ሊያሆና
ስንጠመቅ በእርግጥ የምንገባው ቃል ምንድን ነው?
ሰኔ 2024 (እ.አ.አ)


“ስንጠመቅ በእርግጥ የምንገባው ቃል ምንድን ነው?፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ሰኔ 2024 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ሰኔ 2024 (እ.አ.አ)

ስንጠመቅ በእርግጥ የምንገባው ቃል ምንድን ነው?

ምስል
ጥምቀት

ጥምቀት፣ በአኒ ሄንሪ ኔደር

ቅዱሳት መጻህፍት፣ ስንጠመቅ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በላያችን ላይ ለመውሰድ፣ እግዚአብሔርን ለማገልገል እና ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ፈቃደኛ ለመሆን ቃል ኪዳን (ወይም ቃል) እንደምንገባ ያስተምሩናል ሞዛያ 18፥10 (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥37፣ 77 ተመልከቱ)።

በተጨማሪም ጥምቀት “ወደ እግዚአብሔር በረት ለመምጣት እና ሕዝቡ [ለመባል]” (ሞዛያ 18፥8) ያለንን ፍላጎት ለመፈጸም እንደሚረዳን ከቅዱሳት መጻህፍት እንማራለን። በሌላ አነጋገር፣ የተጠመቅንበት አንዱ ምክንያት የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተክርስቲያን ለመቀላቀል ስለምንፈልግ እና በክርስቶስ አንድ በመሆን የሚመጣውን ፍቅር እና የአባልነት ስሜት እንድንደሰትበት ስለምንፈልግ ነው።

ጌታን ለማገልገል እና ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ያለን ቁርጠኝነት በህይወታችን ውስጥ ብዙ ነገሮችን ሊያካትት ይችላል። ለምሳሌ “አንዳች[ን] የአንዳች[ንን] ሸክም ቀላል እንዲሆኑ ዘንድ ለመሸከም ፈቃደኞች [ለመሆን]፣ ከሚያዝኑት ጋር ለማዘን፤ መፅናናትን [የሚፈልጉትንም ለማፅናናት፣] እናም በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገርና፣ [በምንኖርበት] ቦታዎች ሁሉ … የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን [ልንቆም]” ቃል ገብተናል (ሞዛያ 18፥8–9)።

አትም