ሊያሆና
እኛ መልካም ነገርን ለማድረግ ተጠርተናል
ሰኔ 2024 (እ.አ.አ)


“እኛ መልካም ነገርን ለማድረግ ተጠርተናል” ሊያሆና፣ ሰኔ 2024።

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ሰኔ 2024 (እ.አ.አ)

እኛ መልካም ነገርን ለማድረግ ተጠርተናል

ሌሎችን ስናገለግል፣ ብርሃናችንን ከፍ አድርገን ስንይዝ እና ለየሃይማኖት ነፃነት ስንቆም የእግዚአብሔርን መንግስት እንገነባለን።

ጌዴዎን የሐሰት ትምህርትን በሚሰማው ጊዜ ያውቀው ነበር። ከዚህ በፊት ከንጉስ ኖህ እና “በልባቸው ኩራት [ካ]በጡት” እንዲሁም “[ለ]ስንፍናቸው፣ [ለ]ጣዖት አምላኪነታቸው፣ እናም ለዝሙታቸው ንጉሥ ኖህ በህዝቡ ላይ ባደረገው ቀረጥ [ከተደገፉት] ካህናት” ሰምቶት ነበር (ሞዛያ 11፥5–6)።

ይባስ ብሎም፣ ንጉስ ኖህ ነቢዩን አቢናዲን ገድሎት ነበር እንዲሁም አልማን እና በወንጌሉ የቀየራቸውን ለማጥፋት ፈልጎ ነበር (ሞዛያ 1718፥33–34 ይመልከቱ)። እንደዚህ አይነትን ክፋት ለማስወገድ፣ ጌዴዎን፣ በላማናውያን ወረራ ምክንያት ብቻ ህይወቱን ያተረፈለትን ንጉሱን ለማስቆም ማለ (ሞዛያ 19፥4–8 ይመልከቱ)።

በኋላም፣ 24 የላማናውያን ሴት ልጆችን ስለወሰዱ፣ ጌዴዎን የኖህ ካህናትን በትክክል ወቀሳቸው። አቢናዲ ስለህዝቡ የተናገረው ትንቢት፣ ንስሃ ለመግባት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንደተፈፀመ አየ። (ሞዛያ 20፥17–22 ይመልከቱ)። በላማናውያን ባርነት ውስጥ የነበሩትን የሊምሂ ህዝብ ነፃ ለማውጣት ረዳቸው (ሞዛያ 22፥3–9 ይመከቱ)።

አሁን በእድሜ ከፍ ያለው ጌዴዎን፣ ለህዝቡ የካህናት ተንኮልን ባስተዋወቀው በኔሆር ፊት በቆመ ጊዜ፣ ኩራትን እና ክፋትን በድጋሚ ተጋፈጠ። ኔሆር “ቤተክርስቲያኗን እየተቃወመ” እንዲሁም ህዝቡን ወደተሳሳተ መንገድ ለመምራት እየሞከረ ነበር። (አልማ 1፥3፣ 7፣ 12፥ እንዲሁም 2 ኔፊ 26፥29 ይመልከቱ።)

ጀግናው ጌዴዎን የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መሳሪያው በመጠቀም፣ ኔሆርን ስለ ኃጥያቱ ገሠፀው። ኔሆርም በመናደድ ጌዴዎንን በሰይፍ አጥቅቶ ገደለው። (አልማ 1፥7–9 ይመልከቱ።) “በዚህ ህዝብ መካከል ብዙ መልካም ነገርን ያደረገው” “የጻድቁ ሰው” ዘመንም በዚህ መልኩ አበቃ (አልማ 1፥13)።

የምንኖርባቸው ኋለኞቹ ቀናት ለሌሎች “አገልጋይ” (ሞዛያ 22፥4) በመሆን፣ ለጽድቅ በመቆም እና እግዚአብሔርን የማምለክ እና የማገልገል ነፃነታችንን ስጋቶች በመቋቋም፣ የጌዴዎንን ምሳሌ በመከተል “በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ እንዳለ መሣሪያ” (አልማ 1፥8)ለመሆን ብዙ ዕድሎችን ይሰጡናል። የጌዴዎንን የታማኝነት ምሳሌ ስንከተል እኛም ብዙ ጥሩ ነገርን ማድረግ እንችላለን።

ምስል
አልጋ ላይ ተኝታ ካለች ሴት አጠገብ በሰሃን ምግብ ይዛ የቆመች ሴት

በአገልግሎት አንድ ሁኑ

ቀዳሚ አመራሮች እንዲህ ብለዋል፣ “[የአዳኙ] ተከታዮች እንደመሆናችን፣ እግዚአብሔርን እና በዓለም ዙሪያ ያሉ ጎረቤቶቻችንን መውደድ እንሻለን።” “የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሌሎችን ለመባረክ እና በችግር ላይ ያሉትን ለመርዳት ጉጉት አላት። ይህንን የተቀደሰ ሀላፊነት ለመወጣት ችሎታ፣ ግብዓቶች እና ታማኝ የሆኑ አለም አቀፍ ግንኙነቶች ስላሉን ተባርከናል።”1

የቤተክርስቲያኗ አባላት በቤተመቅደሶቻችን እንዲሁም በአጥቢያዎቻቸው፣ በቅርንጫፎቻቸው እና በካስማዎቻቸው ውስጥ ለሚሰጡት ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ አገልግሎት አመስጋኝ ነኝ። በተጨማሪም የቤተክርስቲያኗ አባላት ስፍር ቁጥር በሌላቸው የማህበረሰብ፣ የትምህርት እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ ስለሚያገለግሉ እና ወደ 200 በሚጠጉ ሀገራት እና ግዛቶች ውስጥ በየዓመቱ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰብአዊ ፕሮጀክቶች ላይ በመሰማራት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዓታትን በበጎ ፈቃደኝነት በመስራታቸው አመስጋኝ ነኝ።2

ቤተክርስቲያኗ በተለያዩ ሀገራት የአገልግሎት ዕድሎችን የምታሰፋበት አንዱ መንገድ JustServe.org ነው። በቤተክርስቲያን የተደገፈ ቢሆንም ሌሎችን ለመባረክ ለሚፈልግ ለማንኛውም ሰው አገልግሎቱ የሚገኘው JustServe.org፣ “የማህበረሰብ የበጎ ፈቃደኞች ፍላጎቶችን፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የአኗኗር ደረጃ ጥራት ከሚያሻሽሉ ከበጎ ፈቃደኞች ጋር ያገናኛል።”3

ቤተክርስቲያኗ እና አባሎቿ በአለም ዙሪያ ካሉ አገልግሎት ሠጪ ድርጅቶች ጋር ይተባበራሉ። ለአባላቶቿ ምስጋና ይግባቸውና፣ ቤተክርስቲያኗ “በ2022 (እ.አ.አ) በጣም ብቸኛው ትልቁ የቀይ መስቀል የደም አስተዋጽዖ አበርካች ነበረች።” በተጨማሪም ቤተክርስቲያኗ በቅርቡ ለቀይ መስቀል የ8.7 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጋለች።4

ቤተክርስቲያኗ ንፁህ ውሃን እና የንፅህና ፕሮጀክቶችን በአለም ዙሪያ ባሉ ቦታዎች ለማዳረስ ከሚሠሩ ድርጅቶች ጋር ትተባበራለች። በ2022 (እ.አ.አ)፣ ቤተክርስቲያኗ እነዚህን በመሠሉ156 ፕሮጀክቶች ውስጥ ተሳትፋለች።5 እኛም ለሚሰቃዩ የእግዚአብሔር ልጆች እፎይታን ከሚያመጡ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር እንተባበራለን እንዲሁም እርዳታ እንሠጣቸዋለን።6

በቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ የሆኑት ፕሬዚዳንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ እንዲ ሲሉ ተናግረዋል፣ “በችግር ላይ ያሉን ሰዎች ለማገልገል እጅ ለእጅ ስንያያዝ፣ ጌታ ልቦቻችንን አንድ ያደርገዋል።”7

ምስል
የጸሃይ ብርሃን ይዘው የገጠሙ እጆች

ብርሃናችሁን ከፍ አድርጉ

የአዳኙ ደቀመዛሙርት እንደመሆናችን መጠን፣ ቃል ኪዳናችንን ስንጠብቅ እና የክርስቶስን የሚመስል ህይወት ስንመራ ጎረቤቶቻችንንም እንባርካለን። መጽሐፈ ሞርሞን “የቤተክርስቲያኗ ሰዎች” ጌታ እንዲጠብቃቸው እና እንዲያበለጽጋቸው ከፈለጉ ጽድቅን መምረጥ ብቻ ሳይሆን የጻድቅ ድምጻቸውንም ማሰማት እንዳለባቸው ያስተምራል (አልማ 2፥3-7፣ እንዲሁም ሞዛያ 29፥27 ይመልከቱ)። ጌታ እምነታችንን እንድናካፍል እና ብርሃናችንን ከፍ አድርገን እንድንይዝ ይጠብቅብናል። “እነሆ፣እናንተ ከፍ የምታደርጉት ብርሃን ነኝ” (3 ኔፊ 18፥24)።

በቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ የሆኑት ፕሬዚዳንት ዳለን ኤች. ኦክስ እንዲህ ብለዋል “ በአገልግሎታችን እና በሥራችን መቀጠላችን መገለጥን ለማግኘት ብቁ ለመሆን ጠቃሚ መንገድ ነው“ ብለዋል። አክለውም፣ “እኛ የተጠራነው የጌታን መስፈርቶች እንድንመሰርት እንጂ የአለምን እንድንከተል አይደለም።”8

የጌታ ደቀ መዛሙርት በትምህርት ቤት፣ በሥራ ወይም በጨዋታ፣ በዕረፍት ጊዜ፣ በመጠናናት ቀጠሮ ወይም በበይነመረብ ላይ፣ “የክርስቶስን ስም ለመልበስ [አያፍሩም]” (አልማ 46፥21)። በቃላችን እና በስራችን፣ እግዚአብሔር እንዳለ እና ልጁን እንደምንከተል እንመሰክራለን።

“እምነታችን የተከፋፈለ አይደለም፣ ወይም በእርግጠኝነት መሆን የለበትም። እምነት ለቤተክርስቲያን ብቻ አይደለም፣ ለቤት ብቻ አይደለም፣ [ለትምህርት ቤት] ብቻ አይደለም” በማለት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን አማኝ የሆኑት የሃይማኖት ብዝሃነት ምሁር፣ ፖል ላምበርት ተናግረዋል። “ይህ ለምትሠሯቸው ነገሮች ሁሉ ነው።”9

የእኛ ምስክርነት፣ መልካም አርአያነት እና መልካም ስራዎች በሌሎች ላይ ሊኖረው ስለሚችለው ተጽእኖ አናውቅም። ነገር ግን ለእውነት ስንቆም እና የአዳኙን ብርሀን ከፍ አድርገን ስንይዝ ሰዎች ያስተውሉናል መንግስተ ሰማያትም ድጋፋቸውን ያሠጡናል።

ምስል
ከቤተመቅደሱ ውጪ የቆመች ሴት

ለየሃይማኖት ነጻነት ቁሙ

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ዓለማዊ ማህበረሰቦች በእምነት ሰዎች ላይ የሚያደርሱት የዚህ ዘመን የካህናት ተንኮል፣ በመፅሐፈ ሞርሞን ዘመን ከነበረው ያን ያህል የተለየ አይደለም። ሐይማኖት በህዝብ እና በፖለቲካዊ መድረኮች ውስጥ ያለውን ወሳኝ ሚናን የሚቃወሙ ሰዎች ድምፅ እየጨመረ ነው። ብዙ ትምህርት ቤቶችን እና ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ የሃይማኖት ተጽዕኖን የማይደግፉ አካላት እና መንግስታት ሥነ ምግባር የጎደለው ድርጊትን፣ አምላክ የለሽነትን እና የስነ-ምግባር አንፃራዊነትን በማስቀደም ላይ ናቸው።

ለሃይማኖታዊ መብታችን የማንቆም ከሆነ፣ በሃይማኖት ነፃነት ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች ስኬታማ ይሆናሉ። በቅርቡ “እንደቤተክርስቲያን የሁሉንም እምነቶች እንዲሁም የሚያሳምኑ ሰዎች እና እምነታቸውን የመናገር መብታቸውን በመከላከል ረገድ ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር እንተባበራለን”10 በማለት አስተምሪያለሁ።

ነፃ ምርጫን ማለትም የመምረጥ ነፃነታችንን አስመልክቶ በሰማይ ጦርነት ተካሂዶ ነበር። ነጻ ምርጫችንን ለማስጠበቅ የሃይማኖት ነጻነታችንን በመከላላከል ረገድ የእኛን ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠይቃል።

ንቁ የሆነ ሃይማኖታዊ እምነት ቤተሰቦችን፣ ማህበረሰቦችን እና ሀገራትን ያጠናክራል እንዲሁም ይጠብቃል። ለህግ ታዛዥነትን ይፈጥራል፣ ለህይወት እና ለንብረት የሚሰጥ ክብርን ያሰርፃል እንዲሁም ሲቪል ማህበረሰብን ለማስቀጠል የሚያስፈልጉትን የልግስና፣ የሀቀኝነት እና የሥነ ምግባርን በጎ ምግባሮችን ያስተምራል። ስለ እምነታችን በፍጹምይቅርታ መጠየቅ አያስፈልገንም።

የእኛ የሚስዮናዊ ጥረት፣ በቤተመቅደስ ውስጥ የምንሠራው የውክልና ስራ፣ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት የምናደርገው ጥረት እና ደስታችን ለሃይማኖታዊ እምነት እና ነፃነት መቆማችንን ይጠይቃል። ሌሎች ነፃነቶችን ሳናጣ ያንን ነጻነት ልናጣው አንችልም።

ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ ሲል አስተምራል፣ “ነፍሴን የሚያነሳሳው የነፃነት ፍቅር ነው—የመላው የሰው ዘር የዜጎች እና የሃይማኖት ነፃነት።”11 ከቤተክርስቲያን መሪዎች የሚሰጥን ምክር ስንከተል የሃይማኖት ነፃነት የእኛን ነፍስ ያነሳሳል፦

  • “ህዝባዊ ጠቀሜታ ስላላቸው ጉዳዮች መረጃ አግኙ ከዚያም በድፍረት እና በጨዋነት ተናገሩ።”12

  • “የሃይማኖት ነፃነት መሸርሸር በጥንካሬ እና በወንጌል እውቀት ለማደግ፣ በተቀደሱ ሥርዓቶች ለመባረክ እና ቤተክርስቲያኑን ለመምራት በጌታ ላይ ለመተማመን ያሉንን እድሎች በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳ ተገንዘቡ።”13

  • “እግዚአብሔር እንዳለ እና ትእዛዛቱ የሚያጸድቁት ፍፁም እውነቶች እንዳሉ ለማረጋገጥ በመናገር ቁሙ።”14

  • “እምነታችንን የመተግበር ነፃነታችንን የሚጎዱ ህጎችን ፈትኑ።”15

  • “መልካምን ለመስራት፣ ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ላይ እምነትን ለመገንባት እና ሌሎችን ወደ ደስተኛ ቦታ ለማምጣት ለመርዳት ወደ አለም ሂዱ።”16

  • ግብዓቶችን በreligiousfreedom.ChurchofJesusChrist.org እና በreligiousfreedomlibrary.org/documents ውስጥ አጥኑ።

ስናገለግል፣ ብርሃናችንን ከፍ አድርገን ስንይዝ እና ለሃይማኖት ነፃነት ስንቆም፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንገነባለን። ለቤተሠቦቻችን፣ ለማህበረሰቦቻችን እና ለአገሮቻችን “ብዙ መልካም ነገሮችን” ለማድረግ በምናደርገው ጥረት ጌታ ይባርከን።

ማስታወሻዎች

  1. “የቀዳሚ አመራር መልዕክት፣” በ Caring for Those in Need፥ 2022 Annual Report of The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints፣ 3፣ ChurchofJesusChrist.org።

  2. Caring for Those in Need፥ 2022 Annual Report፣ 4፣ ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

  3. Justserve.org/about። Justserve በ17 ሐገሮች ውስጥ በመስራት ላይ ይገኛል። በዚህ ተነሳሽነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እና ድርጅቶች እየተባረኩ ው።

  4. ኬትሊን ባንክሮፍት፣ “Church Donates $8.7 M as Part of Red Cross Collaboration፣” Church News፣ ሚያዚያ 22፣ 2023 (እ.አ.አ) 23 ይመልከቱ።

  5. ሜሪ ሪቻርድን፣ “Church Joins with Groups around the World to Tap into the Gift of Water፣” Church News፣ ግንቦት 27፣ 2023,(እ.አ.አ)፣ 12 ይመልከቱ።

  6. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “Helping the Poor and Distressed፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 6–8 ይመልከቱ።

  7. ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣“Opportunities to Do Good”ሊያሆና ግንቦት 2011 (እ.አ.አ)፣ 25።

  8. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “Testimony፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2009 (እ.አ.አ)፣ 94.

  9. ፖል ላምበርት፣ በራቸል ስተርዘር ጊብሰን፣ “Why Is There a Need for Faith in the Workplace?” ” Church News ሚያዝያ 22፣ 2023 (እ.አ.አ)፣ 16 ይመልከቱ።

  10. ሮናልድ ኤ ራዝባንድ፣ “To Heal the World፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 92።

  11. Teachings of Presidents of the Church፥ Joseph Smith (2011 (እ.አ.አ))፣ 345።

  12. ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “Religious Freedom—A Cherished Heritage to Defend” (address at Freedom Festival Patriotic Service, Provo, Utah, June 26, 2016), 5–6, speeches.byu.edu.

  13. ሮናልድ ኤ ራዝባንድ ፣“Free to Choose” (Brigham Young University devotional, Jan. 21, 2020), Jan. 21, 2020), 3, speeches.byu.edu.

  14. ዳለ ኤች አክስ “ Truth and Tolerance (Brigham Young University devotional፣ መሥከረም 11, 2011) 2፣ speeches.byu.edu።

  15. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “Truth and Tolerance፣” 4።

  16. ሮናልድ ኤ ራዝባንድ፣ “ Free to Choose፣” 5 speeches.byu.edu.

አትም