ሊያሆና
ሀይለኛ ግንኙነት
ነሐሴ 2024 (እ.አ.አ)


ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ነሐሴ 2024 (እ.አ.አ)

ሀይለኛ ግንኙነት

ቃል ኪዳን ከውል የበለጠ ነው፤ ይህም ግንኙነት ነው።

ምስል
አረንጓዴ መቀመጫዎች

ሽማግሌ ፒስተን እና ሽማግሌ ሞራስኮ በአርጀንቲና በቤታችን ውስጥ ቤተሰቤን ሲያስተምሩ የተቀመጡበት የአረንጓዴ መቀመጫዎች ፎቶ አሁንም አለኝ። በከፍተኛ የመንፈስ ሃይል በማስተማራቸው የተነሳ፣ ከሄዱ በኋላ የ10 ዓመት ታላቅ እህቴ እና እኔ (9 ዓመት) ያ ሃይል እንዲጋባብን ተስፋ በማድረግ እሮጠን መቀመጫዎቹን እንነካለን።

ሃይሉ ከመቀመጫዎቹ እንዳልመጣ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባለ የቃል ኪዳን ግንኙነት አማካኝነት እንደመጣ ወዲያውኑ ተማርኩኝ።

የእኔ የጥምቀት ልምድ

የመጀመሪያ ቃል ኪዳኔን በህዳር 13፣ 1977 (እ.አ.አ) ገባሁ። ስለጥምቀቴ ብዙም አላስታውስም፣ ነገር ግን ሽማግሌ ፒስተን ወደ ውሃው ውስጥ ስገባ ሲረዳኝ እና ሽማግሌ ሞራስኮ ጸጉሬ እንደረጠበ ማረጋገጫ ሲሰጠኝ አስታውሳለው። እንዲሁም አዲስ የአጥቢያ ጓደኞች ሲያቅፉኝ እና በአርጀንቲናው መልኩ ሲስሙኝ የተሰማኝን ደስታ እና አማኝ የሰማይ አባት ሴት ልጅ ለመሆን የተሰማኝን ጠንካራ ፍላጎት አስታውሳለው።

ምስል
ቤተሰብ በጥምቀት ላይ

ወጣት እህት ስፓነስ (መሃል ላይ) ከወላጆቿ (በስተግራ በኩል)፣ ከእህቷ ሲልቪና (በስተቀኝ በኩል) እና ከሽማግሌ ሞራስኮ ጋር።

ከዛ የተሰማኝ ደስታ ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንደመጣ ተገነዘብኩኝ። ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝን ቃል ኪዳኖች በታማኝነት ስጠብቅ፣ መንፈስ ቅዱስ ከእኔ ጋር ይሆናል። መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባለ የቃል ኪዳን ግንኙነት የሚመጣ ከሀይለኛ በረከቶች መካከል አንዱ ነው።

አሁን፣ ምክንያቶቼ፣ ሃሳቦቼ እና ተግባሮቼ ሲስተጓጎሉ፣ ለመሞከር ተስፋ አለኝ። ለምን? ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባንን መካፈል ቃል ኪዳኖቼን እንዳድስ እና አዲስ ቃል ኪዳኖችን በእየሳምንቱ እንዳደርግ ይረዳኛል። ለዚያም በረከት በጣም አመስጋኝ ነኝ።

የሞቀ የቃል ኪዳን ግንኙነት

ቃል ኪዳኖች በእኛ እና በእግዚአብሔር መካከል የሚደረጉ ኪዳኖች እንደሆኑ ብዙ ጊዜ እንሰማለን። ያ እውነት ሆኖ ሳለ፣ ቃል ኪዳኖች ይህን ብቻ አይደሉም። በእርግጥም፣ “ቃል ኪዳንን መጠበቅ ቀዝቃዛ የንግድ ስምምነት አይደለም ነገር ግን የሞቀ ግንኙነት ነው።”

ከሰማይ አባት እና ከአዳኙ ጋር የቃል ኪዳን ግንኙነትን እንዴት መፍጠር ትችላላችሁ? እናንተን ፍጹም በሆነ መልኩ ይወዷችኋል እና ሊባርኳችሁ ይፈልጋሉ (3 ኔፊ 14፥11 ተመልከቱ)። ነገር ግን ማንኛውም ባለ ሁለት መንገድ ግንኙነት ከሁለቱም አቅጣጫ ጊዜን እና ፍቅርን ይወስዳል።

ከእነርሱ ጋር ብዙ ጊዜን ለማሳለፍ ትፍልጋላችሁን? እነርሱ የሚያደርጉትን ነገሮች ስታደርጉ፣ ከእነርሱ ጋር እየተራመዳችሁ ናችሁ! በአስቸጋሪ ጊዜ ጓዳኛን እንደማዳመጥ፣ ከእህት/ከወንድም ጋር ለመጫወት ጊዜን እንደማዘጋጀት ወይም ብቸኝነት የሚሰማውን ሰው እንደማካተት አይነት ቀላል ሊሆን ይችላል። በቅርቡ በአርጀንቲና ውስጥ ብቸኝነት ለሚሰማው ጓደኛ የድምጽ መልዕክቶችን በመቅዳት እና መልዕክቶችን በመላክ ከእግዚአብሔር ጋር በመጓዝ ጊዜን አሳለፍኩኝ። ከጌታ ጋር በቤቱ ውስጥ ጊዜን ለማሳለፍ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያዬን ሁሌም ለማሳደስ ወሰንኩኝ። ከሰማይ አባት እና ከአዳኛችሁ ጋር ጊዜን ለማሳለፍ የሚረዳችሁን ሃሳቦች ለማግኘት መጸለይ ትችላላችሁ።

ግድ እንዳላችሁ ለእነርሱ ማሳየት ትፈልጋላችሁን? ለመጠበቅ ቃል ኪዳን የገባችሁትን ትዕዛዛት እንደ ህግጋት ዝርዝር ሳይሆን ፍቅራችሁን እደመግለጫ መንገድ ተጠቀሙበት። ለምሳሌ፣ የጥበብ ቃልን ለመጠበቅ ጤናማ ምግቦችን እንዴት ማብሰል እንዳለብኝ ተማርኩኝ። አሁን ሴት ልጆቼን ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ እያስተማርኳቸው ነኝ። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በፍቃደኝነት ስትጠብቁ፣ ለእርሱ እና ለአዳኙ ያላችሁ ፍቅር ያድጋል።

ከእግዚአብሔር እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለን የቃል ኪዳን ግንኙነት የበለጠ እንድናውቃቸው እና በህይወታችን ውስጥ የእነርሱን ሃይል እንዲኖረን ይረዳናል፣ ይህም የሚሆነው አረንጓዴ መቀመጫዎች መስጠት ከሚችሉት ይበልጥ ነው። እና ያ ሃይል ለዘለአለም ይቀይረናል!

ማስታወሻ

  1. አን ኤም. ማድሰን፣ በትሩማን ጂ. ማድሰን The Temple: Where Heaven Meets Earth [ቤተመቅደስ፦ ሰማይ ከምድር ጋር የምትገናኝበት] (2008 እ.አ.አ)፣ 69 ውስጥ።

አትም