በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች
ኢየሱስ ወደ አባቱ ተለመሰ


“ኢየሱስ ወደ አባቱ ተመለሰ፣” የመፅሐፈ ሞርሞን ታሪኮች [2023 (እ.አ.አ)]

3 ኔፊ 284 ኔፊ 1

ኢየሱስ ወደ አባቱ ተለመሰ

ከመሄዱ በፊት ደቀ መዛሙርቱን ማገልገል

ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰበሰበው ህዝብ ይናገራል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለህዝቡ ወንጌልን አስተማረ። እርሱ እግዚአብሔርን እንዲወዱ እና አንዱ ሌላውን እንዲያገለግል አስተምሯቸዋል። ወዲያውም፣ ኢየሱስ ወደ አባቱ ይመለሳል። እርሱም ከሄደ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ህዝቡን እንዲያስተምሩ ጠየቃቸው።

3 Nephi 11፣41; 28፣1

ኢየሱስ ክርስቶስ ፈገግ አለ እናም እጆቹን ወደላይ አነሳ

ከመሄዱ በፊት፣ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እንዲያደርግላቸው የሚፈልጉትን ጠየቃቸው። አብዛኞቹ ደቀመዛሙርት እርሱን በምድር ካገለገሉ በኋላ ከኢየሱስ ጋር መኖር እንደሚፈልጉ ተናገሩ። ኢየሱስም እነርሱ ከሞቱ በኋላ ከእርሱ ጋር እንደሚኖሩ ቃል ገባላቸው።

3 ኔፊ 28፥1–3

ሶስቱ ደቀ መዛሙርት ተጨንቀዋል

ከደቀመዛሙርቱ ሶስቱ አዝነዋል ምክንያቱም ለኢየሱስ ምን እንደሚፈልጉ ለመናገር በጣም ተጨንቀዋል። ነገር ግን ኢየሱስ እነርሱ ከእርሱ ምን እንደሚሹ ያውቅ ነበር። ብዙ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ ለማምጣት መርዳት ይችሉ ዘንድ እስከ ኢየሱስ ዳግም ምጽአት መኖርን ፈልገዋል።

3 ኔፊ 28፥4–7፣ 9

ኢየሱስ ክርስቶስ ለሶስቱ ደቀ መዛሙርት ይናገራል።

ኢየሱስም እንደማይሞቱ ቃል ገባላቸው። እስከ ዳግም ምጽአቱ ድረስ በምድር ይቆያሉ እናም ሰዎችን ወደ እርሱ ለማምጣት ይረዳሉ።

3 ኔፊ 28፥7–11

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አየር ከፍ አለ እና በብርሃንም ተከበበ

በምድር ላይ ከሚቆዩት ከሦስቱ በስተቀር ኢየሱስ እያንዳንዱን ደቀ መዝሙር በጣቱ ነካ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ተለየ እና ወደ ሰማይ አባትም ሄደ።

3 ኔፊ 28፥1፣12

ሶስቱ ደቀመዛሙርት ተደሰቱ እና በዝግታም እየፈኩ ሄዱ።

ከዚህም በኋላ፣ ሰማያት ተከፈቱ እና ሶስቱ ደቀ መዛሙርት ወደ ሰማይ ተወሰዱ። እነርሱም አያሌ አስደናቂ ነገሮችን ሰሙ እና ተመለከቱ እና ስለነዚህ ነገሮችም እንዳይናገሩ ተነገራቸው። እንዳይሞቱ ወይም ህመም እንዳይሰማቸው ሰውነታቸም ተለወጠ።

3 ኔፊ 28፥13–15፣ 36–40

ደቀመዛሙርትም ህዝብን ያጠምቃሉ፡፡

ደቀ መዛሙርት ተመልሰው መጡ እና ስለ ኢየሱስ ህዝቡን ማስተማራቸውን ቀጠሉ። ህዝቡም ኢየሱስን ለመከተል ፈልገዋል እና ወደ ቤተክርስቲያኑ ተጠምቀዋል። የእግዚአብሔር ፍቅር በልባቸው ነበር፣ እና እርስ በርሳቸውም ያላቸውን ይከፋፈሉ ነበር። ደስተኞች ነበሩ፣ እናም እግዚአብሔር ባረካቸው። እያንዳንዱ ሰው 200 ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በሰላም ኖሩ።

3 ኔፊ 28፥16–18፣ 234 ኔፊ 1፥1–23