“አልማ እና ቆሪሆር፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
አልማ እና ቆሪሆር
እግዚአብሔር እውን እንደሆነ ማመን
ቆሪሆር የሚባል ሰው ወደ ዛራሔምላ ምድር መጣ። እግዚአብሔርና ኢየሱስ ክርስቶስ እውን እንዳልሆኑ ለሰዎች ተናገረ።
ቆሪሆር ሰዎች አንድን ነገር ማወቅ የሚችሉት ካዩት ብቻ ነው አለ። በኢየሱስ ባመኑ ሰዎችን ላይ አሾፈ።
ቆሪሆር፣ ሰዎች የእግዚአብሔር ትእዛዛት እንደማያስፈልጓቸው ተናገረ። ሰዎች የፈለጉትን ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይችላሉ አለ። ብዙ ሰዎች አመኑት። መጥፎ ነገሮችን ለማድረግም ወሰኑ።
ቆሪሆር አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎችን ለማስተማር ሞከረ፣ ነገር ግን እነሱ አላመኑትም። አስረው አባረሩት። በምትኩ ወደ ጌዴዎን ምድር ሄደ። በዚያም ያሉት ሰዎች አሰሩት። ወደ አልማ ላኩት።
ቆሪሆር እግዚአብሔር የለም በማለት ለአልማ ነገረው። አልማ እና ሌሎች ካህናት ለህዝቡን እየዋሹ ነው አለ። ቆሪሆር ህዝቡ የማይረባ ባህል እንዲከተል እያደረጉ እንደሆነ ተናገረ። ከህዝቡም ገንዘብ እየወሰዱም ነው አለ። አልማ ይህ እውነት እንዳልሆነ ያውቅ ነበር። በእግዚአብሔርና በኢየሱስ እምነት አለው።
አልማ ነቢያት እና በምድር ላይ ያለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር እንዳለ ሰዎች እንዲያውቁ ይረዳል አለ። ቆሪሆር ተጨማሪ ማረጋገጫ ፈለገ። አልማ ለቆሪሆር ማስረጃ እንደሚሰጥ ተናገረ። እግዚአብሔር ቆሪሆር መናገር እንዳይችል እንደሚያደርግ ተናገረ። አልማ ይህን እንደተናገረ ቆሪሆር መናገር አቃተው።
ቆሪሆር እግዚአብሔር መኖሩን እንደሚያውቅ ጻፈ። ሁልጊዜም ያውቅ ነበር። ሰይጣን እንዳታለለውም ጻፈ። ሰይጣን ቆሪሆር ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ኢየሱስ ውሸት እንዲያስተምር ነግሮት ነበር። ሕዝቡ ስለ ቆሪሆር እውነቱን ሲያውቁ አስተምሮቱን ማመን አቆሙ። ንስሐ ገብተው ኢየሱስን እንደገና መከተል ጀመሩ።