ሊያሆና
ብርሃናችን በምድረበዳ ውስጥ።
ጥር 2024 (እ.አ.አ)


ብርሃናችን በምድረበዳ ውስጥ፣ሊያሆና፣ ጥር 2024 (እ አ አ )

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ጥር 2024 (እ.አ.አ)

ብርሃናችን በምድረበዳ ውስጥ

መፅሐሃፈ ሞርሞንን ከልባቸው የሚያነቡ፣ በትዕዛዛቱ የሚኖሩ እና እውነት ስለመሆኑ የሚጸልዮ፤ መንፈስ ቅዱስ ይሰማቸዋል እንዲሁም በአዳኙ ላይ ያላቸው እምነት እና ምስክርነት ይጨምራል።

ምስል
የያሬድ ወንድም የሚያበሩ ድንጋዮችን ይዞ።

የያሬድ ወንድም የሚያበሩ ድንጋዮችን ይዞ ምስል በኖርማንዲ ፖልተር።

ወጣት ልጅ እያለሁ እንኳን የመፅሐሃፈ ሞርሞን ምስክርነት ነበረኝ። የያሬድ ወንድም እና ህዝቡ ወደ “ቃል ኪዳኗ ምድር” ባደረጉት ጉዞ ታሪክ ላይ በተለየ መልኩ የመሳብ ሥሜት ተሰምቶኝ ነበር(ኤተር 2:9)።

ብርሃን ባልነበራቸው ጀልባዎች የመጓዝ ዕድል ሲገጥመው የያሬድ ወንድም “እነሆ አቤቱ ጌታዬ ይህንን ታላቅ ውሃ በጨለማው እንድናቋርጥ ትፈቅዳለህን?” ሲል ጠየቀ። እናም ጌታ ለያሬድ ወንድም እንዲህ ሲል መለሰለት፥ በጀልባው ውስጥ ብርሃን እንዲኖር ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ? (ኤተር 2:22, 23)

የያሬድ ወንድም ጌታ ሃያል እንደሆነ ያውቅ ነበር። ጌታ የሁሉም ብርሃን ምንጭ እንደነበር ያውቅ ነበር። ሕዝቡ ችግር በሚያጋጥማቸው ጊዜ እርሱን እንዲጠሩ ጌታ እንዳዘዛቸው ያውቅ ነበር። ስለዚህም፣ የያሬድ ወንድም በጌታ እምነትን በመለማመድ፤ 16 ትናንሽ ድንጋዮችን አዘጋጀ። ከዚያም በጣቶቹ ድንጋዮቹን እንዲነካ ጌታን ጠይቆት እንደነበር ታስታውሳላችሁ፤ “ እነርሱም በጭለማ ውስጥ እንዲያበሩ አዘጋጃቸው“ (ኤተር 3:4)።

በመጀመሪያ ያንን ታሪክ አንብቤ ስለነበር፤ ጌታ ድንጋዮቹን ሲነካ የሚያሳይ ምስል በአምሮዬ ተቀርጾ ነበር። ያንን ትዕይንት ልክ አይኔ እያየ የተከናወነ እስኪመስለኘ ድረስ ማየት እችላለሁ። ምናልባትም ያ የሆነው የጨለማው በብርሃን የመወገድ ምስል ለእኔ እውን ስለሆነልኝ ይሆናል።

መንፈስ ቅዱስ በማይሰማኝ ጊዜ፤ ትንሽ ከጌታ መንፈስ ውጭ በምሆንበት ጊዜ ጨለማ ይሰማኛል። ነገር ግን መጽሃፈ ሞርሞንን ሳነብ ብርሃኑ ይመለሳል። መጸሃፈ ሞርሞን ለእኔ ልክ በጌታ እንደተነካው እንደሚያበራው ድንጋይ ሆኖልኛል። የህይወት መንገዴን አብርቶልኛል።

የዘለአለም ብርሃን

ልክ በጌታ እጅ ወደ ጥንታዊቷ የአሜሪካ ምድር እንደተወሰዱት ሕዝቦች፣ ከፍ ከፍ ወደ ወደምታደርገው ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር በምናደርገው ጉዞ እኛ ሁላችንም ወጀቦች እና የጨለማ ቀናቶች ይገጥሙናል። ነገር ግን ጌታ ለያሬዳውያን እና ለኔፋውያን እንዳደረገው ለእኛም ያደርግልናል። ከታዘዝነው፣ በእርሱ እምነትን ከተለማመድን እና እርዳታ እንዲሰጠን ከተማጸነው ይመራናል እንዲሁም መንገዳችንን ያበራልናል።

ጌታ ለኔፊ እንዲህ ሲል ነግሮታል፣ “እናም በምድረበዳ ውስጥ እኔ ብርሃን እሆናችኋለሁ፤ እናም ትዕዛዛቴን ከጠበቃችሁ መንገዱን በፊታችሁ አዘጋጅላችኋለሁ፤ ስለዚህ ትዕዛዛቴን እስከጠበቃችሁ ድረስ ወደ ቃልኪዳኑ ምድር ትመራላችሁ፤ እናም የተመራችሁት በእኔ እንደሆነም ታውቃላችሁ”(1 ኔፊ 17:13)።

ጌታ ለኔፊ ወንድም ለያዕቆብ እንዲህ ብሎ ነገረው “ድምጼን ለሚሰሙ ሁሉ ለዘለአለም ብርሃን እሆንላቸዋለሁ” (2 Nephi 10:14)።

ነቢዩ አቢናዲ ስለአዳኙ እንዲህ ሲል መስክሯል፣ “እርሱ የአለም ብርሃን ህይወት ነው፤ አዎን መጨረሻ የሌለው ፣ሊጨልም የማይችል ብርሃን” (ሞዛያ 16:9)።

አዳኙ ስለራሱ እንዲህ ሲል መስክሯል፣ “እናም እነሆ እኔ የዓለም ብርሃንና ሕይወት ነኝ።” አክሎም “እነሆ እኔ ብርሃን ነኝ፤ ምሳሌም ትቼላችኋለሁ“ (3 ኔፊ 9:18; 18:16)።

ምስል
ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እየተራመዱ

ብርሃኑ ሲሰማን

ነቢያችንን ፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልስንን እወዳቸዋለሁ። ከእርሳቸው ጎን የማገልገል በረከት አግኝቻለሁ። ወደ አንድ ክፍል ሲገቡ፣ ያ ክፍል ወዲያዉኑ የበለጠ ብሩህ የመሆን ሥሜት ያመጣል። የክርስቶስን ብርሃን ተሸክመዋል።

የክርስቶስ ብርሃን እውን ነው። “ከእግዚአብሔር ዘንድ በክርስቶስ በኩል የሚመጣ ለሁሉም ነገሮች ሕይወትን እና ብርሃንን የሚሰጥ መለኮታዊ ሃይል፣ ጉልበት ወይም ተፅዕኖ ነው።” የእግዚአብሄርን ልጆች ወደ መንፈስ ቅዱስ እና ወደ ክርስቶስ ወንጌል የሚመራ ውድ የሆነ መንፈሳዊ ሥጦታ ነው።1 መጸሃፈ ሞርሞንን ማንበብ ያንን ብርሃን ያጠነክራል።

አንዳንድ ጊዜ ወደኋላ ተመልሰን በሕይወታችን ጉዞ እንዴት እንደተረዳን ማየት ያስፈልገናል። ወደ ኋላ ስንመለከት አዳኙ የነበረው ተፅዕኖ በድጋሚ ሊሰማን ይችላል። ቅዱሳት መፃህፍት “አስታውሱ፣ አስታውሱ“ (ሄለማን 5፡12) ሲሉን ሊነግሩን የፈለጉት፣ “ የሆነ ጊዜ ታውቁት የነበረ ወይንም ተሰምቷችሁ የነበረ ነገርን ማስታወስ ብቻ ሳይሆን ያ ብርሃን ይሰማችሁ“ ማለታችው ይመስለኛል።

ለአንዳንዶች የመንፈሳዊ ብርሃን ስሜት በቀላሉ ይመጣላቸዋል። ለአንዳንዶች ደግሞ በግላዊ ችግሮች ወይም ትኩረትን በሚከፋፍሉ አለማዊ ነገሮች ምክንያት የመንፈሳዊ ብርሃንን ስሜት ማግኘት አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል። ነገር ግን እኛ ታማኝ ከሆንን አንዳንዴ ባልጠበቅነው መንገድ ብርሃኑ ይመጣል።

“መጽሃፈ ሞርሞርንንበየቀኑ በጸሎት መንፈስ እንድናነብ”2 የመከሩን ፕሬዚዳንት ኔልሰን፣ መፅሐፈ ሞርሞንን ማንበብ ወደ አዳኙ እንድቀርብ እና የወንጌል ብርሃን፣ የወንጌል እውነት፣ የወንጌልን ትምህርቶች እንድንኖር የሚረዳበትን ብዙ መንገዶች አካፍለውናል።

ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንደተናገሩት፣ መጸሃፈ ሞርሞንን በምናነብበት ጊዜ ለኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ያለን ግንዛቤ እና አድናቆት ያድጋል።

መጽሃፉ የልብ መለወጥ እንድናደርግ ሲረዳን “ዳግም የመወለድ”(ሞዛያ 27 ፡25 ) ፍላጎት ይኖረናል ( ሞዛያ 5፡2ይመልከቱ)።

በመጸሃፈ ሞርሞን የሰፈረውን የእስራኤል መሰብሰብ ትምህርቶች ስናነብ እና ስናጠና፣ በሞት የተለዩንን የመፈለግ እና በቤተ መቅደስ ውስጥ ለእነርሱ የደህንነት እና ከፍ ከፍ የመደረግ ሥርዓቶችን የማድረግ ፍላጎታችን ይጨምራል።

ለጥያቄዎቻችን መልስ፣ ውሳኔዎችን ለማድረግ ምሪት እንዲሁም ንስሃ ለመግባት እና ክፉውን ለመቋቋም ጥንካሬ ስናገኝ ብርሃን ይሰማናል።

እንዲሁም በመጽሃፈ ሞርሞን የሚገኙትን እውነቶች ስናነብ፣ ለነፍሳችን ፈውስ፣ መጽናናት፣ መመለስ፣ እርዳታ ፣ጥንካሬ፣ መጽናናት ይሰማናል 3

አቤቱ ይህ እውነት አይደለምን? አልማ ስለአበጠው፣ ስላቆጠቁጠው የእውነት፣ የእውቀት እና የምስክርነት ዘር አስመልክቶ ጠይቆ ነበር። “አዎን፣ ምክንያቱም ይህ ብርሃን ነው፣ እናም ብርሃን የሆነው ማንኛውም መልካም ነው፣ ምክንያቱም እርሱ የሚለይ ነውና፣ ስለሆነም መልካም መሆኑን ማወቅ ይገባችኋል(አልማ 32:35)።

ምስል
የኢየሱስ ክርስቶስ ምስል

የክርስቶስ ምስል፣ በሄንሪክ ሆፍማን

በጨለማ ውስጥ አዳኙን ፈልጉት።

ጓደኛዬ ካምሪን የአስር አመት ልጅ እያለች አልፎ አልፎ በሚከሰት ነገር ግን ቋሚ በሆነና የቀኝ አይንዋን ኮርኒያ ኢንፌክት ባደረጋት የአይን በሽታ ተያዘች።4 አንዳንድ ጊዜ ከበሽታዋ ጋር ተያያዥ የሆነው ህመም ያለማቋረጥ ሲቀጥል እና ከዓቅም በላይ ሲሆን ካምሪን ማንኛውንም ብርሃን መቋቋም አትችልም ነበር። ወላጆችዋ አይነ ስውር ትሆናለች ብለው በመስጋት፣ የመኝታ ቤቷን መስኮቶች ብርሃን እንዳያስገቡ በማድረግ ምቾትዋን ለመጠበቅ ይሞክሩ ነበር። የካምሪን እናት ጃና እንዲህ ታስታውሳለች፣

“በሽታው እንዳለባት ከታወቀ ከአራት ወራት በኋላ ወደ ጨለማ ክፍልዋ ገባሁ። አይኖቼ ለማየት ከታገሉ በኋላ፣ ካምሪን ልክ በሆድ ውስጥ እንዳለ ጽንስ አልጋዋ ላይ እጥፍጥፍ ብላ ነበር። በጣም ከባድ የሆነ ህመም ውስጥ ከመሆንዋ የተነሳ አትንቀሳቀስም ነበር እንዲሁም ወደ ውስጥ ስገባ በሰማቺኝ ጊዜ እንኳን አላለቀሰችም። ሁለቱም አይኖችዋ አብጠውና ተከድነው ጋደም ብላ ነበር።

“አልጋዋ አጠገብ በርከክ አልኩ፣ እጆቿን በእጆቼ ያዝ አደረኳቸውና ሶስት ጊዜ ጨመቅ ጨመቅ አደረኳቸው ያም በእኛ ሚስጥራዊ ኮድ “እወድሻለሁ“ ማለት ነበር። በተለምዶ “የበለጠ እወድሻለሁ“ ለማለት እሷም አራት ጊዜ መልሳ ጨመቅ ጨመቅ ታደርገኝ ነበር፤ ነገር ግን ምላሽ አልሰጠችኝም። ከፍተኛ ህመም ውስጥ ነበረች። እንባዬ በጉንጮቼ ላይ እየወረዱ፣ በአንድ ወቅት ንቁ የነበረችውን የ10 አመት ልጅ ጭብጥብጥ ብላ ተመለከትኳት። በጣም አዘንኩኝ።”

ጃና በጸጥታ ከልቧ ጸሎት አደረገች።

“የሰማይ አባታችን ከሁሉ የተሻለ እንደሚያውቅ ነገርኩት ነገር ግን ‘እባክህ እርዳት’ ስል ጸለይኩኝ። እዛ ቁጭ ብዬ እየፀለይኩኝ ሳለሁ፣ የሙቀት ማዕበል በላዬ ወረደ። ‘እርሱ ብርሃን ነው በጭለማ ውስጥ ፈልጉት’” የሚለው አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስን የተመለከተ ሃሳብ ወደ አምሮዬ ሲመጣ የመረጋጋት ስሜት ተሰማኝ። the content of this segment is included in segment 94.

ጃናም ጭንቅላቷን ቀና አድርጋ በካምሪን ጆሮ እንዲህ ስትል በሹክሹክታ ነገረቻት “ በጨለማ ውስጥ አዳኙን ማግኘት አለብሽ።“

ከዚያ በኋላም ካምሪን በቤተክርስቲያን የላይብረሪ መተግበሪያ ላይ መዝሙሮችን እና ቅዱሳት መጽሃፍትን ከሰማች በኋላ እንቅልፍ ወሰዳት።

ምስል
የአይን መሸፈኛ ያደረገች ልጃገረድ

የአይኗ ኢንፌክሽን ሲያገረሽ ካምሪን አዳኙን በጨለማ ውስጥ ታገኘዋለች።

የካምሪን ቤተሰብ ፎቶግራፍ።

የካምሪን በሽታ አብዛኛውን ጊዜ አይነሳባትም ነበር ነገር ግን ሲያገረሽባትና ስትሰቃይ ጃና እና ባለቤትዋ ዳሪን በመኝታ ቤትዋ መስኮቶች ላይ ብርድ ልብሶች በመከለል ያጽኗኗት ነበር። በእነዚያ የህመም ጊዜያት ካምሪን “አዳኙን በጨለማ ዉስጥ እየፈለኩት ነው“ ትላለች።5

ህይወት “ጨለማ እና አስፈሪ ምድረ በዳ “ 1 Nephi 8:4)ሲመስል አዳኙን በጨለማ ውስጥ ልንፈልገውም እንችላለን። “ኢየሱስ ክርስቶስ እና ዘላለማዊ አምላክ እንደሆነ“ የሚመሰክርልን መጸሐፈ ሞርሞን 6ወደ እርሱ እንደሚመራን እመሰክራለሁ። መፅሐሃፈ ሞርሞንን ከልባቸው የሚያነቡ፣ በትዕዛዛቱ የሚኖሩ እና እውነት ስለመሆኑ የሚጸልዮ፣ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሰማቸው እንዲሁም በአዳኙ ላይ ያላቸው እምነት እና ምስክርነት እንደሚጨምር አውቃለሁ።

ይህን “ከሁሉም የበለጠ ትክክል“ 7 የሆነውን መጽሃፍ በማንበብ፣ ትልቅ ዋጋ በመስጠት እንዲሁም በብርሃን አለም የራሳችንን እና የሌሎችን እምነት ለማጠንከር በመጠቀም ምስጋናችንን እናሳይ።

ማስታወሻዎች

  1. ርዕሶች እና ጥያቄዎች “የክርስቶስ ብርሃን፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

  2. ራስል ኤም. ኔልሰን “መፅሐፈ ሞርሞንን፦ ያለሱ ሕይወታችሁ ምን ይሆናል?ሊያሆና, ህዳር. 2017, 62–63.

  3. ራስል ኤም. ኔልሰን “መፅሐፈ ሞርሞንን፦ ያለሱ ሕይወታችሁ ምን ይሆናል?” 62,63

  4. ሄርፔስ ሲምፕሌክስ ኬራቲቲስ

  5. ጃና ካኖን እና ልጅዋ ካምሪን ይህንን ታሪክ ስላካፈሉን አመሰግናለሁ።

  6. የመፅሐፈ ሞርሞን የርዕስ ገጽ

  7. የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች: ጆሴፍ ስሚዝ (2007(እ.አ.አ))፣ 64. ።

አትም