Scripture Stories
አልማ በሞርሞን ውሀ አጠገብ


“አልማ በሞርሞን ውሀ አጠገብ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

ሞዛያ 1823

አልማ በሞርሞን ውሀ አጠገብ

የእግዚአብሔር ህዝብ መሆን

ምስል
አልማ ውሃን እየተመለከተ

አልማ ኖህ ለሚባል ንጉሥ ካህን ነበር። አልማ የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነውን አቢናዲ በኖህ ከመገደል ለማዳን ሞከረ። ነገር ግን ኖህ በአልማ ተናደደ፣ ሊገድለውም ፈለገ። አልማ ለደህንነቱ ሲል ከኖህ ሸሸ። ቀን በነበረ ጊዜ፣ አልማ የሞርሞን ውሃ ተብሎ በሚጠራ ቦታ አጠገብ ተደበቀ።

ሞዛያ 17፥2–418፥4–5፣ 8

ምስል
አልማ በውሃ አጠገብ ተንበርክኮ እየጸለየ

አልማ አቢናዲ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረውን አመነ። ኃጢአቱንና ስህተቶቹን ይቅር ይለው ዘንድ እግዚአብሔርን ጠየቀ።

ሞዛያ 18፥1–2

ምስል
አልማ በምሽት በከተማ ውስጥ

አልማ ከሰዎች ጋር በድብቅ በመገናኘት ስለ ኢየሱስ አስተማራቸው። እርሱም ሊሰማ የፈለገን ሁሉ አስተማረ።

ሞዛያ 18፥1–3

ምስል
አልማ ውሃው አጠገብ ሲያስተምር ሰዎች እያዳመጡ

ብዙ ሰዎች አልማን አመኑት። አልማ ሲያስተምር ለመስማት ወደ ሞርሞን ውሃ ሄዱ።

ሞዛያ 18፥3–8፣ 31

ምስል
አልማ በውሃ አጠገብ ቁጭ ብሎ እያስተማረ

ያመኑት የእግዚአብሔር ሰዎች ተብለው ለመጠራት፣ የተቸገሩትን ለመርዳት እና ለሰዎች ስለ እግዚአብሔር ለመናገር ፈለጉ። ስለዚህ አልማ እንዲጠመቁ ጋበዛቸው። በመጠመቅ፣ እርሱን ለማገልገል እና ትእዛዛቱን ለመጠበቅ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ይገባሉ። በምላሹ፣ እግዚአብሔር በመንፈሱ ይባርካቸዋል።

ሞዛያ 18፥8–10፣ 13

ምስል
አልማ አንዲት ሴትን በውሃ እያጠመቀ

ሰዎቹም በጣም ደስተኞች ነበሩ። እጆቻቸውን በማጨብጨብ መጠመቅ እንደሚፈልጉ ተናገሩ። አልማ እያንዳንዳቸውን በሞርሞን ውሃ አጠመቃቸው። ሁሉም በእግዚአብሔር መንፈስ ተሞሉ እንዲሁም እግዚአብሔር ለእነሱ ያለው ፍቅር ተሰማቸው። የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ሆኑ።

ሞዛያ 18፥11–17፣ 30

ምስል
ንጉስ ኖህ በመቆጣት እያመለከተ

ኖህ አንዳንድ ሰዎች አገሩን ለቀው እየወጡ እንደሆነ ተመለከተ። እንዲመለከቷቸው አገልጋዮቹን ላካቸው። አገልጋዮቹ፣ ሰዎች የአልማን ትምህርት ለመስማት ወደ ሞርሞን ምድር ሲሄዱ አዩ። ኖህ በጣም ተናደደ። አልማን እና እሱ የሚያስተምረውን ህዝብ እንዲገድሉ ሰራዊቱን ላከ።

ሞዛያ 18፥31–33

ምስል
አልማ እና ህዝቡ እየተጓዙ

ስለ ሠራዊቱ እግዚአብሔር አልማን አስጠነቀቀ። በእግዚአብሔር እርዳታ አልማ እና ህዝቡ ምድሩን በደህና ለቀው ወጡ። ሰራዊቱ ሊይዟቸው አልቻሉም። ለስምንት ቀናት ያህል በምድረ በዳ ተጉዘው ወደ ውብ ምድር መጡ። እዚያም አዳዲስ ቤቶችን ሠሩ። አልማ ህዝቡን አስተማረ፣ እነሱም ለእግዚአብሔር የገቡትን ቃል ኪዳን ጠበቁ።

ሞዛያ 18፥34–3523፥1–20

አትም