በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ህዝብን አስተማረ


“ኢየሱስ ህዝብን አስተማረ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

3 Nephi 11–27; 4 Nephi 1

ኢየሱስ ህዝብን አስተማረ

ወንጌሉን እንዲማሩ መርዳት

ኢየሱስ ክርስቶስ ደስተኛ ህጻናትን አናገረ፣ እና አያሌ ደስተኛ ሰዎች እነርሱ አካባቢ ተንበርክከዋል እና ያደምጣሉ

በአሜሪካ የነበሩ ህዝቦች ኢየሱስ ክርስቶስን በማየታቸው እና በመስማታቸው ደስተኞች ናቸው። ለአያሌ ዓመታት የአዳኙን መምጣት ይጠባበቁ ነበር።

3 ኔፊ 11፥10፣ 17

ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀመዛሙርቱ እና ከህዝቡ ጋር ይቀመጣል እናም ያስተምራቸዋል።

ኢየሱስ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ያስተማራቸውን ብዙ ተመሳሳይ ነገሮች አስተማራቸው። በኢየሱስ እንዲያምኑ፣ ንስሐ እንዲገቡ እና እንዲጠመቁ አስተማራቸው። ሰዎች ይህን የሚያደርጉ ከሆነ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ይልክላቸዋል። ኢየሱስ እንዴት መጸለይ እንዳለባቸው አስተማራቸው። ሌሎችን ይቅር እንዲሉ አስተማራቸው። እርሱ ለሌሎች ምሳሌ እንዲሆኑ ይፈልግ ነበር።

3 Nephi 11፣31–39; 12፣22–24, 44; 13፣5–14; 17፣8; 18፣15–24

ኢየሱስ ክርስቶስ በፈገግታ ተሞልቷል

ኢየሱስ እርሱ ያስተማራቸውን መረዳት ይችሉ ዘንድ ህዝቡ ወደ ቤታቸው ሄደው እናም ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልዩ ነገራቸው። በሚቀጥለውም ቀን እንደሚመጣ ተናገረ።

3 ኔፊ 17፣1–3

ህዝቡም በእሳት ዙሪያ ተቀምጠዋል እናም እርስ በርሳቸው ይነጋገራሉ

በዚያ ምሽት፣ ህዝቡ ኢየሱስን እንዳዩት ለሌሎች ተናገሩ። እርሱ ስለተናገራቸው እና ስላደረጋቸው ነገሮች ተነጋገሩ። አያሌ ሰዎች ኢየሱስን ለማየት በሌሊት ተጉዘዋል።

3 ኔፊ 19፥1–3

ደቀ መዛሙርቱ ታላቅ ቁጥር ያለውን ህዝብ ያስተምራሉ

በሚቀጥለው ቀን፣ ህዝቡ ከኢየሱስ አስራ ሁለት ደቀ መዛሙርት ጋር ተሰበሰቡ። ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ ያስተማራቸውን ነገሮች በሙሉ ለህዝቡ አስተማሩ። በምድር ላይም ተንበርክከው ጸለዩ።

3 ኔፊ 19፥4–8

ኢየሱስ ክርስቶስ ተንበርክኳል እናም ይጸልያል፣ እና ሌሎች በዙሪያው ያሉ ሰዎችም እንዲሁ ይጸልያሉ

ከዚያም ኢየሱስ መጣ። እርሱም ለደቀመዛሙርቱ እና ለህዝቡ ጸለየ። ደቀመዛሙርቱም ይጸልዩ ነበር፡፡ እነርሱም እንደ አዳኙ ገጽታቸው ያንጸባርቅ ጀመር። ኢየሱስ ደስተኛ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ በእርሱ ባላቸው እምነት ምክንያት ንጹህ ሆኑ። ኢየሱስ ዳግም ጸለየ፣ እና ህዝቡም አስደናቂ ነገሮችን ሲናገር ሰሙት።

3 ኔፊ 19፥15–36

 ደስተኛ ህጻን ኢየሱስ ህዝቡን ሲያስተምር አንድ ሰው መጥቶ እንዲቀላቀል ጋበዘው

ለሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት፣ ኢየሱስ ለህዝቡ ስለሰማይ አባት እቅድ ብዙ ነገሮችን አስተማረ። ቅዱስ ቁርባንንም ከእነርሱ ጋር ተካፈለ። በምድሪቱ የነበረው ህዝብ ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ እና ተጠመቀ። የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ተቀበሉ።

3 ኔፊ 20–274 ኔፊ1፣1–2

ህዝቡ እርስ በርሳቸው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመምጣት ይረዳዳሉ፣ እና ኢየሱስ ክርስቶስም ያናግራቸዋል እና ፈገግ ይላል

ህዝቡ እርስ በርሳቸው ይረዳዱ እና ያላቸውንም ሁሉ ይካፈሉ ነበር። ኢየሱስ እንዲያደርጉት ያዘዛቸውን ሁሉ አድርገዋል። እነርሱም የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተብለው ተጠርተዋል። የሰማይ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ በህዝቡ እጅግ ደስተኞች ነበሩ።

3 ኔፊ 26፥17–2127፥30–314 ኔፊ 1፣3–18