ወርሀዊ የለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ መስከረም 2024 (እ.አ.አ)
ንስሐ መግባት ትፈራላችሁ?
በፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን መሠረት፣ መፍራት የሌለባችሁ ምክንያት እነሆ።
እናንተ የምትፈሩት ምንድን ነው? ሮለርኮስተርስ? የሒሣብ የትምህርት ክፍል? የኢሣይያስ መፅሐፍን ለመረዳት መሞከር?
ንሥሐ መግባትስ? ንስሃ የመግባት ሀሳብ በብርድ ልብሣችሁ ውስጥ መደበቅ ወይም ብዙ ቸኮሌት እንድትበሉ ካደረጋችሁ ይህ ጽሑፍ ለእናንተ ነው።
“እባካችሁን ንስሃ መግባት አትፍሩ ወይም ንስሃችሁን አታዘግዩት” ብለዋል ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን። ይህም ለጥሩ ምክንያት ነው። በፕሬዚዳንት ኔልሰን አባባል ንስሃ ስለመግባት ትክክል የሆኑ እና ያልሆኑ ነገሮች ቀጥሎ ቀርበዋል።
የእግዚአብሔርን ፍፁም ሥጦታ ተቀበሉ
ስለዚህ፣ ንስሐ የመግባትን ፍርሃት ለማሸነፍ ትችሉ ዘንድ በአዳኙ ለመታን ተዘጋጅታችኋልን? አትፀፀቱበትም።
ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፦ “ዓለም መዳን ያስፈልገው ስለነበረ፣ እንዲሁም እናንተ እና እኔ መዳን ስለሚያስፈልገን፣ [የሰማይ አባት] አዳኝ ልኮልናል።
“… የእግዚአብሔርን ፍፁም እና ውድ ሥጦታ እንቀበል። ሸክማችንን እና ኃጢአታችንን በአዳኙ እግር ሥር እንጣል እንዲሁም በንሥሃ እና በለውጥ የሚገኘውን ደስታ እናጣጥም።”
© 2024 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። የMonthly For the Strength of Youth Message, September 2024. ትርጉም። Amharic. 19343 506