ኑ፣ ተከተሉኝ 2024 (እ.አ.አ)
ጥር 1–7 ፦ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት። የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ ገፆች


“ጥር 1–7 ፦ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት። የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ ገፆች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

“ጥር 1–7 የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ ገፆች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለቤት እና ለቤተክርስቲያን፦ መፅሐፈ ሞርሞን 2024 (እ.አ.አ) [2024 (እ.አ.አ)]

ሞርሞን በወርቅ ሰሌዳዎች ላይ  እየጻፈ

ጥር 1–7 ፦ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት።

የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ ገፆች

1 ኔፊ ምዕራፍ 1 ከመድረሳችሁ በፊት እንኳን፣ መፅሐፈ ሞርሞን ተራ መፅሐፍ እንዳልሆነ ትረዳላችሁ። መግቢያ ገፆቹ ከሌሎች በተለየ መልኩ የኋላ ታሪክን ማለትም የመላዕክት ጉብኝትን፣ የጥንት መዝገብ በተራራ ላይ ለክፍለ ዘመናት መቀበሩን እና አንድ ወጣት መዝገቡን በእግዚአብሔር ኃይል መተርጎሙን ጨምሮ ይገልፃሉ። መፅሐፈ ሞርሞን የጥንት አሜሪካ ስልጣኔዎች ታሪክ ብቻ አይደለም። “ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ” እና መፅሐፉ እንዴት መጻፍ፣ መጠበቅ እና ለእኛ መገኘት እንዳለበት እግዚአብሔር እራሱ እንደመራ የመፅሐፈ ሞርሞን የርዕስ ገፅ ሁሉንም ለማሳመን ይጥራል። በዚህ ዓመት መፅሐፈ ሞርሞንን ስታነቡ ጸልዩበት እንዲሁም ትምህርቶቹን ተግባራዊ አድርጓቸው፤ የአዳኙን ኃይል ወደ ሕይወታችሁ ትጋብዛላችሁ። ሶስቱ ምስክሮች በምስክርነታቸው “[በእኔ] አመለካከት ይህ ድንቅ ነው” በማለት እንደተናገሩት እናንተም እንደዚያ ለማለት ትነሳሱ ይሆናል።

በቤት እና በቤተክርስቲያን ለመማር የሚረዱ ሃሳቦች

የመፅሐፈ ሞርሞን የርዕስ ገፅ

መፅሐፈ ሞርሞንን ማጥናት በኢየሱስ ክርስቶስ ያለኝን እምነት ሊያጠነክር ይችላል።

የመፅሐፈ ሞርሞን የርዕስ ገፅ ከርዕስ የበለጠን ነገር ያቀርባል። ሌሎች ነገሮችን ጨምሮ የዚህን ቅዱስ መዝገብ ብዙ ዓላማዎች ይዘረዝራል። እነዚህን ዓላማዎች በርዕስ ገጹ ውስጥ ፈልጉ። ስታሰላስሉ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎች ይረዷችኋል፦ መፅሐፈ ሞርሞን የተሰጠን ለምንድን ነው? መፅሐፈ ሞርሞን ከሌሎች መፅሐፎች የሚለየው በምንድን ነው?

በዚህ ዓመት ውስጥ መፅሐፈ ሞርሞንን ለማንበብ የግል ወይም የቤተሰብ እቅድን ለማውጣት ምናልባት አሁን ጥሩ ሰዓት ሊሆን ይችላል። መቼ እና የት ታነባላችሁ? መንፈስ ቅዱስን ወደ ጥናታችሁ መጋበዝ የምትችሉት እንዴት ነው? በምታጠኑበት ወቅት የምትፈልጉት አንድ የተለየ ነገር አለ? ለምሳሌ፣ በርዕስ ገፁ ላይ ያገኛችኋቸውን አላማዎች የሚያሟሉ ገፆችን ትፈልጉ ይሆናል። በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁን እምነት የሚገነቡ የጥቅስ ዝርዝሮችን ልታወጡ ትችላላችሁ።

2 ኔፊ 25፥26ሞዛያ 3፥5–8አልማ 5፥487፥10–13ሔለማን 5፥123 ኔፊ 9፥13–1811፥6–14ሞሮኒ 10፥32–33 ይመልከቱ።

ትንቢታዊ ቃልኪዳን። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ብለዋል፣ “[በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ] በምታጠኑት ነገር ላይ ስታሰላስሉ የሰማይ መስኮቶች እንደሚከፈቱ፣ እንዲሁም ለእናንተ ጥያቄዎች መልስ እና ለግል ህይወታችሁ መመሪያ እንደምትቀበሉ ቃል እገባለሁ” (“መፅሐፈ ሞርሞን፦ ካለሱ ሕይወታችሁ ምን ይሆን ነበር? [The Book of Mormon: What Would Your Life Be Like without It?]፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2017 (እ.አ.አ)፣ 62–63)።

የሴሚናሪ ምልክት

የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ፤ “የሶስቱ ምስክሮች ምስክርነት”፤ “የስምንቱ ምስክሮች ምስክርነት

የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክር መሆን እችላለሁ።

እንደ ሶስቱ እና ስምንቱ ምስክሮች የወርቅ ሰሌዳውን ባታዩትም እንኳን፣ መንፈስ ቅዱስ መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ይመሰክርላችኋል። የእነሱን ቃላት ስታነቡ ምስክርነቶቻቸው የእናንተን ምስክርነት እንዴት እንደሚያጠነክር አስቡ።

እነዚህ ምስክሮች ስለ መጽሐፈ ሞርሞን ያላቸውን ምስክርነት ስላካፈሉበት መንገድ ምን ያነሳሳችኋል? ስለ መፅሐፈ ሞርሞን በተለይም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ምስክርነት እንዴት እንደምታካፍሉ አሰላስሉ። ለምሳሌ፣ ከዚህ በፊት ስለ መፅሐፈ ሞርሞን ሰምቶ ከማያውቅ ሰው ጋር እየተነጋገራችሁ እንደሆን አስቡ። ለእሱ ወይም ለእሷ ምን ትነግሯቸዋላችሁ? ጓደኛችሁ እንዲያነበው/ድታነበው ለማነሳሳት የምትሞክሩት እንዴት ነው? የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያን መከለስን አስቡ። ለጓደኛችሁ ለማካፈል የሚጠቅም ዝርዝርን እዚያ ውስጥ ታገኙ ይሆናል። የሚከተሉት ቪዲዮዎች ሃሳብ ሊሰጧችሁ ይችላሉ፦

  • “የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ”

  • “መፅሐፈ ሞርሞን ምንድን ነው? የ60 ሰከንዶች አጠቃላይ እይታ”

  • “የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪክ”

ለአንድ ጓደኛ ሰለ መፅሐፈ ሞርሞን የምታካፍሉትን ነገሮች ዝርዝር መፃፍን አስቡ። የመፅሐፈ ሞርሞን መተግበሪያን በመጠቀም መፅሐፈ ሞርሞንን ለማካፈል ሞክሩ።

በተጨማሪም ሮናልድ ኤ. ራስባንድ፣ “ይህ ቀን [This Day]፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 25–28፤ የወንጌል ርዕሶች “መፅሐፈ ሞርሞን፣” የወንጌል ቤተመጽሐፍት “አንድ መልአክ ከሰማይ [An Angel from on High]፣” መዝሙር፣፣ ቁጥር 13 ይመልከቱ።

ጆሴፍ ስሚዝ እና ሶስቱ ምስክሮች በአንድ ላይ ሲጸልዩ

ሶስቱ ምስክሮች ስለ መፅሐፈ ሞርሞን መሰከሩ።

የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ምስክርነት

የመፅሐፈ ሞርሞን አመጣጥ ተአምር ነበር።

የሆነ ሰው መፅሐፈ ሞርሞን ከየት እንደመጣ ቢጠይቃችሁ፣ ምላሻችሁ ምን ይሆናል? መፅሐፈ ሞርሞንን ለእኛ በመስጠት ሂደት ውስጥ የእግዚአብሔርን ሚና እንዴት ትገልጹታላችሁ? የጆሴፍ ስሚዝን ምስክርነት በምታነቡበት ወቅት እሱ እንዴት እንደሚገልጸው ትኩረት ስጡ። ባነበባችሁት መሰረት እግዚአብሔር ስለ መፅሐፈ ሞርሞን ጠቀሜታ ምን የሚሰማው ይመስላችኋል?

እንዲሁም ኡሊሴስ ሶአሬስ፣ “የመፅሐፈ ሞርሞን መምጣት [The Coming Forth of the Book of Mormon]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 32–35፤ ቅዱሳት፣ ቅፅ 1፣ የእውነት መሥፈርት [The Standard of Truth]21–30፤ የወንጌል አርዕስቶች ጽሁፎች፣ “የመፅሐፈ ሞርሞን ትርጉም [Book of Mormon Translation]፣” የወንጌል ቤተ መጽሐፍትን ተመልከቱ።

ተጨማሪ ሃሳብ ለማግኘት የዚህን ወር ሊያሆና እና ለወጣቶች ጥንካሬ መጽሔቶች እትሞችን ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር የሚረዱ ሀሳቦች

የመፅሐፈ ሞርሞን የርዕስ ገፅ

መፅሐፈ ሞርሞንን ማጥናት በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት እንዲኖረኝ ይረዳኛል።

  • ልጆቻችሁ የመፅሐፈ ሞርሞንን ቅጂ እንዲመለከቱ እና እንዲይዙ ፍቀዱላቸው። ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ወደሚለው ንኡስ ርዕስ እንዲጠቁሙ እርዷቸው። “ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆን፣ ዘላለማዊ አምላክ እንደሆነ፣ እራሱን ለሁሉም ሀገሮች እንደገለጸ” የሚለውን ሃርግ በርዕስ ገጹ ላይ እንዲያገኙም ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ይህ ማለት መፅሐፈ ሞርሞን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምረናል ማለት እንደሆነ አስረዷቸው። መፅሐፈ ሞርሞን በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን እምነት እንዴት እንዳጠነከረ በአጭሩ ንገሯችው። ስለሚወዷቸው የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች ጠይቋቸው። “የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች” (የልጆች የመዝሙር መጽሐፍ፣ 118–19) መዘመር ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹን ታሪኮች ሊያስታውሳቸው ይችላል።

መፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ

መፅሐፈ ሞርሞን የሐይማኖታችን የማዕዘን ድንጋይ ነው።

  • የዚህ ሳምንት የአክቲቪቲ ገጽ እና ከታች ያለው ምስል ልጆቹ በየመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ ውስጥ ያሉትን “መፅሐፈ ሞርሞን የሐይማኖታችን የመሠረት [የቅስት አናት መካከለኛ] ድንጋይ ነው” የሚሉትን የጆሴፍ ስሚዝ ቃላት እንዲረዱ ያግዛቸዋል። እንዲሁም በቅስቱ አናት መካከለኛ ድንጋይ ያለው ቅስት መገንባት ወይም መሳል አስደሳች ሊሆን ይችላል። የማዕዘን ድንጋዩ [በቅስቱ አናት ያለው መካከለኛ ድንጋይ] ቢነሳ ምን ሊፈጠር ይችላል? መጽሐፈ ሞርሞን ባይኖረን ኖሮ ምን ይፈጠር ነበር? የመፅሐፈ ሞርሞንን እውነታ ስንቀበል ምን ተጨማሪ ነገር እንደምንረዳ ለማወቅ የመግቢያውን የመጨረሻ አንቀፅ በጋራ ልታነቡ ትችላላችሁ። መፅሐፈ ሞርሞንን በኢየሱስ ክርስቶስ ላለን እምነት እንዴት የማዕዘን ድንጋይ [በቅስት አናት ያለ መካከለኛ ድንጋይ] ማድረግ እንችላለን?

በቅስት አናት ያለ መካከለኛ ድንጋይ አፅንቶ የያዘው የድንጋይ ቅስት

መፅሐፈ ሞርሞን የሐይማኖታችን የማዕዘን ድንጋይ [በቅስት አናት ያለ መካከለኛ ድንጋይ] ነው።

የሶስቱ ምስክሮች ምስክርነት”፤ “የስምንቱ ምስክሮች ምስክርነት

የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክር መሆን እችላለሁ።

  • ለልጆቻችሁ ምስክርነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማስረዳት እነሱ ያላዩትን ነገር ግን እናንተ ያያችሁትን ነገር ልትገልጹላቸው ትችላላችሁ። ከዚያም ተመሳሳይን ነገር ለእናንተ እንዲያደርጉ ፍቀዱላቸው። ይህ መፅሐፈ ሞርሞን የተተረጎመበትን የወርቅ ሰሌዳዎች ወደተመለከቱት ወደ 11 ሰዎች ንግግር ሊመራ ይችላል። ምስክርነቶቹን በጋራ ስታነቡ እነዚህ ምስክሮች ስለ ምስክርነታቸው ሌሎች እንዲያውቁ ለምን እንደፈለጉ ልትናግገሩ ትችላላችሁ። ስለ መፅሐፈ ሞርሞን ለማን መናገር እንፈልጋለን?

የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ምስክርነት

መፅሐፈ ሞርሞን የተሰጠን በእግዚአብሔር ኃይል ነው።

ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ወር ጓደኛ መጽሔት እትም ይመልከቱ።

ጆሴፍ የወርቅ ሰሌዳዎችን ከሞሮኒ ሲቀበል

ሞሮኒ የወርቅ ሰሌዳዎችን ሰጠ፣ በጌሪኤል. ካፕ