በእርግጥም፣ “የተጠነቀቀው ሰው ባልንጀራውን ማስጠንቀቁ አስፈላጊ ነው።”11 የታላቁ የደስታ እቅድ እውቀትን—እና ከዚህ ጋር የተያያዙትን ትእዛዛት—የተቀበልነው ያን እውቀት ለመካፈል ፍላጎት ሊሰማቸው ይገባል፣ ይህም በዚህ ህይወት እና በዘለአለም ሁሉንም ልዩነት ያመጣልና። “የማስጠነቅቀው ባልንጀር ማን ነው?” ብለን ከጠየቅን፣ በእርግጥም በዚህ በሚጀምረው ምሳሌ ውስጥ ይገኛል፣ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፣ [እናም ይቀጥላል]።”12

ስለመልካም ሰማርያ ምሳሌን በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ ማሰብ፣ “ባልንጀራዬ ማን ነው?” የሚለው ጥያቄ ከሁለቱ ትእዛዛት ጋር የተሳሰረ እንደሆነ እንድናስታውስ ያደርጋል። “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ።”13 የማስጠንቀቂያ ድምጽን የሚያነሳሳው ፍቅር፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እና የባልንጀራ ፍቅር ነው። ማስጠንቀቅ እና መንከባከብ ነው። የጌታ ይህን የሚደረገው “በደግነት እና በትህትና”14 እና “በማሳመን፣ በትእግስት፣ በደግነት … ፣ እና ግብዝነት በሌለው ፍቅር”15 ነው። ትንሽ ልጅን በእጁ እሳት እንዳይነካ እንደምናስጠነቅቅ፣ ይህም አስፈጣኒ ለመሆን ይችላል። ይህም ግልጽ እና አንዳንዴም ጠንካራ መሆን ያስፈልገዋል። አንዳንዴም፣ ማስጠንቀቂያ “መንፈስ ቅዱስ በሚነሳሳበት ጊዜ”16 የተግሳጽ ቅርጽ ሊኖረው ይችላል፣ ነገር ግን ይህም በፍቅር ላይ የተተከለ ነው። ለምሳሌ ሚስዮናችንን ለአገልግሎት እና ለመስዋዕት የሚያነሳሳውን ፍቅር ተመልከቱ።

በእርግጥም የቅርብ “ባልንጀራቸው” የሆኑትን፣ ልጆቻቸውን፣ ለማስጠንቀቅ ፍቅር ይገፋፋቸዋል። ይህም ማለት የወንጌልን እውነት ማስተማር እና መመስከር ነው። ይህም ልጆችን የክርስቶስ ትምህርትን፥ እምነት፣ ንስሀ መግባት፣ ጥምቀት፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ማስተማር ነው።17 ጌታ ወላጆች እንዲያስታውሱት እንዳደረገው፣ “ልጆቻችሁን በብርሀን እና በእውነት እንድታሳድጓቸው ዘንድ አዛችኋለሁ።”18

የማስጠንቀቅ የወላጅ ሀላፊነት አስፈላጊ ጉዳይ ተስፋ የሚያስቆርጥ የኃጢያት ውጤትን ብቻ ሳይሆን ደግሞም በትእዛዛት ታዛዥነት የመራምድ ደስታን ለማሳየት ነው። ኤኖስ እግዚአብሔርን ለመፈለግ፣ የኃጢያት ስርየትን ለማግኘት፣ እና ለመቀየር ምን እንዳነሳሳው እናስታውስ፥

“እነሆ፣ አራዊትን ለማደን ወደጫካው ሄድኩ፤ እናም አባቴ ዘለዓለማዊ ህይወትንና እና የቅዱሳን ደስታ በተመለከተ ሁልጊዜ ሲናገር የምሰማቸው ቃላት ወደልቤ ጠልቀው ገቡ።

“እናም ነፍሴ ተራበች፤ በፈጣሪዬም ፊት ተንበረከክሁ፣ እናም ለነፍሴ በሀይለኛ ፀሎትና ልመና ወደእርሱ ጮህኩኝ።”19

ለመነጻጸር በማይቻለው ፍቅሩ እና ለሌሎችና ለእነርሱ ደስታ ባለው ሀሳብ ምክንያት፣ ኢየሱስ ለማስጠንቀቅ አላመነታም። በአገልግሎቱ መጀመሪያ፣ “ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፣ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።”20 ማንኛውም መንገድ ወደ ሰማይ እንደማይመራ ስላወቀም፣ እንዲህ አዘዘ፥

“በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤

“ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።”21

እንዲህም በማለት ለኃጢያተኞችም ጊዜውም ሰጠ፣ “ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም”22

ስለጸሀፊዎች፣ ስለፈራሲዎች፣ እና ስለሰዱቃውያን፣ ኢየሱስ የእነርሱን ግብዝነት በማውገዝ በምንም አላወላወለም። የእርሱ ማስጠንቀቂያዎች እና ትእዛዛት ቀጥተኛ ነበሩ፥ “እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።”23 በእርግጥም አዳኝ እነዚህን ጸሀፊዎች እና ፈራሲያንን አይወድም ብሎ የሚከስ ማንም የለም–ለእነርሱም ቢሆን ለማዳን ተሰቃይቶ ሞቷልና። ነገር ግን እነርሱን በማፍቀር፣ በግልጽ ሳያስተካክላቸው በኃጢያት እንዲቀጥሉ ለመፍቀድ አልቻለም። አንድ ተመልካች እንዳስመለከተው፣ “ኢየሱስ ተከታዮቹ እርሱ እንዳደረገው እንዲያደርጉ አስተምሯል፣ ሁሉንም ለመቀበል ግን ደግሞም ሁሉንም ስለኃጢያት ማስተማር፣ ፍቅር ሰዎችን ስለሚጎዳቸው ማስጠንቀቅድን ያስገድዳልና።”24

አንዳንዴ የማስጠንቀቂያ ድምጽን የሚያነሱት እንደሚፈርሱ ሰዎች ዝም ይባላሉ። በሚያስገርም ሁኔታ ግን፣ እውነት አንጻራዊ ነው የሚሉት እና የምግባር መሰረቶች የግል ምርጫ ጉዳይ ነው የሚሉት የአሁን “የትክክለኛ አስተሳሰብ” ደንብ የማይቀበሉትን ሰዎች በብዛት የሚተቹት ናቸው። አንድ ጸሀፊ ይህን “የሚያሳፈር ባህል” ብሎ ጠርቶታል።

“በበደል ባህል ውስጥ መልካም ወይም መጥፎ እንደሆናችሁ የምታውቁት በህሊናችሁ ስሜት ነው። በሚያሳፍር ባህል መልካም ወይም መጥፎ እንደሆናችሁ የምታውቁት ህብረተሰባችሁ ስለእናንተ በሚሉት፣ እናንተን በማክበር ወይም በመለየት ነው”” … [በሚያሳፍር ባህል፣] ስጋዊ ህይወት በትክክል እና በስህተት ቀጣይነት ላይ የተገነባ አይደለም፣ ይህም በማካተት እና በማግለል ቀጣይነት ላይ የተገነባ ነው። …

“… ሁሉም ሰው በማካተት እና በማግለል ላይ የተመሠረተ የሥነ ምግባር ሥርዓት ውስጥ በምንም ያልረጋ ህይወት አላቸው። ምንም ቋሚ መሰረት የለም፣ ያለው የሚቀያየር የህዝብ ፍርድ ነው። ይህም የተጋነነ፣ የሚቆጣ እና ሁልጊዜም በስነምግባር የሚደነግጥ ባህል ነው፣ በዚህም ሁሉም ለመከተል ይገፋፋሉ። … 

“የሚያሳፍር ባህል አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ኃጢያትን ለመጥላት እና ኃጢያተኞችን ለማፍቀር ትችላላችሁ። የዚህ ዘመን የሚያሳፍር ባህል ማካተት እና ቻይነትን ከፍ አድርጎ ይመለከተዋል፣ ነገር ግን ለማይስማሙት እና በቡድኑ ተገቢ ላልሆኑት ይህም በሚያስደንቅ ሁኔታ ምህረት የሌለው ነው።”25

ይህም “ከደህንነት አለትን፣”26 የፍትህ እና የበጎነት የተረጋጋ እና ቋሚ መሰረት፣ ጋር ይነጻጸራል። በማይገመት የህብረተሰብ ማስተላለፊያ ህግ እና ቁጣ እንደ ምርኮ ከመያዝ፣ እጣ ፈንታችንን ለመምረጥ እና ለመቆጣጠር የምንችልበት የማይቀየር የእግዚአብሔር ህግ መኖሩ እንዴት የሚሻል ነው። “በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን”27 ከመሆን እውነትን ማወቅ እንዴት የሚሻል ነው። ምንም ትክክል ወይም ስህተት የለም በማለትና በኃጢያትና በጸጸት ከመንጎሳቀል ስንሀ በመግባትና በወንጌል መሰረት ከፍ መደረግ እንዴት የሚሻል ነው።

ጌታ እንዳወጀው፣ “በመጨረሻዎቹ ቀናት፣ እኔ በመረጥኳቸው ደቀመዛሙርቶቼ አንደበት፣ የማስጠንቀቂያው ድምጽ ለሁሉም ህዝብ ይሆናል።”28 እንደ ጉበኛ እና ደቀመዛሙርት፣ “ስለሚበልጠው መንገድ”29 ገለልተኛ መሆን አንችልም። እንደ ሕዝቅኤል፣ ሰይፍ በምድር ላይ ሲመጣ እያየን “መለከትን የማንነፋ”30 ለመሆን አንችልም። አለማስጠንቀቅ ፍቅር ሳይሆን ችላ ማለት ነው፤ ይህም መቀበል ሳይሆን ትቶ መሄድ ነው። በእውነትም፣ ይህን ስታስቡበት፣ በዳግም በተመለሰው ወንጌል ውስጥ ሰዎች በጥልቅ ውስጣቸው የሚፈልጉት ነው ያለን። ስለዚህ የሚያስጠነቅቀው ድምጽ ሰላምተኛ ብቻ ሳይሆን፣ የዘማሪው ሀረግ ውስጥ እንደሚገኘው “የድሰታ ጩኸት” ነው።31

Deseret News አስተያየት ጸሀፊው ሀል ቦይድ ዝም በማለት አገልግሎት የማይሰበትን ምሳሌ አሳይቷል። የጋብቻ አስተያየት በአሜሪካ ህብረሰብ ልሂቃን መካከል “የመምህራን ክርክር” ቢሆንም፣ ጋብቻ ራሱ በሚጠቀሙበት የክርክር ጉዳይ አይደለም ብሎ አስመልክቷል። “‘ልሂቃን ያገባሉ እናም በጋብቻ ይቆያሉ እናም ልጆቻቸው የተረጋጋ ጋብቻ ጥቅምን እንዲደሰቱበት ያረጋግጣሉ።’ … ችግሩ ግን የሚኖሩበትን አለመስበካቸው ነው።” ስነ ምግባር መሪነታቸው ለመጠቀምና ከዚህ ዋጋ ለማግኘት በሚችሉት ላይ “ለማስገደድ” አይፈሉም፣ ግን “ትምህርት እና ጠንካራ ቤተሰብ ያላቸው የገለልተኝነት መንጋጋን ማቆም እና ስለጋብቻና ወላጅነት በሚመለከት የሚኖሩበትን መስበክ የሚጀምሩበት ጊዜ አሁን ነው።”32

እናንተ የምትነሱት ትውልዶች፣ በሚመጡት አመታት ጌታ ለስራው ውጤታማነት የሚመካባችሁ ወጣቶች እና ያላገባችሁ ጎልማሳዎች፣ የወንጌል ትምህርትንና የቤተክርስቲያኗን መሰረቶች በይፋዊ እንዲሁም በግል እንደምትደግፉ እምነት አለን። እውነትን የሚቀበሉትን ባለማወቅ እንዲወድቁ ትታችኋቸው አትሂዱ። በትዕግስተኝነት ወይም በፍርሀት— በተፈጠረው ችግር፣ በአለመቀበል፣ ወይም እንዲሁም በመሰቃየት ፍርሀት ሀሳብ አትሸነፉ። የአዳኝን ቃል ኪዳን አስታውሱ፥

“ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።

“ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”33

በመጨረሻም፣ ሁላችንም ለምርጫዎቻችን እና ለምንኖርበት ህይወቶቻችን መልስ የምንሰጥ ነን። “አባቴም በመስቀል እሰቀል ዘንድ ልኮኛል፤ እናም በመስቀል ላይ ከተሰቀልኩ በኋላ፣ ሰዎችን ሁሉ ወደ ራሴ አመጣ ዘንድ፣ እኔ በሰዎች እንደተሰቀልኩ በአብ አማካኝነት ሰዎች ይነሱ ዘንድ፣ መልካምም ይሁኑ መጥፎ በስራቸው እንዲፈረድባቸው በእኔ ፊት ለመቆም ይችሉ ዘንድ፣ ተሰቅያለሁ።”34

ጌታ ከሁሉም በላይ እንደሆነ በማወቅ፣ በአልማ ቃላት እለምናለሁ፥

“እናም አሁን፣ ወንድሞቼ፣ ከልቤ ውስጣዊ ቦታ፣ አዎን እስከህመም በሚሆን በታላቅ ጭንቀት፣ ቃሌን ታደምጡኝ ዘንድ፣ እናም … ኃጢአታችሁን ታስወግዱና፣ የንስሃችሁን ጊዜ እንዳታዘገዩት እመኛለሁ፤

“ነገር ግን በጌታ ፊት እራሳችሁን ትሁት ታደርጉ ዘንድና፣ ቅዱስ ስሙን ትጠሩ ዘንድ፣ እናም ያለማቋረጥ እንድትተጉ እንዲሁም እንድትፀልዩ፣ ከሚቻላችሁ በላይም እንዳትፈተኑም፣ እናም ትሁት፣ የዋህ፣ ታዛዥ፣ ታጋሽ፣ ፍቅር የሞላባችሁና ፅኑ መከራን ቻይ በመሆን በመንፈስ ቅዱስ የምትመሩ እንድትሆኑ እመኛለሁ።

“በጌታ እምነት ይኑራችሁ፣ ዘለአለማዊ ህይወትን ለመቀበል በተስፋ የተሞላችሁ ሁኑ፣ በመጨረሻው ቀን ከፍ እንድትሉና ወደእረፍቱም እንድትገቡ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ሁልጊዜም በልባችሁ ይሁን።”35

ከዳዊት ጋር ለጌታ እንዲህ ለማለት እንቻል፥ “እውነትህንም በልቤ ውስጥ አልሰወርሁም፥ ማዳንህንም ተናገርሁ፤ ምሕረትህንና እውነትህን ከታላቅ ጉባኤ አልሰወርሁም። አቤቱ፥ አንተ ምሕረትህን ከእኔ አታርቅ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ።”36 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።