Scripture Stories
ስለመፅሐፈ ሞርሞን


“ስለመፅሐፈ ሞርሞን፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

ስለመፅሐፈ ሞርሞን

ኢየሱስ ክርስቶስ እና ህዝቡ በአሜሪካ ውስጥ

ምስል
ኢየሱስ በሰማያዊ ብርሃን

መፅሐፈ ሞርሞን ቅዱስ መፅሀፍ ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከረጅም ጊዜ በፊት አሜሪካን አለመጎብኘቱ ያስተምረናል። ከመፅሐፈ ሞርሞን ስለ ኢየሱስ ወንጌል መማር እንችላለን። አሁን እንዴት ሰላም እንደሚኖረን እና አንድ ቀን እንደገና ከእግዚአብሔር እና ከኢየሱስ ጋር እንዴት መኖር እንደምንችል ያስተምረናል።

የመፅሐፈ ሞርሞን ርዕስ ገፆችየመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ3 ኔፊ 11

ምስል
ነቢይ እና እናት ከልጆች ጋር

መፅሐፈ ሞርሞን የተፃፈው በእግዚአብሔር ነቢያት ነው። ሰሌዳዎች በሚባሉ የብረት ገጾች ላይ ጽፈው ነበር። የእነርሱ ታሪኮች እና ምስክርነቶች በኢየሱስ እምነት እንዲኖረን ይረዱናል። ከረጅም ጊዜ በፊት በአሜሪካ ይኖሩ ስለነበሩ ብዙ የህዝብ ቡድኖች ፅፈዋል።

የመፅሐፈ ሞርሞን ርዕስ ገፆየመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ

ምስል
ኔፊ እና ቤተሰቡ በመርከብ ላይ

አንዱ ቡድን ኢየሱስ ከመወለዱ 600 አመት በፊት ከኢየሩሳሌው ወደ አሜሪካ መጡ። ላማናውያን እና ኔፋውያን ተብለው የሚጠሩ ሁለት ሀገሮች ሆኑ።

የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ1 ኔፊ 1፥4

ምስል
ያሬዳውያን ግንቡን ለቀው ሲሄዱ

ከዚህ ብዙ ቀደም ብሎ ሌላ ቡድን ከባቤል ግንብ ወደ አሜሪካ መጥተዋል። እነርሱም ያሬዳውያን ተብለው ይጠሩ ነበር።

የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያኤተር 1፥33–43

ምስል
ሳሙኤል ስለኢየሱስ መወለድ ሲያስተምር

የእግዚአብሔር ነቢያት ሕዝቡን አስተማሩ። ሕዝቡ ሲያዳምጡና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ሲያከብሩ፣ እርሱም ይረዳቸው ነበር። ነቢያት ስለኢየሱስ አስተማሩ እንዲሁም በኢየሩሳሌም እንደሚወለድ ተናገሩ። ኔፋውያን እና ላማናውያን ኢየሱስ ከሞቱ በኋላ እንደሚጎበኛቸው ተማሩ።

2 ኔፊ 1፥2025፥12–1426፥1፣ 3፣ 9ሞዛያ 3፥5–11አልማ 7፥9–13ሔላማን 3

ምስል
ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ከህጻናት ጋር

ልክ ነቢያት እንዳሉት ኢየሱስ መጣ። ኢየሱስ ከሞተ እና ከሞት ከተነሳ በኋላ፣ ህዝቡን ጎበኘ። እያንዳንዱ ሰው በእጆቹ እና እግሮቹ ላይ ያሉትን የምስማር ምልክቶች እንዲዳሡ ፈቀደ። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አወቁ። ወንጌሉን አስተማረ፣ ህዝቡም ጻፉት። ስለኢየሱስ ጉብኝት ለብዙ አመታት ተነጋገሩበት።

3 ኔፊ 11፥7–15፣ 31–4116፥44 ኔፊ 1፥1–6፣ 13–22

ምስል
ሞርሞን የወርቅ ሰሌዳዎችን ይዞ

ሞርሞን ከኢየሱስ ጉብኝት ጥቂት መቶ ዓመታት በኋላ ይኖረ የነበረ ነቢይ ነበር። በሞርሞን የህይወት ዘመን፣ ሕዝቡ ጌታን መከተል አቆሙ። ሞርሞን ከእርሱ በፊት ይኖሩ የነበሩ ነቢያት ጽሑፎች ነበሩት። ብዙዎቹን ጽሁፎቻቸውን በአንድ የሰሌዳዎች ስብስብ ውስጥ አስቀመጣቸው። እነዚህ ፅሁፎች መፅሐፈ ሞርሞን ሆነዋል።

የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያየሞርሞን ቃላት 1፥2–9ሞርሞን 1፥2–4፣ 13–17

ምስል
ሞሮኒ የወርቅ ሰሌዳዎችን ሲቀብር

ሞርሞን ከመሞቱ በፊት፣ ሰሌዳዎቹን ለልጁ ሞሮኒ ሰጠ። በሞሮኒ በህይወት በነበረበት ወቅት፣ ሰዎቹ በጣም መጥፎ ነገሮችን ያደርጉ ነበር። በኢየሱስ የሚያምኑትን ሁሉ ለመግደል ይፈልጉ ነበር። ሞሮኒ ከእርሱ በኋላ የሚኖሩ ሰዎችን ለመርዳት ፈለገ፣ ስለዚህም በሰሌዳዎቹ ላይ የተጨማሪ ነገሮችን ጻፈና ይጠበቁ ዘንድ ቀበራቸው።

የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያየሞርሞን ቃላት 1፥2–2ሞርሞን 8፥1–4፣ 14–16ሞሮኒ 1

ምስል
መልዓኩ ሞሮኒ ለጆሴፍ ስሚዝ ሲገለጽለት

ከብዙ አመታት በኋላ፣ በ1823 (እ.አ.አ)፣ ሞሮኒ መልአክ ሆኖ ወደ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ መጣ። ጆሴፍ ሰሌዳዎቹን የት እንደሚያገኛቸው ሞሮኒ ነገረው። በእግዚአብሔር እርዳታ፣ ጆሴፍ በሰሌዳዎቹ ላይ የተጻፉትን ተረጎመ።

የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1

ምስል
እህት እና ወንድም ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነቡ

አንድ ነገር እውነት እንደሆነ እንድታውቁ እንዲረዳችሁ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ይልካል። መፅሐፈ ሞርሞንን ስታነቡ ስለእውነትነቱእግዚአብሔርን በፀሎት መጠየቅ ትችላላችሁ። በተመሳሳይ መንገድ፣ ኢየሱስ አዳኛችሁ እንደሆነ እና እንደሚወዳችሁ ማወቅ ትችላላችሁ።

የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያሞሮኒ 10፥3–5

አትም