“ንጉስ ኖህ እና ንጉስ ሊምሂ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]
ንጉስ ኖህ እና ንጉስ ሊምሂ
ከላማናውያን ማምለጥ
ንጉስ ኖህ የኔፋውያንን ቡድን ይገዛ ነበር። ብዙ መጥፎ ነገሮችን አድርጎ ስለነበር አንዳንድ ሰዎች በእሱ ይናደዱ ነበር። ጌዴዎን የሚባል ሰው ከኖህ ጋር በሰይፍ ተዋጋ። ኖህ ሮጦ አንድ ግንብ ላይ ወጣ። በግንቡ ላይ ሆኖ የላማናውያን ሰራዊት ሲመጣ አየ። ኖህ ለህዝቡ እንደፈራ ስላስመሰለ፣ ጌዴዎን በህይወት አተረፈው።
ኖህ እና ህዝቡ ሸሹ። ነገር ግን ላማናውያን አሳደዷቸው ከዚያም እነርሱን ማጥቃት ጀመሩ። ኖህ፣ ወንዶቹ ቤተሰቦቻቸውን ትተው ከእርሱ ጋር እንዲሄዱ ነገራቸው።
አንዳንድ ወንዶች ከኖህ ጋር ሄዱ። ነገር ግን ብዙዎቹ ወንዶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር መሆንን መረጡ። የኖህ ልጅ ሊምሂም መቆየትን መረጠ።
ብዙ ሴት ልጆች በሠራዊቱ ፊት በመቆም ላማናውያን ቤተሰቦቻቸውን እንዳይጎዱ ጠየቁ። ላማናውያን ሴት ልጆቹን ሰሙ እናም ኔፋውያን በህይወት እንዲኖሩ ፈቀዱላቸው። በምትኩ፣ ላማናውያን ኔፋውያንን በምርኮ ያዙ።
ሸሽተው የነበሩት ወንዶች ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ፈለጉ። ኖህ ሊያስቆማቸው በመሞከሩ ሰዎቹ ገደሉት። ከዚያም ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመለሱ።
ወንዶቹ ቤተሰቦቻቸው ደህና በመሆናቸው በጣም ተደሰቱ። ኖህ ላይ የከሰተውን ለጌዴዎን ነገሩት።
ህዝቡ ሊምሂ አዲሱ ንጉሳቸው እንዲሆን መረጡት። ሊምሂ፣ እነርሱ ካላቸው ነገር ግማሹን ለላማናውያን እንደሚከፍሉ ለላማናውያን ንጉሥ ቃል ገባ። በምላሹም፣ የላማናውያን ንጉስ የሊምሂን ህዝብ እንደማይጎዳ ቃል ገባ።
ለብዙ ዓመታት በሰላም ኖሩ። ከዚያም ላማናውያን የሊምሂን ሰዎች መጉዳት ጀመሩ። ህዝቡ ዳግም ነፃ መሆን ፈለገ። ላማናውያንን ለመዋጋት ሞከሩ፣ ነገር ግን ተሸነፉ። ህዝቡ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
አንድ ቀን፣ አሞን የሚባል ኔፋውያን ሊምሂን እና ህዝቡን ጎበኘ። አሞን ዛራሔምላ ከምትባል አገር መጣ። ሊምሂ አሞንን በማየቱ ተደሰተ።
አሞን የሊምሂን ህዝቦች ወደ ዛራሔምላ ሊመራ ይችላል፣ ነገር ግን መጀመሪያ ከላማናውያን ማምለጥ ነበረባቸው። ጌዴዎን እቅድ ነበረው።
በሌሊት፣ የላማናውያን ጠባቂዎች እንዲተኙ ለማድረግ ጌዴዎን ተጨማሪ ወይን ሰጣቸው። ጠባቂዎቹ ተኝተው ሳለ፣ ሊምሂ እና ሁሉም ህዝቦቹ ከከተማው አመለጡ።
ወደ ዛራሔምላ በመሄድ ከኔፋውያን ጋር ተቀላቀሉ። ሊምሂ እና ህዝቡ ስለ እግዚአብሔር የበለጠ ተማሩ። እግዚአብሔርን ለማገልገል እና ትእዛዙን ለመጠበቅ ቃል ኪዳን ወይም ልዩ ኪዳን ገቡ። ተጠምቀው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አካል ሆኑ። እግዚአብሔር ከላማናውያን እንዲያመልጡ እንደረዳቸው አስታወሱ።