“ቴአንኩም፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
ቴአንኩም
ህዝቡን ጠባቂ
ቴአንኩም በሻምበል ሞሮኒ ሠራዊት ውስጥ መሪ ነበር። የኔፋውያንን ከተሞች ከላማናውያን ለመጠበቅ ይሞክር ነበር።
አማሊቅያ የላማናውያን ንጉሥ የሆነ ኔፋዊ ነበር። በኔፋውያን ላይም መንገስ ፈለገ። ኔፋውያንን አጥቅቶ ብዙ ከተሞችን ያዘ።
አልማ 47፥1፣ 35፤ 48፥1–4፤ 51፥23–28
የቴአንኩም ጦር፣ የአማሊቅያ ሠራዊት በኔፋውያን ከተሞች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ለማስቆም ሄደ።
ሠራዊቱ ቀኑን ሙሉ ተዋጉ። ቴአንኩም እና ሠራዊቱ ከአማሊቅያ ሠራዊት በሚበልጥ ጥንካሬ እና ችሎታ ተዋጉ። ነገር ግን የትኛውም ሠራዊት አላሸነፈም። በጨለመ ጊዜ ሁለቱም ሠራዊቶች ለማረፍ ውጊያውን አቆሙ።
አልማ 51፥31—32
ቴአንኩም ግን አላረፈም። እሱ እና አገልጋዩ በድብቅ ወደ አማሊቅያ የጦር ሰፈር ሄዱ።
ቴአንኩም ወደ አማሊቅያ ድንኳን ተደብቆ ገባ። አማሊቅያ ከመንቃቱ በፊት ገደለው። ከዚያም ቴአንኩም ወደ ራሱ የጦር ሰፈር ተመለሰና ወታደሮቹ ለመዋጋት ዝግጁ እንዲሆኑ ነገራቸው።
ላማናውያን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ አማሊቅያ ሞቶ አገኙት። ቴአንኩም እና ሠራዊቱ እነርሱን ለመዋጋት ዝግጁ መሆናቸውንም ተመለከቱ።
ላማናውያን ፈርተው ሸሹ። የቴአንኩም እቅድ ላማናውያን ተጨማሪ የኔፋውያንን ከተሞች ለማጥቃት በጣም እንዲፈሩ አደረጋቸው። ቴአንኩም አሁን የኔፋውያን ከተሞች ደህንነታቸው የተጠበቀ ለማድረግ ጊዜ ነበረው። ህዝቡን ለመጠበቅ ጠንክሮ ሰርቷል። ብዙ የኔፋውያን ከተሞችን ደህንነት ለማስጠበቅ ችሏል።