ኃጢያት-ተቋቋሚ ትውልድ
ልጆችን ስታስተምሩ፣ ስትመሩ፣ እና ስታፈቅሩ፣ ጀግናም ኃጢያት-ተቋቋሚ ልጆችን ለመፍጠርና ለማስታጠቅ የሚረዳን የግል ራዕይ ለመቀበል ትችላላችሁ።
ከአመት ግማሽ በፊት፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን “የኃጢአት-ተቋቋሚ ትውልድን የማስተማር እና ለማሳደግ ለመርዳት”1 አስፈላጊነት ተናግረው ነበር። “የኃጢአት-ተቋቋሚ ትውልድ” የሚለው ሀረግ የነፍስ ስሜቴን ነክቶ ነበር።
ንጹህ እና ታዛዥ የሆነ ህይወት የሚኖሩ ልጆችን እናከብራለን። በአለም ውስጥ የብዙ ልጆች ጥንካሬ ምስክር ነኝ። በተለያዩ አስቸጋሪ ጉዳዮች እና ቦታዎች እነርሱም “የሚጸኑና የማይነቃነቁ”2 ናቸው። እነዚህ ልጆች መለኮታዊ ማንነታቸውን ይረዳሉ፣ የሰማይ አባት ለእነርሱ ያለው ፍቅር ይሰማቸዋል፣ እና የእርሱን ፍላጎት ለማክበር ይፈልጋሉ።
ነገር ግን፣ “የሚጸኑና የማይነቃነቁ” ለመሆን የሚታገሉና ስሜታዊ አዕምሮአቸው እየተቆሰሉ ናቸው።3 በየጎኑ “በሚንበለበሉት የጠላት ፍላጻዎች ”4 እየተጠቁ ናቸው እና ማጠናከሪያና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። ልጆቻችንን ወደ ክርስቶስ ለማምጣት በምናደርገው ጥረት በኃጢያት ላይ ጦርነት ለማወጅ እንድንነሳሳ የሚያደርጉን ናቸው።
ከ43 አመት በፊት ሽማግሌ ብሩስ አር. መካንኪ ያሉትን ቃላት አድምጡ፥
“እንደ ቤተክርስቲያኗ አባላት፣ በታላቅ ትግል ላይ ነን ያለነው። በጦርነት ላይ ነን። ከሉሲፈር ጋር ለመዋጋት በክርስቶስ ምክንያት ውስጥ ተመዝግበናል። …
“በየጎኑ የሚዋጋው እና በሚያሳዝን ሁኔታ ብዙ ጉዳት፣ እንዳንዴም ሞት፣ የሚኖርበት ታላቁ ጦርነት አዲስ ነገር አይደለም። …
“አሁን በዚህ ጦርነት ምንም ገለልተኝነት የለም ወይም ለመኖርም አይችሉም።”5
ዛሬ ጦርነቱ በሚቀጥል ከፍተኛ ስሜት ይቀጥላል። ትግሉ ሁላችንንም ይነካል፣ እናም ልጆቻችን በሚቃወሙ ሀይሎች ፊት ለፊት ላይ የሚቆሙ ናቸው። በዚህም፣ መንፈሳዊ እቅዳችንን የማጠናከር ፍላጎታችንን ያባብሳል።
ልጆች የኃጢያት-ተቋቋሚ እንዲሆኑ ማጠናከር የወላጆች፣ የአያቶች፣ የቤተሰብ አባላት፣ የአስተማሪዎች፣ እና የመሪዎች ስራና በረከት ነው። ሁላችንም የመርዳት ሀላፊነት አለን። ነገር ግን ጌታ ወላጆችን ልጆቻቸው “ስለ ንስሀ፣ በህያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እምነት፣ እናም ስለ ጥምቀት እና እጆችን በመጫን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ስለመቀበል”6 ልጆቻቸው እንዲያስተምሩ መመሪያዎች ሰጥቷል።
እንዴት “[ልጆቻችንን] በብርሀን እና በእውነት እንደምናሳድግ”7 የሚያስቸግር ይሆናል፣ ምክንያቱም ይህም ለእያንዳኑ ቤተሰብ ለእያንዳንዱ ልጅ በግል የተሰጠ ነውና፣ ነገር ግን የሰማይ አባት ሁለንታዊ የሆነ መመሪያዎች እኛን ለመርዳት ሰጥቷል። መንፈስ ውጤታማ በሆነ መንገድ ልጆቻችንን በመንፈስ እንድንችል ያነሳሳናል።
ለመጀመር፣ የሲህ ሀላፊነት አስፈላጊነትን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። የኛን—እና የእነርሱን—መለኮታዊ ማንነት እና እቅድ ልጆቻችንን ማን እንደሆኑና ለምን በዚህ እንደሚገኙ ለማየት ከመርዳታችን በፊት መረዳት ይገባናል። ያለጥርጣሬ የሰማይ አባት ወንድ እና ሴት ልጆች እንደሆኑ እና እርሱም መመልኮታዊ ጠበቃ እንዳለው እንዲያውቁ መርዳት አለብን።
ሁለተኛ፣ የንስሀ ትምህርትን መረራት ኃጢያጥ፟-ተቋቋሚ ለመሆን አስፈላጊ ነው። ለኃጢያጥ፟-ተቋቋሚ መሆን ያለ ኃጢያት መሆን አይደለም፣ ነገር ግን ይህም ሁልጊዜ ንስሀ መግባትን፣ ሁልጊዜም ንቁ መሆንን፣ እና ጀግና መሆንን ያመለክታል። ምናልባት ለኃጢያጥ፟-ተቋቋሚ የሚሆነው ኃጢያትን በተደጋጋሚ በመቋቋም በሚመጣ በረከት ይሆናል። ያዕቆብ እንዳለው፣ “ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል።”8
ወጣት ወታደሮቹ “ … በጣም ጀግኖች ነበሩ፤ ነገር ግን እነሆ ይህ ብቻም አልነበረም—በሁሉም ጊዜ በተሰጣቸው በማንኛውም ነገር ታማኝ ሰዎች ነበሩ። አዎን፣ ... የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንዲጠብቁና በፊቱም በቅንነት እንደሚራመዱ ተምረዋልና።”9 እነዚህ ወጣት ሰዎች የክርስቶስ አይነት ስነምግባርን በጠላቶቻቸው ላይ እንደሚጠቀሙበት መሳሪያ ይዘው ወደ ጦርነት ሄደው ነበር። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንድናስታውስ እንዳደረጉን፣ “ድፍረት የማገት ጥሪ ለእያንዳንዳችሁ ሁልጊዜም ይመጣሉ። በህይወታችን በእያንዳንዱ ቀን ድፍረት ያስፈልገዋል፣ ይህም ለታላቅ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን ውሳኔዎች ስናደርግ ወይም በአካባቢያችን ባሉት ጉዳዮች መልስ ስንሰጥ ነው።”10
ልጆቻችን የየቀኑ ደቀመዛሙርትነት መቆጣጠርን ንድፍ ሲመሰርቱ መንፈሳዊ ጥሩርን ይለብሳሉ። ምናልባት የየቀኑ ደቀመዛሙርትነት ሀሳብን የማወቅ ችሎታቸውን አስቀንሰን ገምተን ይሆናል። ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ እንደመከሩን “ቶሎ ጀምሩ እናም ቀጥሉ።”11 ስለዚህ ልጆቻችንን ለኃጢያት-ተቋቋሚ እንዲሆኑ የምንረዳበት ሶስተኛው ቁልፍ ቢኖር፣ ልጆቻችንን ወደ አዳኝ ከሚመሩትከትንሽነታቸው ጀምሪ ከቅዱሳት መጻህፍት፣ ከእምነት አንቀጾች፣ ከወጣቶች ጥንካሬ መፅሔት፣ ከመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮች፣ ከመዝሙሮች፣ እና ከግል ምስክሮቻች የወንጌል ትምህርቶችን በፍቅር ለማቀላቀል መጀመር ነው።
የማይቀየር የጸሎት፣ የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት፣ የቤተሰብ የቤት ምሽት፣ እና የሰንበት አምልኮ ጸባት ወደ ሙሉነት፣ በውስጥ የማይቀየር ወደመሆን፣ እና ጥነካራ የምግባር ዋጋ ያለው—በሌላም አባባል መንፈሳዊ ቅንነት ያለው ወደመሆን ይመራል። በዛሬ አለም ውስጥ፣ ቅንነት እየጠፋ እያለ ቢሆንም፣ ልጆቻችንን በጥምቀት እና ብቤተመቅደስ ውስጥ ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ለመስራት እና ለመጠበቅ ስናዘጋጃቸው፣ እውነተኛ ቅንነት ምን እንደሆነና ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ለመረዳት ያስፈልጋቸውል። ወንገሌን ስበክ የሚለው እንደሚያስተምረው፣ “የተስማሙበትን መጠበቅ ሰዎች [በተጨማሪም ወጣት ሰዎች]] ቃል ኪዳን ለመግባትና ለመጠበቅ ያዘጋጃቸዋል።”12
ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ እንዳስተማሩት፣ “ቃል ኪዳንን ስለመጠበቅ ስንናገር፣ ስለሟች ህይወታችን ዋና እቅድ እየተናገርን ነን።”13 ከሰማይ አባታችን ጋር ቃል ኪዳኖችን መግባትና መጠበቅ ጋር የሚመጣ ልዩ ሀይል አለ። ጠላት ይህን ያውቃል፣ ስለዚህ የቃል ኪዳን መግባት ሀሳብን ይሰውራል።14 ልጆችን ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን እንዲረዱ፣ እንዲገቡ፣ እና እንዲጠብቁ መርዳት ለኃጢያት-ተቋቋሚ ትውልዶችን ለመፍጠት ሌላ ቁልፍ ነው።
ልጆች በቃል ኪዳን መንገድ እየገቡና እያደጉ ሳሉ ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን እንዲገቡና እንዲጠብቁ እንዲት ለማዘጋጀት እንችላለን? ልጆች በትንሽነታቸው ቀላል ቃል ኪዳኖችን እንዲጠብቁ ማስተማር ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን እንዲጠብቁ ሀይል ይሰጣቸዋል።
አንድ ምሳሌ ላካፍል፥ በቤተሰብ የቤት ምሽት፣ አንድ አባት እንዲህ ጠየቀ፣ “ግንኙነታችን እንደቤተሰብ እንዴት ነው?” የአምስት አመቷ ልዚ ታላቅ ወንድሟ ኬቭን በብዛት እንደሚያሳልቅባት እና ስሜቷን እንደሚጎዳ ተናገረች። ኬቭንም ብግድ ልዚ ትክክል እንደሆነች ተቀበለ። የኬቭን እናት ከእህቱ ጋር በተሻሻለ ግንኙነት እንዲኖረው ምን ማድረግ እንደሚችል ጠየቀችው። ኬቭንም አሰበበት እናም እርሷ ላይ ላለመሳለቅ አንድ ቀን በሙሉ እንዲያሳልፍ ለልዚ ቃል ለመግባት ወሰነ።
በሚቀጥለው ቀን መጨረሻ ላይ ለቤተሰብ ጽሎት ሁሉም ሲሰበሰብ፣ የኬቭን አባት ኬቭንን እንዴት እንዳደረገ ጠየቀው። ኬቭንም እንዲህ መለሰ፣ “አባዬ፣ ቃል ኪዳኔን ጠብቄአለሁ!” ልዚ በደስታተስማማች፣ እናም ቤተሰብም ኬቭንን እንኳን ደስ አለህ አሉት።
የኬቭን እናትም ቃል ኪዳኑን ለአንድ ቀን ለመጠበቅ ከቻለ፣ ለሁለት ቀናት ለመጠበቅ ለምን አትችለውም? በማለት ሀሳብ አቀረበች። ኬቭንም እንደገና ለመሞከር ተስማማ። ሁለት ቀናት አለፉ፣ ኬቭንም ቃሉን በመጠበቅ ውጤታማ ነበር፣ እና ልዚም ተጨማሪ ምስጋና ነበራት! አባቱ ለምን ቃሉን በደንበንደሚጠብቅ ሲጠይቀው፣ ኬቭንም እንዲህ አለ፣ “ቃሌን የጠበቅኩት አደርጋለሁ ስላልኩኝ ነው።”
ትንሽ፣ ውጤታማ የሆኑ የቃል ኪዳን ማክበር ልምምዶች ወደ ቅንነት ይመራሉ። ቃል ኪዳንድድ ሁልጊዜም የመጠበቅ ልምምድ ልጆች እግዚአብሔርን ለማገልገል እና ትእዛዛቱን ለማክበር ቃል ለሚገቡበትን የጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የመጀመሪያ ቃል ኪዳንን ለመቀበል የሚያዘጋጅ ነው።15 ቃል መግባትና ቃል ኪዳኖች የማይለያዩ ናቸው።
በመፅሐፈ ዳኔል ውስጥ ስለ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ እና አብደናጎ የንጉስ ናቡከደነፆር አማልክትን አናመልክም ብለው እምቢ አሉ።16 ንጉሱም ይህን ካላደረጉ ወደ እሳት እውጥ እንደሚጣሉ አስጠነቀቃቸው። እንዲህ በማለት እምቢ አሉ፥
የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል። …
“ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት።”17
“ነገር ግን፥ እርሱ ባያድነን።” የእነዚህን ቃላት ትርጉም እና እንዴት ቃል ኪዳንን ከመጠበቅ ጋር እንደሚገናኙ አስቡበት። እነዚህ ሶስት ወጣቶች ታዛዥነታቸውን በመዳን ላይ የጣሉ አልነበሩም። የሚድኑ ባይሆኑም፣ ለጌታ የገቡትን ቃል ኪዳን ይጠብቃሉ፣ እንዲህ ለማድረግ ቃል ገብተዋልና። ቃልኪዳኖቻችንን መጠበቅ ከጉዳያችን ጋር የተገናኙ አይደሉም። እነዚህ ወጣቶች፣ ልክ እንደ ወጣት ጀግናዎች፣ ለልጆቻችን የኃጢያት-መቋቋም ምሳሌዎች ናቸው።
እነዚህ ምሳሌዎች በቤቶቻችን እና በቤተሰቦቻችን ውስጥ እንጠቀምባቸዋለን? “በሥርዓት ላይ በሥርዓት፣ በትእዛዝም ላይ ትእዛዝ”18 ልጆች ውጤታማነትን እንዲቀምሱ እንረዳለን። ቃል የገቡትን ሲጠብቁ፣ መንፈስ በህይወታቸው ይሰማቸዋል። ሽማግሌ ጆሴፍ ቢ. ወርዝልን እንዳስተማሩን “የቅንነት ሽልማት የመንፈስ ቁድስ ጓደኝነት ነው።”19 ከዚያም የልጆቻችን “ልበ ሙሉነት በእግዚአብሔር ፊት እየጠነከረ ይሄዳል።”20 ከቅንነት ውስጥ ሀል ያላቸው፣ ኃጢያትን-የሚቋቋሙ ትውልዶች ይፈለቅላሉ።
ወንድሞችና እህቶች፣ ትትንሽ ልጆቻችሁን ቅርብ አድርጉ—የየቀኑ የሀይማኖት ጸባያችሁን እንዲያዩ እና ቃል የገባችሁትን እና ቃል ኪዳኖቻችሁን ስታከብሩ እንዲመለከቷችሁ ቅርብ አድርጓቸው። “ልጆች ታላቅ አስመሳዮች ናቸው፣ ስለዚህ የሚያመሳስሉት አንድ ነገር ስጧቸው።”21 በእርግጥም ኃጢያት-የሚቋቋሙ ትውልዶችን ቃል በምግባት ቃል በመግባት እና ቃል ኪዳን በቃል ኪዳን ለጌታ ለማስተማርና ለማሳደግ እየረዳን ነን።
ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኗን እንደሚመራ እመሰክራለሁ። ልጆችን በአዳኝ መንገድ ስታስተምሩ፣ ስትመሩ፣ እና ስታፈቅሩ፣ ጀግናም ኃጢያት-ተቋቋሚ ልጆችን ለመፍጠርና ለማስታጠቅ የሚረዳን የግል ራዕይ ለመቀበል ትችላላችሁ። ጸሎቴም ልጆቻችን የኔፊን ቃላቶች እንዲደግሙ ነው፥ “ኃጥያትስ በምመለከትበት ወቅት በጥላቻ ታንቀጠቅጠኛለህን?”22 አዳኛችን ለአለም ኃጢያቶች ክፍያ እንዳደረግ እመሰክራለሁ23—ምክንያቱም እርሱ እንዲህ አደርጋለሁ ብሏልና፣ እናም እርሱ እኛ ሟቹች ለመረዳት ከምንችለው በላይ ይወደናልና24—ምክንያቱም እርሱ እንዲህ አደርጋለሁ ብሏልና። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።