ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያንን እንዴት እንደምንጠቀም


ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያንን መጠቀም፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2024 (እ.አ.አ) [2023 ( እ.አ.አ)]

ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያንን መጠቀም፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ 2024 (እ.አ.አ)

ቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍትን እያጠኑ

ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያንን መጠቀም

ይህ ጽሁፍ ለማን ነው?

ይህ ጽሁፍ መፅሐፈ ሞርሞንን—በግለሰብ ደረጃ፣ እንደ ቤተሰብ እና በቤተክርስቲያን ክፍሎች ውስጥ ለመማር ለሚፈልግ ለማንኛውም ሰው ይሆናል። ከዚህ በፊት ቅዱሳት መጻህፍትን ዘወትር የማታጠኑ ከነበረ፣ ይህ ጽሁፍ እንድትጀምሩ ይረዳችኋል። ቀድሞውኑ በቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ጥሩ ልምድ ካላችሁ፣ ይህ ጽሁፍ የበለጠ ትርጉም ያለው ተሞክሮ እንዲኖራችሁ ይረዳል።

ግለሰቦች እና ቤተሰቦች በቤት

ከሁሉም የተሻለው ወንጌልን የመማሪያ ስፍራ ቤት ነው። በቤተክርስቲያን ያሉ አስተማሪዎቻችሁ ሊረዷችሁ ይችላሉ እንዲሁም ከሌሎች የአጥቢያ አባላት ማበረታቻ ልታገኙ ትችላላችሁ። ሆኖም በመንፈሳዊ ለመቀጠል እናንተ እና ቤተሰባችሁ እለት ተእለት “የእግዚአብሄርን መልካም ቃል” መመገብ (ሞሮኒ 6:4 ይኖርባቸኋል፤ እንዲሁም ራስል ኤም. ኔልሰን“Opening Remarks፣” ሊያሆና፣ ሕዳር 2018 [እ.አ፣አ] 6–8)ይመልከቱ።

ይህንን ጽሁፍ ለእናንተ በሚረዳ በማንኛውም መንገድ ተጠቀሙበት። መዘርዝሮቹ በመጽሃፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ዘላለማዊ እውነቶችን ያጎላሉ እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ፣ ከቤተሰባችሁ ወይም ከጓደኞቻችሁ ጋር ቅዱሳት መጻህፍትን ለማጥናት የሚረዱ ሃሳቦችን እና ተግባራትን ይጠቁማሉ በምታጠኑበት ጊዜ፣ ለእናንተ ትርጉም ያላቸውን ዘላለማዊ እውነቶች እንድታገኙ የመንፈስን ምሪት ተከተሉ። እግዚአብሄር ለናንተ ያለውን መለእክት ፈልጉ እንዲሁም የምትቀበሏቸውን መነሳሳቶች ተከተሉ።

አስተማሪዎች እና ተማሪዎች በቤተክርስቲያን

የመጀመሪያ ክፍልን፣ የወጣቶች ወይም የጎልማሶች የሰንበት ትምህርት ክፍልን፣ የአሮናዊ ክህነት ቡድንን ወይም የወጣት ሴቶች ክፍልን የምታስተምሩ ከሆነ ለማስተማር በምትዘጋጁበት ጊዜ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ያሉትን መዘርዝሮች እንድትጠቀሙ ትበረታታላችሁ። ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት ስርአተ ትምህርት ነው። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ያሉት የትምህርት ሃሳቦች በቤት አና በቤተክርስቲያን ውስጥ ለመማር የተዘ ጋጁ ናቸው። ለማስተማር ስትዘጋጁ በቅዱሳን ጽሁፎች ካሏችሁ ከራሳችሁ ተሞክሮዎች ጀምሩ። እጀግ አስፈላጊው ዝግጅታችሁ የሚከናወነው ቅዱሳት ጽሁፎችን ስትመረምሩ እና የመንፈስ ቅዱስን መነሳሳትን ስትሹ ነው። ይበልጥ እንደ ሰማይ አባት እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትሆኑ የሚረዷችሁን ዘላለማዊ እውነቶች ፈልጉ። ኑ፣ ተከተሉኝ እነዚህን አንዳንድ እውነቶች እንድትለዩ እና የቅዱሳት ጽሁፎችን አንደምታ እንድትገነዘቡ ሊረዳችሁ ይቸላል።

ወንጌልን ለመማር ከሁሉም የተሻለው መንገድ ቤት ተኮር እና በቤተክርስቲያን የተደገፈ መሆኑን አስታውሱ፡፡ በሌላ አነጋገር የአናንተ ዋና ኃላፊነት የምታስተምሯቸው ሰዎች ወንጌልን በቤት ውስጥ ለመማር እና ለመኖር የሚያደርጉትን ጥረት መደገፍ ነው። ልምዶቻቸውን፣ ሃሳቦቻቸውን እና በቅዱሳት መጻህፍት ስለሚገኙ ሃረጎች ያሏቸውን ጥያቄዎች እንዲያካፍሉ እድሎችን ስጧቸው። ያገኟቸውን ዘላለማዊ እውነቶች እንዲያጋሩ ጋብዟቸው። ይህ የአንድን ጽሁፍ የተወሰነ ክፍል ከመሸፈን የበለጠ አስፈላጊ ነው።

የመጀመሪያ ክፍል

የመጀመሪያ ክፍልን ለማስተማር የምታደርጉት ዝግጅት የሚጀምረው በግል እንዲሁም ከቤተሰባችሁ ጋር መጽሐፈ ሞርሞንን በምታጠኑበት ጊዜ ነው። ይህንን ስታደርጉ፣ በመጀመሪያ ክፍላችሁ ውስጥ ያሉትን ልጆች አስመልክቶ ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጡ መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን እና ሃሳቦችን ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ። ጸልዩ፤ ከዚያም መንፈስ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲማሩ እንድትረዷቸው በሃሳቦች ሊያነሳሳችሁ ይችላል።

ለማስተማር በምትዘጋጁበት ጊዜ፣ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ያሉትን የማስተማሪያ ሃሳቦች በማገላበጥ ተጨማሪ መነሳሳትን ልታገኙ ትችላላችሁ።ሁ። በኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው እያንዳንዱ መዘርዘር “ልጆችን ለማስተማር የሚጠቅሙ ሃሳቦች” የሚል ክፍል አለው። እነዚህን ሀሳቦች መነሳሳት እንዲሰማችሁ እንደሚያደርጉ ጥቆማዎች ውሰዷቸው። በመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ያሉትን ልጆች ታውቋቸዋላችሁ—እንዲሁም ከእነሱ ጋር በክፍል ውስጥ በምትገናኙበት ጊዜ የበለጠ በደንብ ታውቋቸዋላችሁ። እግዚአብሄርም ያውቃቸዋል፤ ስለዚህም እነሱን ለማስተማር እና ለመባረክ በምትችሉባቸው ከሁሉም የተሻሉ መንገዶች ያነሳሳችኋል።

በክፍላችሁ ያሉ ልጆች በኑ፣ ተከተሉኝ ውስጥ ያሉትን አንዳንድ መልመጃዎች አስቀድመው ሰርተው ሊሆን ይችላል። ያ መልካም ነው። መደጋገም ጥሩ ነው። ልጆቹ በቤት የተማሯቸውን ነገሮች አንዳቸው ለሌላቸው እንዲያካፍሉ መጋበዝን ግምት ውስጥ አስገቡ—ሆኖም፣ ልጆች በቤት ውስጥ ባይማሩም እንኳን ሊሳተፉ የሚችሉባቸውን መንገዶች ማቀድም አለባችሁ። ልጆች እነዚህን እውነቶች በተለያዩ አክቲቪቲዎች በተደጋጋሚ ሲማሩ የወንጌልን እውነቶች በላቀ ብቃት ይማራሉ። አንድ የመማር አክቲቪቲ ለልጆቹ ውጤታማ ሆኖ ካገኛችሁት በተለይ ትንንሽ ልጆችን እያስተማራችሁ ከሆነ ድገሙት። ባለፈው ትምህርት ጥቅም ላይ የዋለ አክቲቪቲን መከለስም ትችላላችሁ።

አምስት እሑዶች ባሏቸው ወራት ውስጥ፣ የመጀመሪያ ክፍል አስተማሪዎች በአምስተኛው እሑድ መርሐ ግብር የተያዘለትን ኑ፣ ተከተሉኝ መዘርዝር በ“አባሪ ለ፦ ልጆች ለእድሜልክ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንገድ ላይ እንዲሆኑ ማዘጋጀ” ውስጥ ባሉት አንድ ወይም ከአንድ በላይ የትምህርት አክቲቪቲዎች ተኳቸው።

የወጣቶች እና የጎልማሶች የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍሎች

በሰንበት ትምህርት ቤት ክፍሎች የምንሰበሰብበት አንዱ ዋና ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል በምናደርገው ጥረት እርስ በርስ ለመደጋገፍ እና ለመበረታታት ነው። ይህንን ማድረግ የሚቻልበት ቀላሉ መንገድ “በዚህ ሳምንት በኑ፣ ተከተሉኝአማካኝነት መጽሐፈ ሞርሞንን ስታጠኑ መንፈስ ቅዱስ ምን አስተማራችሁ?” የሚል ጥያቄን በመጠየቅ ነው። የዚህ ጥያቄ መልስ በኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌሉ ላይ ያለን እምነት ወደሚገነባ ትርጉም ያለው ውይይት ሊያመራ ይችላል።

ከዚያም በኑ፣ ተከተሉኝ ውስጥ ባሉት የጥናት ሐሳቦች ላይ በመመርኮዝ ውይይት መጋበዝ ትችላላችሁ። ለምሳሌ አንድ የጥናት ሃሳብ አልማ 36 ውስጥ መፈለግን እና አዳኙ በንስሃ ውስጥ ስላለው ሚና የሚያስተምር የቃላት ዝርዝር ማዘጋጀትን ሊጠቁም ይችላል። የክፍል አባላት ያገኟቸውን ቃላት እንዲያካፍሉ እና እንዲናገሩ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ። ወይም ጊዜ ወስዳችሁ በክፍል ደረጃ በጋራ ዝርዝሩን ልታዘጋጁ ትችላላችሁ።

የአሮናዊ ክህነት ቡድን እና የወጣት ሴቶች ክፍሎች

የአሮናዊ ክህነት ቡድን እና የወጣት ሴቶች ክፍሎች እሁድ እሁድ በሚገናኙበት ጊዜ ዓላማቸው በተወሰነ መልኩ ከሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል የተለየ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመማር ረገድ እርስ በርስ ከመረዳዳት በተጨማሪ እነዚህ ቡድኖች የመዳን እና በዘላለም ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግ ስራን ስለማከናወን በጋራ ለመምከር ይገናኛሉ(አጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል1.2 ይመልከቱ)። ይህንን በክፍል እና በቡድን አመራሮች መመሪያ ያደርጋሉ።

በዚህ ምክንያት፣ እያንዳንዱ የቡድን ወይም የክፍል አመራር አባል ለምሳሌ ወንጌልን በመኖር፣ የተቸገሩ ሰዎችን በማገልገል፣ ወንጌልን በማካፈል ወይም በቤተመቅደስ እና በቤተሰብ ታሪክ ሥራ በመሳተፍ ረገድ ስለሚደረጉ ጥረቶች የተመለከተ ውይይትን በመምራት መጀመር አለበት።

ከዚህ በጋራ ክሚመካከሩበት ጊዜ በኋላ አንድ አስተማሪ ወንጌልን በአንድ ላይ በመማር ረገድ ክፍሉን ወይም ቡድኑን ይመራል። ጎልማሳ መሪዎች ውይንም የክፍል ወይንም የቡድን አባላት እንዲያስተምሩ ሊመደቡ ይችላሉ። የክፍል ወይንም የቡድን አመራር ከጎልማሳ መሪዎች ጋር በመመካከር እነዚህን ምደባዎች ያከናውናሉ።

እንዲያስተምሩ የሚመደቡ ሰዎች በኑ፣ ተከተሉኝ ሳምንታዊ መዘርዝር ውስጥ ባሉት የመማር ሃሳቦች በመጠቀም መዘጋጀት አለባቸው። በያንዳንዱ መዘርዝር ውስጥ ያለው ይህ ምልክት የሴሚናሪ ምልክት በተለይ ለወጣቶች የሚሆን አክቲቪቲን ያሳያል። ሆኖም በመዘርዝሩ ውስጥ ያሉት ማንኛቸውም ሃሳቦች ለወጣቶች እንደትምህርት እክቲቪቲ በመሆን ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

ለቡድን ወይም ለክፍል ስብሰባዎች ናሙና አጀንዳ ለማግኘት አባሪ መን ይመልከቱ።